የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
አዘጋጅ እና አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
⇒ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለሁለት ሳምንታት ሲያወዛግብ እና ሲራዘም የቆየው የኢትዮጵያ ቡና እና የመቐለ 70 አንደርታ ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ይደረጋል።በ27ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ውስጥ የተካተተው ይህ ጨዋታ በፌድሬሽኑ እና በሁለቱ ክለቦች መሀከል በነበሩ እሰጣ እገባዎች እስከ ዛሬ ሳይደረግ ቆይቶ ነበር።የሁለቱ ክለቦች ደጋፊ ማህበሮችም በትናንትናው ዕለት ዕርቀ-ሰላም አካሂደዋል።
የባህር ማዶ ስፖርታዊ ዜናዎች
⇒ብራዚላዊው አጥቂ ድራማዊ በሆነ መልኩ ወደ ካታሎኒያ ሊመለስ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
Globoesporte እንደዘገበው ባርሴሎና ከክለቡ ፓሪሰም ዤርመን ጋር የ27 አመቱን አጥቂ በማስፈረም ጉዳይ ላይ ድርድር ጀምሯል።ኔይማር የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ አንስቶ ስሙ በስፋት ከተለያዩ ሀያል የአውሮፓ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ሲሆን ወደ ብሉግራናዎቹ ይሄዳል የሚለው ዜና ግን ሚዛን እየደፋ ይመስላል።
ጋዜጣው እንደዘገበው ባርሳ ያቀረበው €100ሚ. ሲሆን ከገንዘቡ በተጨማሪ ሳሚኤል ኡምቲቲ ፥ ኦስማን ዴምቤሌ እና ኢቫን ራኪቲችም የዝውውር አካል እንዲሆኑ ይፈልጋል።
ትናንት ከኔይማር ጋር በተያያዘ ጥያቄ የቀረበለት የቀድሞው የክለብ አጋሩ ሊውስ ሱዋሬዝ "ማን ነው ኔይማርን የማይፈልገው ክለብ?" በማለት ተጨዋቹ በሁሉም ክለቦች የሚፈለግ ትልቅ ተጨዋች መሆኑን ተናግሮ ወደ ካምፕ ኑ ቢመጣ እንደሚደሰት ተናግሯል።
የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቲቴ ደግሞ "ኔይማር መጫወት ያለበት የሚያስደስተው ክለብ ውስጥ ነው" በማለት ተናግረዋል።
(Globoesporte)
⇒ታላቁ 'የሮማው ጣኦት' ፍራንቼስኮ ቶቲ ትናንት ከ30 አመት በኋላ ከሮማ ጋር መለያየቱ እውን ሆኗል።ቶቲ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የተጫወተበትን እና በታማኝነት ያገለገለበትን ክለብ ትናንት ነው መልቀቁን ይፋ ያደረገው።ቶቲ ከሁለት አመት በፊት ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ላለፉት ሁለት አመታት በስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ነበር ሲሰራ የሰነበተው።
ትናንት ከስንብቱ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ቶቲ ምክንያቱን ሲናገር በተጨዋቾች ዝውውርም ላይ ሆነ በወሳኝ የክለቡ ጉዳዮች ላይ የሱ አስተዋፅኦን ክለቡ አለመቀበሉ መሆኑን ተናግሯል።ቶቲ ሳምፕዶሪያን በስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት እንደሚረከብ ይጠበቃል።
(Goal)
⇒ማን ዩናይትድ ለራሽፎርድ አዲስ ኮንትራት እንዳቀረበለት The Times ዘግቧል።ጋዜጣው እንዳተተው ከሆነ እንግሊዛዊው ተስፈኛ ታዳጊ አጥቂ ስሙ በስፋት ከተለያዩ ክለቦች ጋር መያያዙን ተከትሎ ነው ቀያይ ሰይጣኖቹ አዲስ ኮንትራት ያቀረቡለት።
ራሽፎርድ በኦልድ ትራፎርድ እስከ ቀጣዩ አመት የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ሲሆን ዩናይትድ ተጨዋቹን የረዥም ጊዜ ኮንትራት ነው ማስፈረም የሚፈልገው።የማን ዩናይትድ ደጋፊዎች ግን ከክለባቸው አካዳሚ ያደገውን እና የሚወዱትን ተጨዋች ክለቡ እንዲያቆይላቸው ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።
(The Times)
⇒ንብረትነቱ የሪያል ማድሪድ የሆነው ሀሜስ ሮድሪጌዝ ወደ ጣሊያኑ ክለብ ናፖሊ ለመሄድ በመርህ ደረጃ መስማማቱን ታዋቂው ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ጂያንሉካ ዲማርዚዮ ዘግቧል።
ለሁለት አመታት በውሰት በባየርን ሙኒክ ሲጫወት የነበረው ኮሎምቢያዊ ኮከብ በባቫሪያው ክለብ ያለውን ጊዜ ጨርሶ ወደ ማድሪድ የተመለሰ ሲሆን ሎስብላንኮዎቹ ተጨዋቹን በቋሚነት መሸጥ ይፈልጋሉ።
(Gianluca Di Marzio)
⇒የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ሮበርቶ ማርቲኔዝ ሮሜሮ ሉካኩ የተጨዋችነት ህይወቱን መስመር ለማስያዝ ከማንቸስተር ዩናይትድ እንዲለቅ እና ቋሚ ተሰላፊ ወደ ሚያደርገው ክለብ መሄድ እንዳለበት መክረውታል።
የ26 አመቱ ተጨዋች በተለይ ባሳለፍነው አመት ሁለተኛ ሲዝን እምብዛም የመሰለፍ ዕድል አልተሰጠውም ነበር ፥ ስሙም በስፋት ከአንቶኒዮ ኮንቴው ኢንተር ሚላን ጋር በመያያዝ ላይ ነው።
(Goal)
⇒አዲሱ የጁቬንትስ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ትላልቅ ተጨዋቾችን ወደ ቱሪን ለማምጣት ከወዲሁ ሽር ጉድ ጀምረዋል።
ፖል ፖግባ ፥ ሰርጂ ሚሊንኮቪች ሳቭች ፥ ፌድሪኮ ቼዛ እና ኒኮላ ዛኒዬሎ የአሮጊቷ በኩል የታቀዱ ተጨዋቾች ናቸው።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን የማሳካት ከፍተኛ ሀላፊነት የተጣለባቸው ሳሪ ከክለቡ ይወጣል እየተባለ ያለው ፓውሎ ዲባላም በቱሪን እንዲቆይ ይፈልጋሉ።
(La Gazzetta dello Sport)
⇒ሳሪን ያሰናበተው ቼልሲ በምትኩ የቀድሞ ሌጀንዱን ፍራንክ ላምፓርድ ለመሾም ጥረት እያደረገ ሲሆን ደርቢ ካውንቲ ደግሞ ጆን ቴሪን የላምፓርድ ምትክ አድርጎ መሾም ይፈልጋል ፥ ላምፓርድ ከለቀቀ።
(Daily Mail)
⇒ማን ዩናይትድ ፖል ፖግባን ለማቆየት ሳምንታዊ £500,000 ሊያቀርብለት ነው።ቀያይ ሰይጣኖቹ ደሞዙን በዚህ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያሰቡት ፈረንሳዊውን ኢንተርናሽናል ከኦልድ ትራፎርድ ለመውጣት ከጫፍ መድረሱን ተከትሎ ነው።የ27 አመቱ አማካይ በባርሴሎና ፥ በሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና በጥብቅ ይፈለጋል።

No comments:
Post a Comment