አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
በአራት የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በተለያዩ ክለቦች ዋንጫዎችን ያሳኩት ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በቀጣይ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው ብሔራዊ ቡድኖችን ማሰልጠን ላይ ትኩረት እንደሚያደረጉ ተናገሩ።
አወዛጋቢው አሰልጣኝ ከማንቸስተር ዩናይትድ ከተሰናበቱ አንስቶ ከአሰልጣኝነት እርቀው በቢን ስፖርት በተንታኝነት በመስራት ላይ ሰንብተዋል።
ትናንት Eleven Sports ላይ በነበራቸው ቃለ ምልልስ የ56 አመቱ ሰው ወደ አሰልጣኝነት ለመመልስ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።
"በአዳዲስ ውድድሮች ላይ መሳተፍ እፈልጋለው።በአለም ዋንጫ ወይም በአውሮፓ ዋንጫ ላይ።ለረዥም ጊዜያት ሳስብበት ሰንብቻለው ፥ እናም አሁን ከክለብ ይልቅ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን ነው ያሰብኩት።
ምናልባት ፖርቱጋልን ሊሆን ይችላል? አላውቅም።"
ራሳቸውን "ዘ ስፔሻል ዋን" በማለት የሚጠሩት ጆዜ የመጀመሪያ ስኬታቸውን 2003 ላይ ፖርቶን በመያዝ የሊጉን ዋንጫ ያሳኩ ሲሆን በአመቱም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ድል ተቀዳጅተዋል።
ከዚያም በቼልሲ ቤት በተከታታይ 2005 እና 2006 ፕሪሚየር ሊጉን ያሳኩ ሲሆን ተጨማሪ አራት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችንም አሳክተዋል።
ወደ ሀገረ ጣሊያንም ተጉዘው ኢንተር ሚላንን 2010 ላይ ሻምፒዮንስ ሊጉን እንዲያሳካ አድርገዋል፡፡
ሞሪንሆ ወደ ስፔንም ተጉዘው ከሪያል ማድሪድ ጋር 2012 ላይ ስፔን ላሊጋን ማሳካታቸው የሚታወስ ሲሆን በማን ዩናይትድ ቤትም ዩሮፓ ሊግን አሳክተዋል።
No comments:
Post a Comment