አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
ድሬዳዋ ከተማ ዮናታን ከበደ፣ ኃይሌ እሸቱ እና ወሰኑ ማዜ
ክለቡ ቀሪ የውል ኮንትራት እያለን ያለአግባብ አሰናብቶናል
በሚል ለፌድሬሽኑ ክስ ማስገባታቸው ይታወሳል፡፡ ፌድሬሽኑ
ጉዳዩን ሲመለከት ከቆየ በኃላ ደመወዛቸውን እንዲከፍል፤
በአስር ቀናት ውስጥም ተግባራዊ እንዲያደርግ ፌድሬሽኑ
መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ድሬዳዋ የፌዴሬሽኑ ወሳኔን
በመቃወም ባለፈው ሳምንት መግለጫ የሰጠ ሲሆን
ፌድሬሽኑ በድጋሚ ትላንት ውሳኔውን ተግባራዊ
እንዲያደርግ አስጠንቅቋል።
ምንጭ- ሶከር ኢትዮጵያ ድህረ-ገፅ
ምንጭ- ሶከር ኢትዮጵያ ድህረ-ገፅ
የባህር ማዶ ዜናዎች
- ዛሬ በብራዚል አስተናጋጅነት እየተደረገ ያለው 46ተኛው ኮፓ አሜሪካ ሲቀጥል በምድብ ሁለት ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።የምድቡ መሪ ኮሎምቢያ 6:30 ኳታርን ስትገጥም ለሊት 9:30 ደግሞ አርጀንቲና ከ ፓራጓይ ይጫወታሉ።በ0 ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ያለችው አርጀንቲና ከዚህ ጨዋታ 3 ነጥብ ካላገኘች ከምድቡ የማለፏ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል ፥ ሊዮኔል ሜሲም ሀገሩን የመታደግ ከፍተኛ ሀላፊነት ተጥሎበታል።
ሊውስ ኤንሪኬ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነቱ ሊለቅ ነው።የቀድሞ የባርሴሎና አጥቂ ላ ሮሃዎቹ ባደረጓቸው ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች በግል ችግር ምክንያት ሜዳ ውስጥ አልተገኘም ነበር።በዚህም ምክንያት ከነ ምክትል አሰልጣኙ ሮቤርቶ ሞሬኖ ስፔን አሰልጣኞቿን ማሰናበቷን በቀናት ውስጥ ይፋ ታደርጋለች።
(AS)
ማንቸስተር ሲቲ የቀኝ መስመር ተከላካዩን ካይል ዎከር ተጨማሪ ኮንትራት ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።ውሃ ሰማያዊዎቹ እንግሊዛዊውን ተከላካይ ለተጨማሪ ሁለት አመታት በኢቲሃድ እንዲቆይ ያስፈረሙት ሲሆን በአጠቃላይ ከዛሬው ውል ጋር እስከ 2024 የሚያቆይ ኮንትራት ፈርሟል።
(Goal)
ቦሩሲያ ዶርትመንድ የቀድሞ ተጨዋቹን ማትስ ሂውመልስ ከባየር ሙኒክ በድጋሚ አስፈርሟል።
የ30 አመቱ ተከላካይ ከዚህ በፊት ለስምንት አመታት በዶርትመንት ተጫውቶ ነበር ወደ ሀያሉ ክለብ ባየርን ሙኒክ 2016 ላይ የተጓዘው ፥ በባቫሪያው ክለብ በነበረው ሶስት አመትም በተከታታይ ክለቡ የጀርመን ቡንደስሊጋን ሲያሳካ የቡድኑ አካል ነበር።
(Goal)
ፒ.ኤስ.ጂ የጁቬንትሱን ዊንገር ዳግላስ ኮስታ ለማዘዋወር ወጥኖ በመስራት ላይ ይገኛል።የ28 አመቱ ብራዚላዊ በቱሪን ያለፈውን አመት አብዛኛውን ጊዜ በጉዳት ቢያሳልፍም የፓሪሱ ክለብ ግን ኔይማርን የመልቀቁ ጉዳይ ዕውን እየሆነ ስለመጣ ተጨዋቹን ይፈልገዋል።
(reports Sportitalia)
በአራት የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በተለያዩ ክለቦች ዋንጫዎችን ያሳኩት ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በቀጣይ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው ብሔራዊ ቡድኖችን ማሰልጠን ላይ ትኩረት እንደሚያደረጉ ተናገሩ።
አወዛጋቢው አሰልጣኝ ከማንቸስተር ዩናይትድ ከተሰናበቱ አንስቶ ከአሰልጣኝነት እርቀው በቢን ስፖርት በተንታኝነት በመስራት ላይ ሰንብተዋል።
ትናንት Eleven Sports ላይ በነበራቸው ቃለ ምልልስ የ56 አመቱ ሰው ወደ አሰልጣኝነት ለመመልስ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ከዚያም በቼልሲ ቤት በተከታታይ 2005 እና 2006 ፕሪሚየር ሊጉን ያሳኩ ሲሆን ተጨማሪ አራት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችንም አሳክተዋል።
ወደ ሀገረ ጣሊያንም ተጉዘው ኢንተር ሚላንን 2010 ላይ ሻምፒዮንስ ሊጉን እንዲያሳካ አድርገዋል፡፡
ሞሪንሆ ወደ ስፔንም ተጉዘው ከሪያል ማድሪድ ጋር 2012 ላይ ስፔን ላሊጋን ማሳካታቸው የሚታወስ ሲሆን በማን ዩናይትድ ቤትም ዩሮፓ ሊግን አሳክተዋል።
(Eleven Sports)
ከኦልድ ትራፎርድ የመውጫ በር ላይ ያለ የሚመስለው ፖል ፖግባ ከሪያል ማድሪድ ይልቅ ምርጫው ጁቬንትስ መሆኑ ተነግሯል።የ26 አመቱ አማካይ አዲስ ክለብ እንደሚፈልግ በግልፅ የተናገረ ሲሆን ማን ዩናይትድ ግን ከፍተኛ የሆነ የደሞዝ ጭማሪ አድርጎለት በክለቡ ሊያቆየው ይፈልጋል።
(Sky Sports)
ቼልሲ ላምፓርድን በዋና አሰልጣኝነት በዚህ ሳምንት እንደሚሾም ይጠበቃል።ቼልሲ ከደርቢ ካውንቲው አሰልጣኝ ጋር እንደተነጋገረም ታውቋል።እንደ Evening Standard ዘገባ ላምፓርድ በተጨዋችነት የምንጊዜም ግብ አስቆጣሪ ወደ ሆነበት ክለብ በአሰልጣኝነት ለሶስት አመታት የሚቆይበት ኮንትራት እንደሚሰጠው ይጠበቃል።
(Evening Standard)
ኔይማር ለፒ.ኤስ.ጂ አመራሮች ወደ ባርሴሎና መመለስ እንደሚፈልግ ነግሯቸዋል ሲል የካታላኑ ጋዜጣ Mundo Deportivo ዘግቧል።ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ሁለት ያልተሳኩ አመታትን በፓርክ ደ ፕሪንስ ካሳለፈ በኋላ ወደ ብሉግራናዎቹ መመለስ እንደሚሻ በግልፅ ለፓሪሱ ክለብ ፕሬዝደንት ናስር አል-ኻላፊ ነግሯቸዋል ነው የተባለው።ጋዜጣው እንዳለው ኔይማር ቃል በቃል ለፕሬዝደንቱ "ከዚህ በላይ እዚህ መቆየት አልፈልግም ፥ ቤቴ ወደ ሆነው ክለብ መመለስ እፈልጋለው " ነው ያላቸው።
(Mundo Deportivo)

"በአዳዲስ ውድድሮች ላይ መሳተፍ እፈልጋለው።በአለም ዋንጫ ወይም በአውሮፓ ዋንጫ ላይ።ለረዥም ጊዜያት ሳስብበት ሰንብቻለው ፥ እናም አሁን ከክለብ ይልቅ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን ነው ያሰብኩት።ምናልባት ፖርቱጋልን ሊሆን ይችላል? አላውቅም።"
ራሳቸውን "ዘ ስፔሻል ዋን" በማለት የሚጠሩት ጆዜ የመጀመሪያ ስኬታቸውን 2003 ላይ ፖርቶን በመያዝ የሊጉን ዋንጫ ያሳኩ ሲሆን በአመቱም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ድል ተቀዳጅተዋል።ከዚያም በቼልሲ ቤት በተከታታይ 2005 እና 2006 ፕሪሚየር ሊጉን ያሳኩ ሲሆን ተጨማሪ አራት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችንም አሳክተዋል።
ወደ ሀገረ ጣሊያንም ተጉዘው ኢንተር ሚላንን 2010 ላይ ሻምፒዮንስ ሊጉን እንዲያሳካ አድርገዋል፡፡
ሞሪንሆ ወደ ስፔንም ተጉዘው ከሪያል ማድሪድ ጋር 2012 ላይ ስፔን ላሊጋን ማሳካታቸው የሚታወስ ሲሆን በማን ዩናይትድ ቤትም ዩሮፓ ሊግን አሳክተዋል።
(Eleven Sports)
ከኦልድ ትራፎርድ የመውጫ በር ላይ ያለ የሚመስለው ፖል ፖግባ ከሪያል ማድሪድ ይልቅ ምርጫው ጁቬንትስ መሆኑ ተነግሯል።የ26 አመቱ አማካይ አዲስ ክለብ እንደሚፈልግ በግልፅ የተናገረ ሲሆን ማን ዩናይትድ ግን ከፍተኛ የሆነ የደሞዝ ጭማሪ አድርጎለት በክለቡ ሊያቆየው ይፈልጋል።
(Sky Sports)
ቼልሲ ላምፓርድን በዋና አሰልጣኝነት በዚህ ሳምንት እንደሚሾም ይጠበቃል።ቼልሲ ከደርቢ ካውንቲው አሰልጣኝ ጋር እንደተነጋገረም ታውቋል።እንደ Evening Standard ዘገባ ላምፓርድ በተጨዋችነት የምንጊዜም ግብ አስቆጣሪ ወደ ሆነበት ክለብ በአሰልጣኝነት ለሶስት አመታት የሚቆይበት ኮንትራት እንደሚሰጠው ይጠበቃል።
(Evening Standard)
ኔይማር ለፒ.ኤስ.ጂ አመራሮች ወደ ባርሴሎና መመለስ እንደሚፈልግ ነግሯቸዋል ሲል የካታላኑ ጋዜጣ Mundo Deportivo ዘግቧል።ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ሁለት ያልተሳኩ አመታትን በፓርክ ደ ፕሪንስ ካሳለፈ በኋላ ወደ ብሉግራናዎቹ መመለስ እንደሚሻ በግልፅ ለፓሪሱ ክለብ ፕሬዝደንት ናስር አል-ኻላፊ ነግሯቸዋል ነው የተባለው።ጋዜጣው እንዳለው ኔይማር ቃል በቃል ለፕሬዝደንቱ "ከዚህ በላይ እዚህ መቆየት አልፈልግም ፥ ቤቴ ወደ ሆነው ክለብ መመለስ እፈልጋለው " ነው ያላቸው።
(Mundo Deportivo)
No comments:
Post a Comment