ሜሲ ግብ ቢያስቆጥርም አርጀንቲና አሁንም ማሸነፍ አልቻለችም
ትናንት በኮፓ አሜሪካ በምድብ ሁለት በተደረገው ጨዋታ አርጀንቲና ከ ፓራጓይ ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።በጨዋታው የፓራጓዩ ኢቫን ፔሪስ በእጁ የነካው ኳስ በVAR አማካይነት ወደ ፍፁም ቅጣት ምትነት ተለውጦ ሜሲ በ57ተኛው ደቂቃ አስቆጥሮታል።
ሪቻርድ ሳንቼዝ ደግሞ በ37ተኛው ደቂቃ የፓራጓይን ግብ በስሙ ያስመዘገበው ተጨዋች ነው።ፓራጓይ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ የነበር ቢሆንም ዴርሊስ ጎንዛሌዝ የመታውን ኳስ ፍራንሶ አርማኒ መልሷታል።ከሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ያገኘችው አርጀንቲና ከምድቡ ለማለፍ እሁድ ተጋባዧን ሀገር ኳታር ማሸነፍ የግድ እና የግዷ ሆኗል።ማሸነፍ ብቻ ግን አያሳልፋትም ፥ ምክንያቱም ፓራጓይ በቀጣዩ ጨዋታ ካሸነፈች የአርጀንቲና ከምድቡ ማለፍ ህልም ሆኖ ይቀራል።
የምድብ ሁለት ደረጃ
የሀገራት ስም ተጫወተ ንፁ ግብ ነጥብ
1.ኮሎምቢያ 2 2 6
2.ፓራጓይ 2 0 2
3.ኳታር 2 -1 1
4..አርጀንቲና 2 -2 1
No comments:
Post a Comment