ሜሲ አሁንም አርጀንቲናን መታደግ አልቻለም
አዘጋጅ እና አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)
ለሊት 7 ሰዓት በተደረገው የኮፓ አሜሪካ ምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ አርጀንቲና በ ኮሎምቢያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።
ልክ እንደ ተገመተው የላቲን አሜሪካ እግር ኳስ ሀይል እና ጉልበትን የቀላቀለ እንደመሆኑ በጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች በኩል በድምሩ 30 ጊዜ ጥፋቶች ተሰርተዋል ፥ አርጀንቲና (13) ኮሎምቢያ (17)።
አርጀንቲና በጨዋታው 11 ጊዜ የግብ ሙከራ ያደረገች ሲሆን 6ቱ ኢላማቸውን የጠበቁም ነበሩ ፥ ምንም እንኳን ፍሬ አልባ ቢሆኑም።በተቃራኒው የጨዋታውን አሸናፊ ኮሎምቢያ ስንመለከት 6 ጊዜ የግብ ሙከራ አድርገው 2ቱ ኢላማቸውን የጠበቁ ነበሩ ፥ ሁለቱም ኳሶችም ወደ ግብነት ተቀይረዋል።
የኳስ ቁጥጥርን ስንመለከት አርጀንቲና (52%) ኮሎምቢያ ደግሞ (48%) ነበር።ጨዋታው እስከ ለሰባ ደቂቃዎች ያህል ያለ ግብ ቢጓዝም 71 ደቂቃ ላይ ማርቲኔዝ ከ ሀሜስ ሮድሪጌዝ የተላከለትን ኳስ ወደ ግብነት በመቀየር አሀዱ አለም ፥ ከዚያም መደበኛው የጨዋታ ክፈለ ጊዜ ሊገባደድ አራት ደቂቃዎች ሲቀሩት ዛፓታ አንድ ግብ አክሎ የካርሎስ ኪሮዧ ኮሎምቢያ ከመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ወሳኝ ሶስት ነጥቧን አግኝታለች።
ከጨዋታው በኋላ አርጀንቲና ሁል ጊዜ ድል ሲርቃት ትችቶች ሚዥጎደጎዱበት ሜሲ አሁንም እነዚያን ትችቶች ማስተናገዱን ቀጥሏል።ብዙዎች ግን ሜሲ ብቻውን ከቡድኑ ተነጥሎ መተቸት የለበትም እያሉ ነው።
No comments:
Post a Comment