ዕለተ ቅዳሜ የወጡ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ስፖርታዊ ዜናዎች
አዘጋጅ እና አቅራቢ አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
ሴናፍ ዋቁማ እና ሰናይት ቦጋለ
⇛ሁለቱ የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ሴናፍ ዋቁማ እና ሰናይት ቦጋለ
ለአስር ቀናት ሙከራ ወደ ስውዲን ትላንት ተጉዘዋል ፡፡
በዘንደሮው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዲቪዚዮን
በአዳማ ከተማ የሴቶች ቡድን ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ
የነበራቸው እና ከክለቡ ጋር የ2011 የሊጉ ቻምፒዮን
በመሆን ዓመቱን በድል የጨረሱት አማካዩዋ ሰናይት ቦጋለ
እና የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ክብርን ያገኘችሁ አጥቂዋ
ሴናፍ ዋቁማ ለአስር ቀናት የሙከራ ጊዜን በስውዲን
ለማሳለፍ ትላንት አመሻሽ ወደ ስፍራው አቅንተዋል፡፡ ይህን
ዕድል እንዲያገኙ ያስቻለው አሰልጣኝ ዐቢይ ካሳሁን
እንደሆነ ለሶከር ኢትዮጵያ የተናገሩት ተጫዋቾቹ በሙከራ
ጊዜያቸው የተሻለ ቆይታን አሳልፈው በስውዲን ሊግ ውስጥ
ለመታየት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
በአዳማ ከተማ ወጪያቸው ተሸንፍኖላቸው ወደ ስፍራው
የሚያመሩት ሁለቱ ተጫዋቾች ለስውዲኑ ክለብ አይኤፍ ኬ
አልካማር በተባለ ክለብ ነው የሙከራ ጊዜያቸውን
የሚያሳልፉት። በቅርቡ ቱቱ በላይ እና ሎዛ አበራ ረዘም ያለ
የሙከራ ጊዜን ያሳለፉ ሲሆን ከገንዘብ ጋር በተያያዙ
ጉዳዮች ሳይስማሙ በመቅረታቸው መመለሳቸው
ይታወሳል ፥ ሲል ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።
ምንጭ - Soccer Ethiopia
የባህር ማዶ ስፖርታዊ ዜናዎች
ሪቤሪ ወደ ሌላ ታላቅ ክለብ?
ከበርካታ ስኬታማ አመታት በኋላ ከባየርን ሙኒክ ጋር ዘንድሮ የተለያየው ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ፍራንክ ሪቤሪ ወደ ሌላ ታላቅ ክለብ በመሄድ መጫወት እንደሚፈልግ ተናገረ።የ36 አመቱ ሰው ከፈረንሳዩ ጋዜጣ L’Equipe ጋር ባደረገው ሰፋ ያለ ቆይታ " አሁንም ብዙ ነገር ማድረግ እንደምችል ይሰማኛል፥ ለተጨማሪ ሁለት አመታትም ለመጫወት አስቢያለው " ብሏል።
(L'Equipe)
ማን ዩናይትድ ቴልማዝን ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል
ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጄሚያዊውን ኢንተርናሽናል ዮሪ ቴልማዝ ለማዘዋወር ጠንክሮ እየሰራ ነው ሲል HLN አስነብቧል።በውሰት አመቱን በሌስተር ሲቲ ቤት አሳልፎ የነበረው አማካዩ በዚህ የዝውውር መስኮት ክለቡ ሞናኮ በቋሚነት ሊሸጠው ይፈልጋል።
(HLN)
ሚላን ሎቭረንን ለማዘዋወር እንቅስቃሴ ጀምሯል
ኤሲ ሚላን የሊቨርፑሉን ተከላካይ ዲያን ሎቭረን ወደ ሳንሴሮ ጁሴፔ ሚዬዛ ለማዘዋወር ከቀያዮቹ ጋር ድርድር መጀመሩን Milan News አትቷል።ክሮሺያዊው ኢንተርናሽናል በአንፊልድ ደስተኛ ቢሆንም በቋሚነት መሰለፍን ግን አጥብቆ ይሻል።ጀርመናዊው የጌጌም ፕረሲንግ አቀንቃኝ ጀርደን ክሎፕ ግን ከሱ ይልቅ ባሳለፍነው ሲዝን ጆይል ማቲፕን ነበር ሲያሰልፉ የቆዩት።
(Milan News)
የፍራንክ ላምፓርድ ቀጣይ ማረፊያ?
ደርቢ ካውንቲ አሰልጣኙን ፍራንክ ላምፓርድ ለተጨማሪ አመታት ለማቆየት ድርድር ጀምሯል።ላምፓርድ ባሳለፍነው አመት የሻምፒየንስ ሺፑን ክለብ ይዞ ወደ ሊጉ ለማደግ ከጫፍ ደርሶ ሳይሳካለት ቢቀርም ገና በአሰልጣኝነት ህይወቱ መጀመሪያ ይህንን ማሳየቱ በተለይ በቀድሞ ክለቡ ቼልሲ አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።ማውሪዚዮ ሳሪን ወደ ጁቬንትስ ለመሸኘት የቆረጡ የሚመስሉት ሰማያዊዎቹም የቀድሞ ኮከባቸውን በጥብቅ ይሹታል።
(Sky Sports)
ሪያል ማድሪድ ሁለት አማካዮቹን መሸኘት ይፈልጋል
ሎስብላንኮዎቹ ሁለት አማካዮቻቸውን በውሰት ከክለባቸው ለመሸኘት እየሰሩ ነው ……… ሉካስ ቫስኩዌዝ እና ብራሂም ዲያዝን።ሪያል ማድሪድ ሀዛርድን ካስፈረመ በኋላ የቋሚነት ቦታ እንደማይኖረው የተረዳው ሉካስ ቫስኩዌዝ ምናልባትም ሊሸጥ እንደሚችልም ተነግሯል።የ19 አመቱ ብራሂም ዲያዝ ግን ዚነዲን ዚዳን ለበርካታ አመታት ተተኪ እንደሚሆን ስለሚያስብ ለጊዜው በውሰት ሌላ ክለብ እንዲቆይ ነው የሚፈልገው።
(Marca)
ማን ዩናይትድ አሁንም ዋን ቢሳካን ለማዘዋወር ጥረቱን ቀጥሏል
ቀያይ ሰይጣኖቹ በዚህ የዝውውር መስኮት ከሚፈልጓቸው ክለቦች አንዱ የሆነው ዋን ቢሳካ መሆኑ የዋለ ያደረ ዜና ቢሆንም ክለቡ ክሪስታል ፓላስ ግን ቀላል ተደራዳሪ ሆኖ አልተገኘም።
ከዚህ በፊት £40ሚ አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ዩናይትድ አሁን ሂሳቡን ከፍ በማድረግ £60ሚ አቅርቧል።የ21 አመቱ ፉል ባክ በኦሊ ጉናር ሶልሻየር በጥብቅ ነው የሚፈለገው።
(the Guardian)
ኢንተር ኢካርዲን ከዚህ በፊት ከተመነለት ባነሰ ሊሸጠው ነው
ኢንተር ሚላን አርጀንቲናዊውን አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ £70ሚ ቢተምነውም ፈቃደኛ የሆነ ክለብ ባለመኖሩ እና ተጨዋቹ ከክለቡ የመልቀቅ ፍላጎት ስላለው ከዚህ በፊት ከተመነለት ባነሰ ዋጋ ለጁቬንትስ ለመሸጥ አስቧል።ኢንተር ከአሮጊቷ እዚህ ዝውውር ላይ ፓውሎ ዲባላ አሊያም ሁዋን ኩዋድራዶ እንዲታከለም ትፈልጋለች።
(Gazetta)
ለዝውውር £40ሚ ብቻ በመተመን ለኡናይ ኤምሬ ያሰናዳው የአርሰናል አስተዳደር ይህ ገንዘብ ከጊዜው የገበያ ዋጋ አንፃር አነስተኛ በመሆኑ ኦዚልን በመሸጥ ሌላ የገንዘብ ምንጭ መፍጠርን አስቧል።
የቱርኮቹ ክለቦች ጋላታሳራይ ፥ ፌነርባቼ እና ቤስኪታሽ የተጨዋቹ ዋነኛ ፈላጊዎች ናቸው።
(the Sun)
No comments:
Post a Comment