የእሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)
ሊቨርፑል ለግብፃዊው የ27 አመት ኢንተርናሽናል መሀመድ ሳላህ ከሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ £150ሚ. ቢቀርብለትም ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።ተጨዋቹም ከቀያዮቹ ቤት መውጣትን አይፈልግም።
(Mirror)
ፈረንሳዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ ወደ ሪያል ማድሪድ ይሄዳል የሚለው ዜና እውን ለመሆን የተቃረበ ይመስላል።ተጨዋቹ ለማንቸስተር ዩናይትድ አመራሮችም ወደ በርናቢዮ መጓዝ እንደሚፈልግ ነግሯቸዋል ነው የተባለው።ዚዳን ፖግባን በጥብቅ ይፈልገዋል።
(ABC - in Spanish)
ማንቸስተር ዩናይትድ የዌስት ሀሙን ፈረንሳዊ ተከላካይ ኢሳ ዲዮፕ ለማዘዋወር ጥያቄ አቅርቧል።ስካይ ስፖርትስ እንደዘገበው ከሆነም ቀያይ ሰይጣኖቹ £45ሚ. አቅርቧል።
(Sky Sports)
ብራዚላዊው የ22 አመት አጥቂ ጋብሬል ጄሱስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት እሱም ሆነ አጋሩ ሰርጂዮ አጉዌሮ ከማንቸስተር ሲቲ እንደማይለቁ ተናግሯል።ጄሱስ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በቋሚነት የመሰለፍ ዕድል በፔፕ ጋርዲዮላ እምብዛም አልተሰጠውም ነበር።
(Mail)
ጁቬንትስ የቶተንሃሙን እንግሊዛዊ ዊንገር ኬረን ትሮፒየ ለማዘዋወር £45ሚ. አቅርቧል።አሮጊቷ በተለይ በቀጣዩ አመት ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ሙሉ ትኩረቷን አድርጋ ለመስራት በማሰቧ በርካታ ተጨዋቾችን እንደምታስፈርም ይጠበቃል።
(Times - subscription required)
ቤልጄሚያዊው አጥቂ ክርስቲያን ቤንቴኬ ምንም እንኳን ከቻይና ብዙ የዝውውር ጥያቄዎች ቢቀርቡለትም እርሱ ግን በክሪስታል ፓላስ መቆየትን ይፈልጋል።
(Standard)
ፈረንሳዊው የቼልሲ አማካይ ቲሙ ባካዮኮ አንድ ቀን ለፓሪሰን ዤርመን መጫወት እንደሚፈልግ መናገሩን ተከትሎ ስሙ በስፋት ከፓሪሱ ክለብ ጋር በመገናኘት ላይ ይገኛል።
(L'Equipe - in French)
ጀርደን ክሎፕ የክለባቸው ሁለተኛ ግብ ጠባቂ ሲሞን ሚኞሌት በዚህ የዝውውር መስኮት እንደሚለቅ ስለሚጠበቅ በምትኩ የሳውዝሀምተኑን አሌክስ ማካርቲ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል።
(Star)
ሜሲ አሁንም አርጀንቲናን መታደግ አልቻለም
ለሊት 7 ሰዓት በተደረገው የኮፓ አሜሪካ ምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ አርጀንቲና በ ኮሎምቢያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።
ልክ እንደ ተገመተው የላቲን አሜሪካ እግር ኳስ ሀይል እና ጉልበትን የቀላቀለ እንደመሆኑ በጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች በኩል በድምሩ 30 ጊዜ ጥፋቶች ተሰርተዋል ፥ አርጀንቲና (13) ኮሎምቢያ (17)።
አርጀንቲና በጨዋታው 11 ጊዜ የግብ ሙከራ ያደረገች ሲሆን 6ቱ ኢላማቸውን የጠበቁም ነበሩ ፥ ምንም እንኳን ፍሬ አልባ ቢሆኑም።በተቃራኒው የጨዋታውን አሸናፊ ኮሎምቢያ ስንመለከት 6 ጊዜ የግብ ሙከራ አድርገው 2ቱ ኢላማቸውን የጠበቁ ነበሩ ፥ ሁለቱም ኳሶችም ወደ ግብነት ተቀይረዋል።
የኳስ ቁጥጥርን ስንመለከት አርጀንቲና (52%) ኮሎምቢያ ደግሞ (48%) ነበር።ጨዋታው እስከ ለሰባ ደቂቃዎች ያህል ያለ ግብ ቢጓዝም 71 ደቂቃ ላይ ማርቲኔዝ ከ ሀሜስ ሮድሪጌዝ የተላከለትን ኳስ ወደ ግብነት በመቀየር አሀዱ አለም ፥ ከዚያም መደበኛው የጨዋታ ክፈለ ጊዜ ሊገባደድ አራት ደቂቃዎች ሲቀሩት ዛፓታ አንድ ግብ አክሎ የካርሎስ ኪሮዧ ኮሎምቢያ ከመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ወሳኝ ሶስት ነጥቧን አግኝታለች።
ከጨዋታው በኋላ አርጀንቲና ሁል ጊዜ ድል ሲርቃት ትችቶች ሚዥጎደጎዱበት ሜሲ አሁንም እነዚያን ትችቶች ማስተናገዱን ቀጥሏል።ብዙዎች ግን ሜሲ ብቻውን ከቡድኑ ተነጥሎ መተቸት የለበትም እያሉ ነው።
(Goal)
No comments:
Post a Comment