ሰበር ዜና
[ይፋዊ] ማውሪዚዮ ሳሪ የጁቬንትስ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዘጋጅ እና አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)
ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ አንድ አመትን በቼልሲ ቤት ካሳለፉ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ጁቬንትስን በአሰልጣኝነት መያዛቸው ይፋ ሆኗል።
ሳሪ ወጣ ገባ በነበረው የስታንፎርድ ብሪጅ ቆይታቸው ዩሮፓ ሊግን ማሳካት የቻሉ ቢሆንም በተለይ ከአጨዋወታቸው ጋር ተያይዞ ሊጉን ለመላመድ ተቸግረው ነበር።ጣሊያናዊው ሰው በአመቱ ዩሮፓ ሊግን ከማሳካት በተጨማሪ ቼልሲ በቀጣዩ አመት ሻምፒዮንስ ሊግን እንዲሳተፍ ማድረግም ችሏል።
ሳሪ አሮጊቷም እስከ 2022 ለማሰልጠንም ተስማምተው የሶስት አመት ኮንትራት ፈርመዋል።ሊጉ ላይ ለአመታት የነገሰው ጁቬ ሻምፒዮንስ ሊጉን ከሳሪ አመራርነት ይቀዳጅ ይሆን? …… መልሱን ጊዜ ይፈታዋል
No comments:
Post a Comment