Sunday, June 16, 2019

"አዲስ ፈተና የምፈልግበት ትክክለኛው ጊዜ ነው" ፖግባ

"አዲስ ፈተና የምፈልግበት ትክክለኛው ጊዜ ነው" ፖግባ

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



ፈረንሳዊው የቀያይ ሰይጣኖቹ አማካይ ፖል ፖግባ በብዙ ፈተናዎች የተሞላ አመትን ካሳለፈ በኋላ ከኦልድ ትራፎርድ መውጫ በር ላይ የደረሰ ይመስላል።
ቁመተ መለሎው አማካይ ስሙ በስፋት ከዝውውር ጋር እየተያያዘ ባለበት በዚህ ጊዜም ጉዳዩ ላይ ቤኒዝል አርከፍክፎበታል።የ26 አመቱ አማካይ ይህንን ብሏል

"እኔ በማንቸስተር ዩናይትድ ባሰለፍኳቸው ሶስት አመታት ደስተኛ ነኝ።ጥሩም መጥፎም ጊዜያት ነበሩ ይህ ሁሌም ያጋጥማል።ከነዚህ አመታት በኋላም በዚህ አመት ባሳለፍኩት ሲዝንም በግሌ ምርጡ ጊዜዬ ነበር ……አሁን አዲስ ፈተና የምፈልግበት ትክክለኛው ጊዜ ይመስለኛል ፥ አዎ ስለ አዲስ ፈተና በማሰብ ላይ ነኝ።"





ፖግባ አመቱ ሲጀመር አንስቶ በጆዜ ሞሪንሆ ስር ደስተኛ ያልነበረ ሲሆን ከፖርቹጋላዊው ሰው ጋርም እሰጣ እገባ ውስጥ መግባቱ አይዘነጋም።ከዚያም ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ከተሾመ አንስቶ በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት አስደናቂ ጊዜን ቢያሳልፍም የኋላ ኋላ ግን አቋሙ ወርዷል።

ፖግባ ስሙ በስፋት ከሪያል ማድሪድ ፥ ባርሴሎና እና ጁቬንትስ ጋር በመያያዝ ላይ ነው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...