አዘጋጅ እና አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
በአቡዳቢ ከበርቴዎች ስር የሚገኘው እና በፋይናንት ጉምቱ የሆነው የፓሪሱ ክለብ በአለም የተጨዋቾች ሪከርድ ዋጋ ከባርሴሎና አዘዋውሮት የነበረውን ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማር በስተመጨረሻ ሊሸኘው በመሰናዳት ላይ ይገኛል።
ትልቁ የፈረንሳይ ሚዲያ L'Equipe እንደዘገበው ክለቡ ትክክለኛው ዋጋ ከቀረበለት በዚሁ በክረምቱ የዝውውር መስኮት 10 ቁጥር ለባሹን ኮከብ ለመሸጥ አይኑን አያሽም።
ብራዚላዊው ኮከብ ወደ ፈረንሳይ ከተጓዘ አንስቶ በተለይ በሊጉ ጥራት ደረጃ ማነስ እና በተለያዩ መሰል ጉዳዮች ደስተኛ አለመሆኑ ተስተውሏል ፥ ከተጨዋቾች ጋርም በተደጋጋሚ እሰጣ እገባ ውስጥ የቆየ ሲሆን ጉዳት ሳይደርስበት ተጎድቻለሁ በማለትም ወደ ሀገሩ ብራዚል ያለ በቂ ምክንያት እየተጓዘ ለክለቡ የበላይ አመራሮችም አስቸጋሮ ሆኖባቸው ነበር።
በዚህም ምክንያት የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በዚህ ሰዓት አይናቸውን የጣሉበት ሲሆን የቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና እና ተቀናቃኙ ሪያል ማድሪድ ደግሞ ጉዳዩን ከፊት ሆነው በአፅንኦት ይመለከቱታል።ሆኖም ፔዤ በትንሹ 2017 ላይ የከፈለውን €222ሚ. ይፈልጋል ነው የተባለው።
የፔዤው ፕሬዝዳንት ናስር አል-ኻላፊም ትናንት ባወጡት መግለጫ 'ታዋቂ ታዋቂ ፀባይ' የሚያራምዱ ሰዎችን አንታገሰም ማለታቸው ብዙዎች ኔይማርን መሆኑ ነው ሲሉ ተርጉመውታል።
ምንጭ - L'Equipe
No comments:
Post a Comment