Monday, June 17, 2019

የሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

የዕለተ ሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ ዜናዎች

የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70

እንደርታ መካከል የእርቀ ሠላም

ጉባዔ ተካሄደ

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኃይለየሱስ
ፍስሃ (ኢ/ር)፣ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ፕሬዝደንት ፍቃደ
ማሞ (መ/አለቃ)፣ የመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ፕሬዝደንት
ክንደያ ገብረሕይወት (ፕሮፌሰር) እና የደጋፊ ማኅበር
ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የዕርቀ ሠላም የውይይት
መድረኩ የተካሄደው።
ሰፊ ውይይት በሁለቱም ክለቦች መካከል ከተካሄደ በኃላ
የፊታችን ማክሰኞ በ10:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም
የሚካሄደው የቡና እና መቐለ ጨዋታ በፍፁም ስፖርታዊ
ጨዋነት እንዲጠናቀቅ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ባለ
ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባዔው
ተጠናቋል።
1ኛ. በስፖርታዊ ውድደር ጊዜ የሚንፀባረቁ ስፖርታዊ
ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች እና ባህርያትን ሁለቱም ክለቦች
ማውገዝ እና ማረም ሲገባቸው አለማድረጋቸው ክፍተቶች
እንዲበዙና አለመግባባቱ እንዲፈጠር ምክንያት መሆናቸውን
አምነው ተቀብለው ለማስተካከል መግባባት ላይ
ደርሰዋል።
2ኛ. ስፖርት የሠላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት መገለጫ
መሆን ሲገባው ከዚህ በተቃራኒ የተጓዘ በመሆኑ የክለባት
ደጋፊዎቻችን ፣ የስፖርት ማኅበረሰብ እንዲሁም ህዝብን
የሚያሳዝን ስለሆነ ሊታረም የሚገባው መሆኑን ከስምምነት
ደርሰናል።
3ኛ. ስፖርቱን ወዳልተገባ መንገድ እንዲሄድ የተለያዩ
አካላት እየተጠቀሙበት ስለሚገኝ ከዚህ ድርጊታቸው
እንዲታቀቡ አስፈላጊውን ስራ እንዲሰራ ሁለቱም ክለባት
ከስምምነት ደርሰዋል።
4ኛ. የፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 11 የሚካሄደው ጨዋታ
ሠላማዊ ሆኖ እንዲፈፀም የሁለቱም ክለባት ደጋፊዎች
ክለባቸውን በስፖርታዊ ጨዋነት ሠላማዊና ፣ በህጋዊ
መልኩ እንዲደግፉ ጥሪ ተደርጓል።
5ኛ የ. ደጋፊዎች ከሚነሱበት ስፍራ ጀምሮ ሠላማዊ ጉዞ
እንዲኖራቸው የሚመለከታቸው አካላትና ህዝቡ
አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ። ደጋፊዎችም ከፀጥታ
ኃይሎች ጋር በመተባበር ፍፁም ሠላማዊ ውድድር
እንዲሆን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
6ኛ. ለዚህም እንዲረዳ ከሁለቱም ክለባት 6 አባላት ያሉት
እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በመተባበር እንዲሰሩ ኃላፊነት ተሰጥቷል። በቀጣይነትም
የሁለቱም ክለባት አመራሮች ዘላቂ የሆነ ወንድማማችነት
እንዲኖር በጋራ ለመስራት ከውሳኔ ደርሰዋል።
በመጨረሻም የሁለቱም ክለባት አመራሮች እስካሁን
ለተፈጠረው አለመግባባት ለደጋፊው እና ለህዝቡ ይቅርታ
ጠይቀዋል። ዛሬ 07:00 ላይም በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል
ሁለቱም ክለቦች ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ ይሆናል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ድህረ ገፅ አስነብቧል።
ምንጭ- ሶከር ኢትዮጵያ




የባህር ማዶ ስፖርታዊ ዜናዎች

ማንቸስተር ዩናይትድ ፖል ፖግባን የሚለቅ ከሆነ በምትኩ ክሮሺያዊውን የ31 አመት አማካይ ኢቫን ራኪቲች እና የ26 አመቱን ብራዚላዊ አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ከባርሴሎና ማዘዋወር ይፈልጋል።ፖግባ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ኦልድ ትራፎርድን ይለቃል የሚለው ዜና በስፋት እየተነገረ ይገኛል።

(Mundo Deportivo - in Spanish)





እንግሊዛዊው የ33 አመት ተከላካይ ጋሪ ካሂል በቀድሞ አሰልጣኙ አንቶኒዮ ኮንቴ ኢንተር ሚላን ቤት ተፈልጓል።ኮንቴ አዲስ እየገነባ ላለው ቡድን አንጋፋውን ተከላካይ ለጥቂት ጊዜ ቆይታም ቢሆን ይፈልገዋል።

(Sport Mediaset - in Italian)





በሪያል ማድሪድ ቤት ያለው እህል ውሃ ያከተመ የሚመስለው ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል በበርካታ የአውሮፓ ጉምቱ ክለቦች እየተፈለገ ሲሆን የጀርመኑ ሀያል ክለብ ባየርን ሙኒክ ደግሞ በአንድ አመት የውሰት ውል ሊወስደው ይፈልጋል።

(Sun)





ቶተንሃም የሊዮኑን ፈረንሳዊ የ22 አመት አማካይ ታንጉይ ንዶምቤሌ ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።ይህ ዝውውር በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።

(Telefoot - in French)





ሊቨርፑል በዩዲኒዜ በጥብቅ በመፈለግ ላይ ያለውን የቤስኪታሹን ቱርካዊ አማካይ ዶሩካን ቶኮዝ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል።የጣሊያኑ ክለብ ዩዲኒዜ የተጨዋቹ የረዥም ጊዜ ፈላጊ ነው።

(Fotomac - in Turkish)





የማንቸስተር ሲቲው ታክቲሺያን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሪያል ቤቲሱን አንጋፋ ግብ ጠባቂ አሲየር ሬስጎ በማምጣት ሁለተኛ ግብ ጠባቂው ማድረግ ይፈልጋል።

(Sun)







በአቡዳቢ ከበርቴዎች ስር የሚገኘው እና በፋይናንት ጉምቱ የሆነው የፓሪሱ ክለብ በአለም የተጨዋቾች ሪከርድ ዋጋ ከባርሴሎና አዘዋውሮት የነበረውን ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማር በስተመጨረሻ ሊሸኘው በመሰናዳት ላይ ይገኛል። ትልቁ የፈረንሳይ ሚዲያ L'Equipe እንደዘገበው ክለቡ ትክክለኛው ዋጋ ከቀረበለት በዚሁ በክረምቱ የዝውውር መስኮት 10 ቁጥር ለባሹን ኮከብ ለመሸጥ አይኑን አያሽም።ብራዚላዊው ኮከብ ወደ ፈረንሳይ ከተጓዘ አንስቶ በተለይ በሊጉ ጥራት ደረጃ ማነስ እና በተለያዩ መሰል ጉዳዮች ደስተኛ አለመሆኑ ተስተውሏል ፥ ከተጨዋቾች ጋርም በተደጋጋሚ እሰጣ እገባ ውስጥ የቆየ ሲሆን ጉዳት ሳይደርስበት ተጎድቻለሁ በማለትም ወደ ሀገሩ ብራዚል ያለ በቂ ምክንያት እየተጓዘ ለክለቡ የበላይ አመራሮችም አስቸግሮ ሆኖባቸው ነበር።

በዚህም ምክንያት የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በዚህ ሰዓት አይናቸውን የጣሉበት ሲሆን የቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና እና ተቀናቃኙ ሪያል ማድሪድ ደግሞ ጉዳዩን ከፊት ሆነው በአፅንኦት ይመለከቱታል።ሆኖም ፔዤ በትንሹ 2017 ላይ የከፈለውን €222ሚ. ይፈልጋል ነው የተባለው።

የፔዤው ፕሬዝዳንት ናስር አል-ኻላፊም ትናንት ባወጡት መግለጫ 'ታዋቂ ታዋቂ ፀባይ' የሚያራምዱ ሰዎችን አንታገሰም ማለታቸው ብዙዎች ኔይማርን መሆኑ ነው ሲሉ ተርጉመውታል።

(L'Equipe)







ማውሩዚዮ ሳሪ በቼልሲ ቤት የነበራቸው ቆይታ በቁጥሮች እንዴት ይገለጻል

➲ሁለት ጊዜ ለፍፃሜ ጨዋታዎች ደርሰዋል።አንደኛው ዮሮፓ ሊግ ላይ ሲሆን በዚህም ዋንጫውን ማንሳት ችለዋል ፥ ሀለተኛው ደግሞ ካራባኦ ካፕ ላይ ሲሆን በማንቼስተር ሲቲ የሽንፈትን ፅዋ ቀምሰዋል።

➲በፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ሲሆን ከመሪው ማን ሲቲ በ26 ነጥብ አንሰው ነበር።

➲በአጠቃላይ በሁሉም የውድድር አይነቶች 63 ጨዋታዎች ላይ ሰማያዊዎቹን በአሰልጣኝነት መርተዋል።

➲የማሸነፍ ስሌታቸው በመቶኛ 61.9% ነበር።39 ጨዋታ አሸንፈዋል ፥ 13 አቻ ፥ 11 ሽንፈት

➲ቼልሲ በሳሪ ስር የመጀመሪያዎቹን 12 ጨዋታዎች አልተሸነፈም ነበር ፥ 5 ጨዋታዎችንም በተከታታይ ማሸነፍ ችሎ ነበር

➲በሁሉም የውድድር አይነቶች ቡድናቸው 112 ግቦችን ሲያስቆጥር 58 ተቆጥሮበታል

➲5 ለ 0 ትልቁ ያሸነፉበት ውጤት ሲሆን በፕሪሚየር ሊግ ሀደርስፊልድን በተመሳሳይ ዳይናሞ ኬይቭን በዩሮፓ ሊግ
6 ለ 0 ደግሞ ትልቁ ሽንፈታቸው ነበር በማንቸስተር ሲቲ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...