የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
28ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ነገ ቅዳሜ ቀጥለው ሲውሉ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ ፥
ባህር ዳር ከተማ [9:00] ወላይታ ድቻ
ስሑል ሽረ [9:00] ደደቢት
ሀዋሳ ከተማ [9:00] መከላከያ
ጅማ አባ ጅፋር [9:00] ኢትዮጵያ ቡና
አህጉራዊ ዜናዎች
የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል፡፡ከጊዜ ወደ ጊዜ በተመልካቾች ድርቅ እየተመታ ያለውን ውድድር ዘንድሮ የምታስተናግደው ግብፅ ነች።ለ32ተኛ ጊዜ የሚደረገው የአፍሪካውያን ትልቁ ውድድር ዛሬ በ5 ሰዓት ሲጀመር አስተናጋጇ ግብፅ ዚምባቡዌን ታስተናግዳለች።ሰባት ጊዜ የአህጉሩን ዋንጫ በማንሳት ቁንጮ የሆኑት ፈርዖኖቹ በውድድሩ እምብዛም ልምድ የሌላትን ዚምባቡዌ በቀላሉ እንደሚረቱ የብዙዎች ግምት ሆኗል።የባህር ማዶ ዜናዎች
የቀድሞ የሊቨርፑል ፥የቼልሲ ፥ የኤሲ ሚላን ፥የአትሌቶኮ ማድሪድ እና የስፔን ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የነበረው ፈርናንዶ ቶሬዝ በዛሬው ዕለት ከእግር ኳስ አለም በተጨዋችነት መለየቱን ይፋ አድርጓል።
የ35 አመቱ አጥቂ በአሁኑ ሰዓት በጃፓኑ ክለብ ሳጋን ሱ በመጫወት ላይ የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ድህረ ገፆቹ ነው ከእግር ኳስ መሰናበቱን ይፋ ያደረገው።
በሳምንቱም ከአልባሴቴ ጋር በነበረው ጨዋታ የመጀመሪያ ግቡን ለክለቡ ያስቆጠረ ሲሆን ፍራሽ አዳሾቹ ወደ ስፔን ላሊጋ እንዲያድጉም አድርጓል።
ከዚያም በስፔን ካሉ ታላላቅ አጥቂዎች ውስጥ አንዱ በመሆን ለአምስት ተከታታይ አመታት የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ ፥ ይህም ወደ ሊቨርፑል እንዲመጣ ምክንያት ሆነው።
አንፊልድ ከደረሰ ወዲያም የተጨዋችነት ህይወቱን አስደናቂ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ባልተጠበቀ ሁኔታ 2011 ላይ የዝውውር መስኮቱ ሊጠናቀቅ ሰዓታት ሲቀሩት ወደ ቼልሲ እስኪዘዋወር ድረስም ለቀያዮቹ በ142 ጨዋታዎች 81 ግቦችን ከመረብ አዋህዷል።
ቼልሲ ከገባ በኋላ ግን አጀማመሩ አላማረም ነበር።በ2010/11 የውድድር ዘመንም በመጀመሪያዎቹ 18 ጨዋታዎች አንድ ግብ ብቻ ነበር ያስቆጠረው።
በሰማያዊዎቹ ቤት በነበረው ቆይታ 2012 ላይ ኤፍ.ኤ ካፕ እና ሻምፒዮንስ ሊግን 2013 ላይም ዩሮፓ ሊግን አሳክቷል።
ከዚያም ስድስት ወራትን በጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ካሳለፈ በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ተመልሷል።2018 ላይም ወደ ጃፓን ከመሄዱ በፊት ከአትሌቲኮ ጋር ዩሮፓ ሊግን አሳክቷል።
በኢንተርናሽናል መድረክም ለሀገሩ ስፔን እጅግ ስኬታማ ጊዜን አሳልፏል።ሀገሩ 2008 እና 2012 በተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫን እንዲሁም 2010 ላይ የዓለም ዋንጫ ስታሳካ ከስኳዱ ወሳኝ ተጨዋቾች አንዱ ነበር።
ኤል ኒ ኖ በአንድ ወቅት የተከላካዮች ራስ ምታትም ነበር ፥ ያየነው እናውቀዋለን ……
(Sky Sports)
የሪያል ማድሪዱ ፈረንሳዊ ኮከብ ካሪም ቤንዜማ ከኔይማር ጋር የተነሳውን ፎቶ በኢንስታግራም ገፁ ላይ መልቀቁን ተከትሎ የብራዚላዊው ተጨዋች ስም ከሎስብላንኮዎቹ ጋር በስፋት መያያዝ ጀምሯል።ከፒ.ኤስ.ጂ ጋር መለያየቱ አይቀሬ የሚመስለው ኔይማር ከሁለቱ የስፔን ሀያላን ክለቦች አንዱን በቀጣዩ አመት ማረፊያው እንደሚያደርግ ይጠበቃል።የ35 አመቱ አጥቂ በአሁኑ ሰዓት በጃፓኑ ክለብ ሳጋን ሱ በመጫወት ላይ የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ድህረ ገፆቹ ነው ከእግር ኳስ መሰናበቱን ይፋ ያደረገው።
"አሁን ይፋ የማደርገው ለየት ያለ ነገር አለ።ከ18 አስደሳች አመታት በኋላ ፥ ከእግር ኳስ ጋር የምለያይበት ትክክለኛው ጊዜ ነው።በቀጣዩ እሁድ በቶክዮ ስለ ዝርዝሩ ጋዜጣዊ መግለጫ የምሰጥ ይሆናል ፥ እዛው እንገናኝ" በማለት ነው የፃፈው።
ቶሬዝ የጃፓኑን ክለብ የተቀላቀለው 2018 ላይ የልጅነት ክለቡን አትሌቲኮ ማድሪድ ከለቀቀ በኋላ ነው።32 ግቦችንም ለኤዥያው ክለብ አስቆጥሮ ነበር።
ድንቁ አጥቂ ኤል ኒኖ የእግር ኳስ ህይወቱን የመጀመሪያ ጨዋታ አሀዱ ያለው 2001 ላይ በሁለተኛው ዲቪዥን የአትሌቲኮ ማድሪድን ማሊያ በመልበስ ከሌጋኔስ ጋር ነበር።በሳምንቱም ከአልባሴቴ ጋር በነበረው ጨዋታ የመጀመሪያ ግቡን ለክለቡ ያስቆጠረ ሲሆን ፍራሽ አዳሾቹ ወደ ስፔን ላሊጋ እንዲያድጉም አድርጓል።
ከዚያም በስፔን ካሉ ታላላቅ አጥቂዎች ውስጥ አንዱ በመሆን ለአምስት ተከታታይ አመታት የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ ፥ ይህም ወደ ሊቨርፑል እንዲመጣ ምክንያት ሆነው።
አንፊልድ ከደረሰ ወዲያም የተጨዋችነት ህይወቱን አስደናቂ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ባልተጠበቀ ሁኔታ 2011 ላይ የዝውውር መስኮቱ ሊጠናቀቅ ሰዓታት ሲቀሩት ወደ ቼልሲ እስኪዘዋወር ድረስም ለቀያዮቹ በ142 ጨዋታዎች 81 ግቦችን ከመረብ አዋህዷል።
ቼልሲ ከገባ በኋላ ግን አጀማመሩ አላማረም ነበር።በ2010/11 የውድድር ዘመንም በመጀመሪያዎቹ 18 ጨዋታዎች አንድ ግብ ብቻ ነበር ያስቆጠረው።
በሰማያዊዎቹ ቤት በነበረው ቆይታ 2012 ላይ ኤፍ.ኤ ካፕ እና ሻምፒዮንስ ሊግን 2013 ላይም ዩሮፓ ሊግን አሳክቷል።
ከዚያም ስድስት ወራትን በጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ካሳለፈ በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ተመልሷል።2018 ላይም ወደ ጃፓን ከመሄዱ በፊት ከአትሌቲኮ ጋር ዩሮፓ ሊግን አሳክቷል።
በኢንተርናሽናል መድረክም ለሀገሩ ስፔን እጅግ ስኬታማ ጊዜን አሳልፏል።ሀገሩ 2008 እና 2012 በተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫን እንዲሁም 2010 ላይ የዓለም ዋንጫ ስታሳካ ከስኳዱ ወሳኝ ተጨዋቾች አንዱ ነበር።
ኤል ኒ ኖ በአንድ ወቅት የተከላካዮች ራስ ምታትም ነበር ፥ ያየነው እናውቀዋለን ……
(Sky Sports)
(Goal)
አሌክሳንደር ላካዜት እና ሳሙኤል ኡምቲቲ ትናንት በአሜሪካ ለበዓል አብረው ሲዝናኑ ታይተዋል።ስሙ በስፋት ከአርሰናል ጋር ሲያያዝ የቆየው ፈረንሳዊው የባርሴሎና ተከላካይ ኡምቲቲ ወደ ኤምሬትስ ሊሄድ እንደሚችል ፍንጭ ነውም ተብሏል።
(Goal)
የቀድሞው የቼልሲ ግብ ጠባቂ ፔትር ቼክ ዛሬ የቼልሲ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሆኖ ተሹሟል፡፡ቼክ በዩሮፓ ሊግ አርሰናል በ ቼልሲ ከተሸነፈበት ጨዋታ በኋላ ጓንት መስቀሉን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡እናም ከተጨዋችነት በኋላ በሌላ ሀላፊነት ሰማያዊዎቹን የተቀላቀለ ሲሆን ፍራንክ ላምፓርድም በቅርቡ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ እንደሚሾም ይጠበቃል።
(Mirror)
ማን ዩናይትድ እና ቼልሲ ዋነኛ ፈላጊዎቹ ቢሆኑም ፌሊፔ ኩቲንሆ ወደ ሊቨርፑል ሊመለስ እንደሚችል Le 10 Sport አስነብቧል።18 እምብዛም አመርቂ ያልሆኑ ወራትን በካምፕ ኑ ያሳለፈው ብራዚላዊ ኢንተርናሽናል ወደ አንፊልድ በድንገት ሊመለስ የሚችልበት ዕድል አለ ብሏል ጋዜጣው።
(Le 10 Sport)
ኦሊጉናር ሶልሻየር ፖግባ ከክለቡ እንዲለቅ ይፈልጋል ሲል Daily Star አስነብቧል።ኖርዌያዊው አሰልጣኝ ከቀያይ ሰይጣኖቹ ለዝውውር የተመደበለት ገንዘብ £100M ብቻ በመሆኑ ነው ፖግባን በመሸጥ ተጨዋሪ ገንዘብ በመጨመር አዳዲስ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ያቀደው።ሮሜሮ ሉካኩም ቲያትር ኦፍ ድሪምስ መውጫ በር ላይ የቆመ ሁለተኛው ተጨዋች ነው።
(Daily Star )
አትሌቲኮ ማድሪድ ፖርቱጋላዊውን የ19 አመት ድንቅ አማካይ ጆዋዎ ፌሊክስ በ€120M ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።በቤኔፊካ ድንቅ አመትን ያሳለፈው ፌሊክስ በማን ዩናይትድም በጥብቅ ይፈለጋል።
(Evening Standard)
የባርሴሎናው ፕሬዝደንት ባርቶሚዮ ስሙ በስፋት ከሊቨርፑል ጋር በመያያዝ ላይ ያለው ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ኦስማን ዴምቤሌ በባርሴሎና እንደሚቆይ ተናግረዋል።
(Mirror)
it just rumors...
ReplyDelete