Thursday, June 20, 2019

የሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

የሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ሊዮን የ20 አመቱን አማካይ ጂያን ሉካስ ከብራዚሉ ክለብ  ፍላሚንጎ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።የተከላካይ አማካዩ የሊግ ዋኑን ክለብ የሚቀላቀለው በ€8M ሲሆን በቀጣዩ ሰኞ ፈረንሳይ ተጉዞ የህክምና ምርመራውን የሚያደርግ ይሆናል።
(Globoesporte)




ወደ 'ካላክቲኮስ' አስተሳሰባቸው የተመለሱት የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝደንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ኪልያን ምባፔን በ2020 ወደ በርናቢዮ ለማምጣት ካሁኑ ወጥነዋል።
ሎስብላንኮዎቹ ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል በፓሪሱ ክለብ ተጨማሪ ኮንትራት እንደማይፈርም ተስፋ አድርገዋል ፥ አሁን እስከ 2023 የሚያቆይ ኮንትራት ነው ያለው።ማድሪድ ለተጨዋቹ €15M አመታዊ ደሞዝም አሰናድቶለታል።
(AS)






ዴክላን ራይስ አሁን ወደ ማን ዩናይትድ የመሄጃ ትክክለኛው ጊዜ ነው ብሎ አያስብም።እንግሊዛዊው የዌስት ሀም አማካይ በቀያይ ሰይጣኖቹ በጥብቅ ከሚፈለጉት ተጨዋቾች ውስጥ ነው።
(Daily Star)






በተደጋጋሚ እየተነገረ ያለው የዋን ቢሳካ እና የማን ዩናይትድ ጉዳይ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።ቀያይ ሰይጣኖቹ ዝውውሩን ለመጨረስ £60M ለክሪስታል ፓላስ አቅርበዋል።እንግሊዛዊው የ21 አመት ፉል ባክ በዚህ ዋጋ የሚዘዋወር ከሆነ በቦታው የተጨዋቾች ሪከርድ ዋጋ ይሆናል።
(Daily Mail)






ኬይለር ናቫስ ወደ ፖርቱጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ለማምራት ተቃርቧል።ኮስታሪካዊው ኢንተርናሽናል በሪያል ማድሪድ ቤት ኩርቶዋ ከመጣ አንስቶ የቋሚ ተሰላፊነት ዕድልን ማጣቱን ተከትሎ በዚህ የዝውውር መስኮት በርናቢዮን መልቀቁ አይቀሬ ነው።
(A Bola)






ኡናይ ኤምሬ ሉካስ ቫስኩዌዝን ወደ ኤምሬትስ ማዘዋወር የዚህ የዝውውር መስኮት ዋነኛ ውጥናቸው ነው።
ቫስኩዌዝ የኤድን ሀዛርድን ዝውውር አስከትሎ በሪያል ማድሪድ ቤት የሚኖረው እህል ውሃ ያበቃ ይመስላል።ስፓኒያርዱ ተጨዋች ከአርሰናል በተጨማሪ በጣሊያኖቹ ሮማ እና ኢንተር ሚላን በጥብቅ ይፈለጋል።
(Don Balon)





ቶተንሃም የስፖርቲንግ ሊዝበኑን የ24 አመት አማካይ ለማዘዋወር ከልጁ ወኪል ጋር ተነጋግሩል።ተጨዋቹ ከስፐርስ በተጨማሪ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(The Telegraph)






ሪያል ማድሪድ ከአካዳሚው አንስቶ ያሳደገውን ማርኮስ ሊዮሬንቴን በ€40M ለከተማ ተቀናቃኙ አትሌቲኮ ማድሪድ ሸጦታል።ብዙ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ሊዮሬንቴ በመሸጡ የማድሪድ ደጋፊዎች በማህበራዊ ድህረ ገፆች ዚዳን ላይ የትችት ናዳ እያወረዱበት ነው።
(Official Real Madrid)





ሊቨርፑል ኦስማን ዴምቤሌን ወደ አንፊልድ ለማስኮብለል €150M አሰናድቷል።ዠርደን ክሎፕ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ያሳኩበትን ቡድናቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ፈረንሳዊውን ኢንተርናሽናል በጥብቅ ይሹታል ነው የተባለው።
(Don Balon)






ሮሜሮ ሉካኩ በስተመጨረሻ ወደ ኢንተር ሚላን ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።ቤልጄሚያዊው ኢንተርናሽናል በጣሊያኑ ክለብ በሳምንት  £180,000  የሚከፈለው ሲሆን ለዝውውሩ ኢንተር €75M ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
(The Sun )

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...