አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መርሃ ግብርቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011
ባህር ዳር ከተማ [9:00] ወላይታ ድቻ
ስሑል ሽረ [9:00] ደደቢት
ሀዋሳ ከተማ [9:00] መከላከያ
ጅማ አባ ጅፋር [9:00] ኢትዮጵያ ቡና
እሁድ ሰኔ 16 ቀን 2011
መቐለ 70 እ. [9:00] ደቡብ ፖሊስ
አዳማ ከተማ [9:00] ፋሲል ከነማ
ሲዳማ ቡና [9:00] ድሬዳዋ ከተማ
ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2011
ቅዱስ ጊዮርጊስ [11:00] ወልዋሎ ዓ/ዩ
ምንጭ- ሶከር ኢትዮጵያ
የባህር ማዶ ዜናዎች
ጁቬንትስ በበርካታ ክለቦች የሚፈለገውን የአያክሱን ድንቅ ተከላካይ ማቲያስ ደ ላይት ለማዘዋወር €70M ተቅርቧል፥ አሮጊቷ ለኔዘርላንዳዊው ተጨዋች የአምስት አመት ኮንትራትም አቅርባለች።ጁቬ ለተጨዋቹ አመታዊ €15m-€20m ለመክፈልም ነው ወጥና እየሰራች ያለችው።
(De Telegraaf)
ማንቸስተር ሲቲ ሮድሪን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ማስፈረም የሚችል ከሆነ ፋቢያን ዴልፍን ከክለቡ ለማሰናበት አስቧል።
ሮድሪ ወደ ኤቲሀድ የሚመጣ ከሆነ በቦታው ኬቨን ደብሮይነ ፥ ኢኻይ ጉንዶጋን እና ፊል ፎድን ስለሚኖሩ የዴልፍ አስፈላጊነት እምብዛም ነው።የ12 ወራት ኮንትራት ብቻ የውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት የቀረው እንግሊዛዊ አማካይ ወደ ቱርኩ ጋላታሳራይ እንደሚሄድም ይጠበቃል።
(Daily Mail)
ሪያል ማድሪድ ከኔይማር ዝውውር እጁን አውጥቷል።
ሪያል ማድሪድ ከኔይማር ዝውውር ጋር ደጋፊዎቹ ባላቸው አሉታዊ ምልከታ እና ተጨዋቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሜዳ ውጪ ባለው ጥሩ ያልሆነ ስም ምክንያት ከዝውውሩ እጁ አውጥቷል ሲል ለክለቡ ቅርብ የሆነው ጋዜጣ AS አስነብቧል።
የፍሎረንቲና ፔሬዝ አስተዳደር ለደጋፊዎቹ በኔይማር ዙሪያ ባዘጋጀው መጠይቅም የሎስብላንኮዎቹ አብዛኛዎቹ ደጋፊዎች ተጨዋቹ ወደ በርናቢዮ እንዲመጣ እንደማይፈልጉ አሳውቀዋል።
(AS)
ዋን ቢሳካን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ለማምጣት እየባዘኑ ያሉት ማን ዩናይትዶች አሁን ደግሞ ለክለቡ ክሪስታል ፓላስ €55M አቅርበዋል።የ21 አመቱ እንግሊዛዊ ኢንተርናሽናል በኦሊ ጉናር ሶልሻየር በጥብቅ ከሚፈለጉ ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ከገባ ውሎ ቢያድርም እስካሁን ግን ቲያትር ኦፍ ድሪምስ መክተም አልቻለም።
(Mirror)
ከጣሊያን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አሁን ባለው ሁኔታ ጁቬንትስ ፖል ፖግባን ለማዘዋወር ያለውን ውድድር ከፊት እየመራ ነው ማለት ይቻላል።አስቸጋሪ አመታትን በኦልድ ትራፎርድ ያሳለፈው ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል በሪያል ማድሪድም በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወቃል።
(Mirror)
ከባለፉት አመታት ዘንድሮ ጠንካራ የተከላካይ መስመር ያሳየው ሊቨርፑል በዝውውር መስኮቱ ኩሊባሊን ከናፖሊ በማስፈረም ለቀጣዩ ሲዝን ከቨርጅል ቫን ዳይክ ጋር ለማጣመር አቅዷል።ሊቨርፑል የ28 አመቱን ጠንካራ ተከላካይ ከኔፕልሱ ክለብ የሚያዘዋውር ከሆነ ይበልጥ እንደሚጠነክር ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡
(Mirror)
የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዠርደን ክሎፕ ክለባቸው በዚህ የዝውውር መስኮት ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያወጣ ተናገሩ።ዘንድሮ ስኬታማ ሲዝንን ያሳለፉት ክሎፕ
" ሊቨርፑል ውጥረት ውስጥ ያለ ክለብ ነው ፥ እናም እንደ ተቃራኒዎቻችን በርካታ ገንዘብ ለተጨዋቾች ማውጣት ካልቻልን መፎካከር ከባድ ነው።ሁሉም ክለቦች ዝውውሩ ላይ ተሳታፊ ናቸው እኛም እንዲሁ" በማለት ነው የተናገሩት።
(Mirror)
አሮን ራምሴ፥ዳኒ ዌልቤክ፥ዴኒዝ ሱዋሬዝ፥ፔትር ቼክ፥ዳቪድ ኦስፒናን እና ሌችስታይነርን የለቀቀው አርሰናል ለነዚህ ተጨዋቾች ያወጣው የነበረውን ሳምንታዊ £400,000 በተጨዋቾቹ መልቀቅ ብቻ ይቆጥባል ተብሏል።
(The Sun)
አርሰናል ለኬረን ቴርኒ £15M አቅርቦ በሴልቲክ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ £25M አቅርቧል።መድፈኞቹ በዚህ ክረምት ውሉ የሚጠናቀቀውን ናቾ ሞንሪያልን ተክቶላቸው ቴርኒ እንዲጫወት ይፈልጋሉ።የስኮትላንዱ ክለብ እስከ 2023 ኮንትራት ያለውን የ22 አመቱን የግራ መስመር ተከላካይ በተቻለ መጠን በክለቡ ማቆየት ይፈልጋል።
(Mirror)
No comments:
Post a Comment