አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራት ጨዋታዎች ሲደረጉ በርካታ ግቦች ከመረብ አርፈዋል
መሉ ውጤቶች……
ሀዋሳ ከተማ 5-1 መከላከያ
ጅማ አባ ጅፋር 1-2 ኢትዮጵያ ቡና
ስሑል ሽረ 5-0 ደደቢት
ባህር ዳር ከተማ 1-1 ወላይታ ድቻ
ምንጭ-ሶከር ኢትዮጵያ ድህረ ገፅ
መሉ ውጤቶች……
ሀዋሳ ከተማ 5-1 መከላከያ
ጅማ አባ ጅፋር 1-2 ኢትዮጵያ ቡና
ስሑል ሽረ 5-0 ደደቢት
ባህር ዳር ከተማ 1-1 ወላይታ ድቻ
ምንጭ-ሶከር ኢትዮጵያ ድህረ ገፅ
የዝውውር ዜናዎች
ማን ዩናይትዶች ለግብ ጠባቂያቸው ዴቪድ ዴሄያ አዲስ ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።ቀያይ ሰይጣኖቹ ለስፓኑያርዱ የግብ ዘብ የአምስት አመት ኮንትራት እና ሳምንታዊ £350,000 ደሞዝ አሰናድተውለታል።ዴሄያ ግን ወደ ሀገሩ ክለብ ሪያል ማድሪድ የመሄድ ዕቅድ አለው።
(Sun)
ሪያል ማድሪዶች የ26 አመቱን ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል ፖል ፖግባ ከኦልድ ትራፎርድ ወደ በርናቢዮ ማምጣት የዚህ የዝውውር መስኮት ዋነኛ ዕቅዳቸው ነው።ይህ የማይሳካ ከሆነ የቶተንሃሙን ክርስቲያን ኤሪክሰን እንደአማራጭ ለማዘዋወር ይሻሉ።
(Goal)
የማን ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ከፍተኛ ገንዘብ ላቀረበው ክለብ ፖል ፖግባ እንዲሸጥ ለቀያይ ሰይጣኖቹ የበላይ አካላት መልዕክቱን አስተላልፏል።አሁን ባለው ሁኔታ ፖግባ ወደ ጁቬንትስ የመሄድ ዕድሉ ሰፊ ነው።
(Star)
ቶተንሃም ክርስቲያን ኤሪክሰንን ለማድሪድ የሚሸጥ ከሆነ ከሎስብላንኮዎቹ ከገንዘብ በተጨማሪ ስፓኒያርዱ የ22 አመት ዊንገር ማርኮ አሴንሲዮ የዝውውሩ አካል እንዲሆን ይፈልጋል።
(Sun)
ኢንተር ሚላን የ26 አመቱን ቤልጄሚያዊ የማን ዩናይትድ አጥቂ ሮሜሮ ሉካኩ ወደ ሳንሴሮ ለማምጣት በቃል ደረጃ ከስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ከዛ በፊት ግን ወጪውን ለማካካስ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ መሸጥ ይሻል።
(Guardian)
ጁቬንትስ ኬረን ትሪፒየን ለማዘዋወር ከቶተንሃም ጋር ድርድር እያደረገ ሲሆን ስፐርስ ለእንግሊዛዊው የ28 አመት የቀኝ መስመር ተከላካይ £25M የሚቀርብላት ከሆነ ተጨዋቹን ወደ ቱሪን ለመሸኘት ዝግጁ ናት።
(Telegraph)
ዌስት ሀም፥ዋት ፎርድ እና ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው ሼፍልድ ዩናይትድ ቶጓዊውን የቀድሞ የአርሰናል አጥቂ ኢማኑኤል አዲባዮር ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ናቸው።የ35 አመቱ አንጋፋ አጥቂ አሁን በየትኛውም ክለብ ኮንትራት ስለሌለው በነፃ ነው ዝውውሩ የሚፈፀመው፡፡
(Sun)
ፓሪሰን ዤርመን ለባርሴሎና ብራዚላዊው የ27 አመት አጥቂ ኔይማር በየትኛውም ዋጋ የማይሸጥ እና ለድርድር የማይቀርብበት ተጨዋች መሆኑን አሳውቆታል።
(Mail)
አትሌቲኮ ማድሪድ ስፓኒያርዱን የአርሰናል የቀኝ መስመር ተከላካይ ሄክቶር ቤለሪን ለማዘዋወር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን መድፈኞቹ ከተስማሙ የ29 አመቱን ዊንገር ቪቶሎ ሊሰጣቸውም ዝግጁ ነው።
(Telegraph)
ቼልሲ የቀድሞው ተጨዋቹ ፍራንክ ላምፓርድ በደርቢ ካውንቲ በኮንትራት ውስጥ ስላለ ለሻምፒየን ሺፑ ክለብ £4M በካሳ መልክ ለመክፈል ጥያቄ አቅርቧል።ላምፓርድ በቀጣዩ ሳምንት የቼልሲ አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙ ይፋ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል።
(ESPN)
No comments:
Post a Comment