Friday, June 7, 2019

ኤድን ሀዛርድ ሪያል ማድሪድን ተቀላቀለ

[ይፋዊ] ኤድን ሀዛርድ በ€100ሚ. ሪያል ማድሪድን ተቀላቀለ


ቤልጄሚያዊው ኮከብ ሰባት አመታትን በስታንፎርድ ብሪጅ ካሳለፈ በኋላ በስተመጨረሻ ሳንቲያጎ በርናቢዮ ከትሟል።
ሀዛርድ ወደ ነጫጮቹ ቤት የተጓዘው በ€100ሚ. ሲሆን እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራት መፈራረሙን ሪያል ማድሪድ ይፋ አድርጓል።ክለቡ ሀዛርድ ከአምስት ቀናት በኋላ ከደጋፊዎች ጋር ትውውቅ እንደሚያደርግም አሳውቋል።
የሎስብላንኮዎቹ ወኪል ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ለንደን ተጉዞ ከቼልሲዋ ዳይሬክተር ማሪና ግራኖቪስካያ ጋር ሰፊ ድርድር ካደረገ በኋላ ነው ዝውውሩ እውን የሆነው።
የ28 አመቱ ቤልጄሚያዊ በተደጋጋሚ ለማድሪድ መጫወት ትልቁ  ህልሙ መሆኑን መናገሩ ይታወሳል።በተለይ ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ ዚነዲን ዚዳንን እያደነቀ እንዳደገም በአንድ ወቅት በሰፊው ሀተታ ሰጥቶ ነበር።



ኤድን ሀዛርድ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ መውጣት በኋላ በእጅጉ የተዳከመውን የነጮቹን ቤት የአጥቂ መስመር ያጠነክራል ተብሎም እየተነገረ ይገኛል።የማድሪድ ደጋፊዎችም በተጨዋቹ ዝውውር ደስተኛ መሆናቸው እየገለፁ ይገኛል።

በአብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ) የቀረበ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...