Saturday, June 15, 2019

አርጀንቲና ከ ኮሎምቢያ ዛሬ በኮፓ አሜሪካ ይፋለማሉ

አርጀንቲና ከ ኮሎምቢያ ዛሬ በኮፓ አሜሪካ ይፋለማሉ


አዘጋጅ እና አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)


አለማችን ላይ ካሉ የሀገራት ውድድሮች በጥራት እና ኮከብ ተጨዋቾችን በማሳየት ከግንባር ቀደሞቹ የሆነው የላቲን አሜሪካ ሀገራት ውድድር የሆነው ኮፓ አሜሪካ ትናንት በብራዚል አስተናጋጅነት ተጀምሯል።በመክፈቻ ጨዋታም ብራዚል ቦሊቪያን 3 ለ 0 አሸንፋለች።

ውድድሩ ዛሬ ሲቀጥል ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።ቬንዝዌላ ከ ፔሩ የመጀመሪያው ነው ሲሆን ሀለተኛው እና ተጠባቂው ጨዋታ በምድብ ሁለት አርጀንቲና ከ ኮሎምቢያ የሚያደርጉት ነው።በአርጀንቲና በኩል ሊዮኔል ሜሲ የሚጠበቅ ሲሆን በኮሎምቢያ በኩል ደግሞ ሀሜስ ሮድሪጌዝ አይን የተጣለበት ተጨዋች ነው።


አርጀንቲና - የዘንድሮ አርጀንቲና በስኳድ ደረጃ ለየት ያለ ነው።ለዓመታት የምናውቃቸው የነበሩት እና የለመድናቸው ፊቶች ሀቪየር ማሼራኖ እና ኤንዞ ፔሬዝን ጭምር ዘንድሮ አንመለከትም።አማካይ ተጨዋቾች ላይ መሰረት ያደረገ ቡድንም ነው ዘንድሮ የሚመስለው።ጂዮቫኒ ሎ ሴልሶ እና ሌንድሮ ፓራዴዝ ስፍራውን ይመሩታል።በአጥቂ በኩልም ሊዮኔል ሜሲ እና አጉዌሮ ከፍተኛ ሀላፊነት የተጣለባቸው ሲሆን ከፓውሎ ዲባላ ጋር እንደሚጣመሩም ነው የሚጠበቀው።የዚህ በድን ክፍተት ተብሎ የሚታሰበው የተከላካይ ክፍሉ ነው።
ዕድሜው ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ እየተጠጋ የሚገኘው ሊዮ ሜሲ ለሀገሩ ዋንጫን አላስገኘም በሚል እንደሚተች ይታወቃል ፥ እናም ብዙዎች ይሄ ኮፓ አሜሪካ የመጨረሻ ዕድሉ ነው እያሉ ነው።



ኮሎምቢያ - ኮሎምቢያ በጣም ጠጣር የሆነ ቡድን ነው ፥ በጣም ጠንካራ የሚባል የተከላካይ መስመርም አለው።በቁመተ መለሎው ዬሪ ሚና እና ዳቪንሰን ሳንቼዝ ይመራል።የላቲን አሜሪካ እግር ኳስ በአብዝሃኛው ጉልበት ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ ሁለቱ ተጨዋቾች ለአጨዋወቱ አመቺ ናቸው።እዚህ ቡድን ውስጥ ከፍተኛው ሀላፊነው የተጫነበት አንበሉ እና አንጋፋው የ 33 አመት አጥቂ ራዳሚን ፋልካኦ ላይ ነው።ለሀገሩ በትልቅ ደረጃ የሚያደርገው የመጨረሻ ቶርናመንት እንደሚሆንም ይታሰባል።ሀሜስ ሮድሪጌዝም ለዚህ ቡድን ተገን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።
ይህ ቡድን አማካይ ላይም ጉልበትን ከ ችሎታ ጋር ያጣመሩ ባላተሰጥኦ ተጨዋቾች አሉት ፥ ይህ ቡድን ለዋንጫ ከታጩትም ውስጥ ነው።

ጨዋታው ከለሌቱ 7 ሰዓት ይደረጋል!

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...