Friday, June 14, 2019
የዕለተ ቅዳሜ ስፖርታዊ ወሬዎች
═════════════════════════
ሊቨርፑል በዚህ አመት በጀርመን ቡንደስሊጋ ለአርቢላይፕዚክ 16 ግቦችን
ያስቆጠረውን የ 23 አመቱን ጀርመናዊ አጥቂ ለማስፈረም እየመሩ ይገኛሉ
ባየርሙኒክ ፊቱን ወደ ማንችስተር ሲቲ ሊሮይ ሳኔ ማዞሩን ተከትሎ ተጫዋቹ ላይ
ያለውን ፍላጎት ማቀዝቀዙን ተከትሎ።የዝውውር ገንዘቡም £50m ተተምኑዋል።
(mirror)
═════════════════════════
አርሰናል ለጋቦናዊው አጥቂያቸው ፔርኤሜሪክ ኦበሚያንግ ከቻይና ክለብ
£300,000- ሳምንታዊ ደሞዝ መቅረቡን ተከትሎ መድፈኞቹ ከኦበሚያንግ ጋር
አዲስ ኮንትራት በሚፈርምበት ዙሪያ ለመደራደር አየተመለከቱ ይገኛሉ።
(mirror)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ የከተማ ተቀናቃኙን ማንችስተር ሲቲን በአንግሊዛዊው
ተከላካይ ሀሪ ማጉዌር ዝውውር እንደሚረታ ተማምኑዋል።እናት ክለቡ ሌስተር
ሲቲም ከተጫዋቹ ዝውውር £80m ገደማ ይፈልጋሉ ነገር ግን ሲቲ ለተጫዋቹ ከ
£50m የመክፈል ፍላጎት የለውም።በዚህም ቀያይ ሴጣኖቹ በቀጣዩ ሳምንት
ቀበሮዎቹ ያሉትን ሙሉ ለሙሉ መክፈል ባይችሉም የተጠጋጋ ገንዘብ በመክፈል
ዝውውሩን እንደሚጨርሱት ተማምነዋል። (mirror)
═════════════════════════
በዚህ አመት በፈረንሳይ ሊግ 1 ለፓሪሴንዤርመን 24 ጫወታዎችን ያደረገው
ፈረንሳያዊው የ 19 አመት ተከላካይ ሙሳ ዲያቢ ወደ ጀርመኑ ክለብ
ባየርሊቨርኩሰን መዘዋወሩ ተረጋግጧል።የፈረንሳዩ ከበርቴ ቡድንም
ለተጫዋቻቸው መልካሙን ሁሉ እንደሚመኙ በቲውተራቸው ገልፀዋል።
═════════════════════════
በ 2017 ከቶተንሀም ሆስፐር በ £50m የተዘዋወረው እንግሊዛዊው የ 29
አመት የመስመር ተከላካይ ካየል ወከር በኢትሀድ የ 3 አመት ቀሪ ኮንትራት
ቢኖረውም ለተጨማሪ ሁለት አመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈረም
ተዘጋጅቱዋል።(Manchester Evening News)
═════════════════════════
የቀድሞ የጁቬንቱስ እና የአሁኑ የዌስትሀም ተከላካይ አንጌሎ ኦግቦና
በድጋሚ ወደ ጣልያን ለመመለስ የቦሎኛ ኢላማ ሆኑዋል።Il Resto del
Carlino
.═════════════════════════
ፓሪሴንዤርመን ጣልያናዊውን የናፖሊ የፊት መስመር ሆነውን ሎሬንዞ
ኢንሴኚን ለማስፈረም ለኔፕልሱ ቡድን ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።በዚህ
ደረጃ እስካሁን ፒኤስጂ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረበም ነገር ግን በቀጣዩ
ሳምንት ከተጫዋቹ እና ከወኪሉ ጋር ንግግር ለማድረግ አስበዋል።(Gazzetta
dello Sport)
═════════════════════════
በዚህ ክረምት ከፓሪሴንዤርመን ጋር በነፃ የተለያየው ፈረንሳያዊው አማካይ
አድሪያን ራቢዮት በይፋ ከጁቬንቱስ ጋር እየተወያየ ነው።እንደወኪል አክት
እያደረገች ያለችው እናቱ ለCorriere dello Sport and Tuttosport
ጁቬንቱስ ማለት ትልቅ ክለብ ነው ማንኛው ተጫዋች ሊጫወትበት
የሚፈልግበት በማለት አስተያየት ሰተዋል በጣልያን ኤርኮል ሪዞርት
በመሆን።በተጨማሪም እየተነጋገራችሁ ነው ሚባለው ዜናም እውነት ነው
ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አዎ እውነት ነው በማለት አረጋግጠዋል።
═════════════════════════
እንደ German magazine Kicker ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ በዚህ ክረምት
ከባየርሙኒክ ጋር ከበርካታ አመታት ቡኃላ የተለያየው ፈረንሳያዊው የክንፍ
መስመር ተጫዋች ፍራንክ ሪቤሪ በአስገራሚ ሁኔታ ስሙ ዘንድሮ ወደ
ፕሪምየርሊጉ ካደገው ሼፊልድ ዩናይትድ ጋር ተያይዞ ተነስቷል።
═════════════════════════
አርሰናሎች ፈረንሳዊውን ለመሃል ተከላካይ ሎረንት ኮሴልኒን የ£10.6m
ሂሳብ ከቀረበላቸው ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል።ተከላካዩም በፍላይ ኤሜሬት
የሚያቆየው የ 1 አመት ቀሪ ኮንትራት ብቻ ነው የሚቀረው።(Source: Daily
Star)
:
ቦሩሲያ ዶርትመንድ፣ ባየር ሌቨርኩሰን፣ ኤሲ ሚላን እና ሞናኮዎች በዚህ
ክረምት ኮሽሌይኒን ለማዛወር ፍላጎት ያሳዩ ክለቦች ሲሆኑ፤ 40ሚ.ፓ ብቻ
የዝውውር ባጀት ያላቸው ኡናይ ኤምሬ ተጭዋቹን በመልቀቅ ተጨማሪ
የዝውውር ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ሊለቁት ፍቃደኛ ሆነዋል። (Source: BILD)
═════════════════════════
ባርሴሎና የሬያል ቤቲሱን ግብ ጠባቂ ፓው ሎፔዝን ለማስፈረም ከሮማ
ፉኩኩር ገጥሞታል።የስፔን ሶስተኛው ግብ ጠባቂ የውል ማፍረሻውም £30m
ገደማ ነው።Sport.
═════════════════════════
እንደሆላንዱ De Telegraaf ከሆነ የበርካታ የአውሮፓ ክለቦችን ቀልብ
የሳበው ማቲያ ዴሊት ቤተሰቦች በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪሲ ቤት እየፈለገ
እንደሆነ ተነግሩዋል ይህ ደግሞ የ 19 አመቱ ተከላካይ ወደ ፓሪሴንዤርመን
እንደሚዘዋወር ፍንጭ ነው ተብሏል።
═════════════════════════
በ 2016 ከስድስት ሲዝን ቆይታ ቡኃላ ከስታምፎርድ ብሪጅ በመልቀቅ ወደ
ቻይናው ክለብ Jiangsu Suning የተቀላቀለው ብራዚላዊው አማካይ ራሚሬስ
በድጋሚ ወደ ብራዚል በመመለስ በነፃ ዝውውር ፓርሜላስን ተቀላቅሏል።
═════════════════════════
ለሬያል ማድሪድ ቅርብ እንደሆነ የሚነገርለት ማርካ ትላንትና ባወጣው ዘገባ
ሬያል ማድሪድ የFC ቶኪዮውን የ 18 አመት ኮከብ ታክፉሳ ኩቦን €1million
አመታዊ ደሞዝ እና የ 5 አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት
ደርሰዋል።ለጃፓኑ ክለብም €2million የዝውውር ሂሳብ ይከፍላሉ።
═════════════════════════
ስፔናዊው አማካይ ሳንቲያጎ ካዘሮላ በቪያርያል ለተጨማሪ 1 አመት
የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ፈርሟል።
═════════════════════════
ኤቨርተን እና ፓሪሴንዤርመን ሁለቱም ክለቦች የአያክሱን ብራዚላዊ አጥቂ
ዴቪድ ኔሬስን በ £35m ገደማ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው። (Source: UOL
Esporte)
═════════════════════════
የባርሴሎናው አለቃ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ለኢቫን ራኪቲች ትክክለኛ የዝውውር
ጥያቄ የሚቀርብላቸው የካታሎኑ ክለብ ቢሸጠው ቅር እንደማይላቸው
ተገልፁዋል።ማንችስተር ዩናይትድም በክሮሽያዊው አማካይ ላይ ፍላጎት
እንዳላቸው አሳይተዋል።(Source: Cadena SER)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴስን
ለማስፈረም እየመሩ ይገኛሉ።ሊቨርፑል እና ማንችስተር ሲቲም የተጫዋቹ ፈላጊ
ናቸው።(Source: Radio Rossonera)
═════════════════════════
የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ ሮሚዮ ሉካኮ በግል ጉዳዮች ከኢንተር ሚላን
ጋር ከስምምነት ደርሱዋል የ5 አመት ኮንትራተም ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።የ
26 አመቱ ቤልጄማዊ በአመትም £6.6m ወደ ካዝናው ይከታል።(Source:
Gazzetta dello Sport)
══════════════════════
የደርቢ ካውንቲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ አዲሱ የቸልሲ አሰልጣኝ ሆኖ
ሊሾም ነው ጣልያናዊው አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ሳሪ በስታምፎርድብራጅ እንዲቆዩ
የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ ካደረጉ ቡኃላ።ላምፓርድ በድጋሚ ወደ ሰማያዊዎቹ
ቤት ተመልሶ ሲመጣም የቀድሞ የቡድን አጋሩን ዲዴር ድሮግባን በአሰልጣኝ
እስታፉ ውስጥ ማካተት ይፈልጋል ነገር ግን ጆንቴሪን ማካተት አይፈልግም።
(Sun)
═════════════════════════
የ 26 አመቱ ፈረንሳያዊ የማንችስተር ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ
ከኦልትራፎርድ በመልቀቅ ወደ ሳንቲያጎ በርናበው የማቅናት ፍተኛ ፍላጎት
አለው።(Marca)
═════════════════════════
የክሪስታል ፓላሱ £50m-የተገመተው የ 21 አመቱ እንግሊዛዊ የመስመር
ተከላካይ አሮን ዋን ቢሳካ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የማቅናት ፍላጎት
ቢኖረውም ግን ከንስር አሞራዎቹ ቤት ለመልቀቅ ማስገደድ አይፈልግም።(Sky
Sports)
═════════════════════════
ቶተንሀም ሆስፐር የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ ከሆነው ከ 24 አመቱ
የስፖርቲንግ ሊዝበኑ ፖርቹጋላዊ አማካይ ዝውውር እራሳቸውን አግለዋል።
(Mail)
═════════════════════════
የቸልሲው ብራዚላዊ አማካይ ዊልያን በስታምፎርድ ብሪጅ ለተጨማሪ ሁለት
አመት የሚያቆየውን ኮንትራት ለመፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።(Sun)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን
ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያን በኦልትራፎርድ ለማቆየት የተሻሻለ
ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።(ESPN)
═════════════════════════
ዩናይትዶች ባሁን ሰአት የአሮን ቫን ቢሳካ ዝውውርን ለማጠናቀቅ አተኩረው
እየሰሩ ነው። [evening standard]
═════════════════════════
አያክስ ለሞሮኩዋዊው የክንፍ መሰመር ተጫዋች ሀኪም ዚያች ከ£30m
በላይ የዝውውር ገንዘብ ይፈልጋሉ።አርሰናል እና ሊቨርፑል ከ 26 አመቱ
ተጫዋች ጋር ስማቸው የተያያዙ ክለቦች ናቸው። (Mirror)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ የ 23 አመቱን አርጀንቲናዊ አማካይ ጆቫኒ ሌሴልሶን
የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ነገር ግን የተጫዋቹ እናት ክለብ ሬያል ቤቲስ
ለዝውውሩ £67m ይፈልጋሉ ከዛ በታች በሆነ ገንዘብም የመደራደር አላማ
የላቸውም።እንዲሁ በተመሳሳይ ቶተንሀም ሆስፐርም የተጫዋቹ ፈላጊ ክለብ
ናቸው።(inews)
═════════════════════════
ሊቨርፑል ለ 24 አመቱ አይቬሪኮስታዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኒኮላስ
ፔፔ ለማስፈረም ሊል ጥያቄ ማቅረባቸው እየተነገረ ይገኛል።(Le10 Sport,
via Daily Express)
═════════════════════════
የአርሰናሉ አማካይ ሉካስ ቶሬራ ምንም እንኳን በመድፈኞቹ ቤት የመጀመሪያ
ሲዝኑ ጥሩ የውድድር አመት ቢያሳልፍም የለንደን ህይወትን መላመድ ከበደኝ
ማለቱን ተከትሎ ቆይታው የአርሰናል ደጋፊዎችን ጥርጣሬ ላይ ጥሉዋል ክለብም
በዚህ ዙሪያ ምንም አይነት የሰጠው ነገር የለም። (Source: Daily Mirror)
═════════════════════════
ቸልሲ ፍራንክ ላምፓርድ ከደርቢ ካውንቲ ጋር ኮንትራት ስላለው አዲሱ
አሰልጣኛቸው አድርገው ለመሾም ለሻምፕዮን ሺፑ ክለብ የውል ማፍረሻ £4m
መክፈል ይጠበቅባቸዋል። (Source: SkySports)
═════════════════════════
የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ የሊሉን የፊት አጥቂ ኒኮላስ ፔፔን ዝውውር
የሚያጠናቅቁት ከሆነ ግብፃዊውን መሃመድ ሳላህ ለመሸጥ ፍቃደኛ
ናቸው። (Source: Le10 Sport)
═════════════════════════
የ 31 አመቱ አርጀንቲናዊ የቀድሞ የቸልሲ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጉዌን ስሙ
ከሮማ ጋር ተያይዞ መነሳቱን ተከትሎ ወኪሉ እና ወንድሙ ሂጉዌን የእግርኩዋስ
ህይወቱን በጁቬንቱ እንደሚያጠናቅቅ ገልፁዋል።(Mirror)
═════════════════════════
ላዚዮ በአልባኒያዊው ግብ ጠባቂው ቶማስ ስትራኮሻ ላይ £44.5m
የዝውውር ዋጋ ለጥፈውበታል።የ 24 አመቱ ግብ ጠባቂ ስሙ ከአርሰናል እና
ከቶተንሀም ጋርም ተያይዞ ተነስቱዋል።(Il Messaggero, via
Football.London)
═════════════════════════
አዲሱ የሮማ አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ በዚህ ክረምት የማንችስተር
ዩናይትዱን ብራዚላዊ አማካይ ፍሬድን ለማስፈረም እያጤኑ ይገኛሉ።(Metro)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ የ 21 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ሺያን ሎንስታፍን
አሳምነው ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።ነገር ግን አማካዩ በኒውካስል
ለመቆየት ቁርጠኛ መሆኑም ተያይዞ ተዘግቡዋል።(London Evening
Standard)
═════════════════════════
አርሰናል የ 17 አመቱን ብራዚላዊ አማካይ ሬነሪ ጄሱስን ለማስፈረም
ለፍላሚንጎ ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።(Tuttomercatoweb, via
Talksport)
═════════════════════════
በአሁን ሰዓት በብራዚላ እግርኩዋስ ፌዴሬሽን በአስተባባሪነት እየሰራ
የሚገኘው የ 41 አመቱ የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ኤዱ በድጋሚ ወደ
መድፈኞቹ ቤት በመመለስ የቴክኒካል ዳይሬክተርነትን ቦታ ለመያዝ ከጫፍ
ደርሱዋል። (Football.London)
═════════════════════════
ቶተንሀም ሆስፐር £1m መድቡዋል በአዲሱ ስቴዴማቸው ለተጫዋቾች
የመዝናኛ ቦታውን ከፍ ባለ ደረጃ ለመስረት።ከሁለት ወራት ቡኃላም ስራ
ይጀምራል።(Sun)
═════════════════════════
ዌስትሀም እና ቶተንሀም ሆስፐር የቀድሞ የሊቨርፑል የክንፍ መስመር ተጫዋች
የነበረውን ሱሶን ከኤስሚላን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።የውል ማፍረሻውም
£35m ነው።(Source: Calciomercato)
ሊቨርፑል የ 25 አመቱን የሊዮን ኩዋስ አቀጣጣይ ነቢል ፈኪርን የማስፈረም
ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም።እንደሚታወቀው ባለፈው አመት ወደ ሊቨርፑል
ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ባለበት ጉዳት ምክንያት ዝውውር
ሳይሳካ ቀርቶ ነበረ።(Source: Independent)
ቤልጄማዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ ቶማስ ሙኒር በአርሰናል ቢፈለግም
በፓሪሴንዤርመን መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።(Source: Daily
Express)
ትላንትና የተጠናቀቁ ዝውውሮች
DEAL DONE : ዌስትሃሞች የ23 አመቱን ስፔናዊ ኢንተርናሽናል አማካይ
ፓብሎ ፎርናልስን ከቪያሪያል በ £24m እና በአምስት አመት ኮንትራት
ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል። (Source: West Ham United)
═════════════════════════
DEAL DONE : ሃርቬይ ባርኔስ በሌስተር ሲቲ ለተጨማሪ አምስት አመታት
የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል። (Source: Leicester City
Football Club)
═════════════════════════
DEAL DONE : ኤሲ ሚላኖች የክለቡን ሌጀንድ ፓውሎ ማልዲኒን
የክለባቸው ቴክኒካል ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።
(Source: AC Milan)
═════════════════════════
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment