Friday, June 14, 2019

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ እና አቅራቢ ⇒ አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ) 

የሀገር ውስጥ ዜናዎች

የኢትዮጵያ ቡና እና ፌድሬሽኑ ጉዳይ መጨረሻ ያገኘ ይመስላል

→የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን እና የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ውዝግብ ያበቃ ይመስላል።ፌድሬሽኑ ከትናንት በስቲያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 አንደርታ ጨዋታ ለዛሬ አርብ በዝግ ስቴዲየም እንዲካሄድ የወሰነ ቢሆንም ኢትዮጵያ ቡና ግን ትናንት በሰጠው የመልስ መግለጫ ይህንን ጨዋታ እንደማያካሂድ በገለፀው መሰረት ዛሬ ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል ።
ሆኖም ዛሬ በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ጨዋታው ማክሰኞ በ10 ሰዓት ለተመልካች ክፍት ሆኖ እንዲካሄድ ተወስኗል።ቡና በደል ደርሶብኛል በመሆኑም ጉዳዩን እሰከ ካስ ድረስ እወስደዋለው ማለቱ አይዘነጋም።
(መረጃውን ያገኘነው ከጋዜጠኛ ኑራ ኢማም ፌስቡክ ገፅ ላይ ነው)

የባህር ማዶ ስፖርታዊ ዜናዎች

ጁቬንትስ የፖግባን ጉዳይ እየገፋበት ነው


→የጁቬንትሱ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራቺ ለንደን ከተማ ወደ የሚገኘው የማንቸስተር ዩናይትድ ቅርንጫፍ መጓዛቸው ተጠቁሟል።ሰውየው ወደ ሀገር እንግሊዝ ያቀኑትም በ26 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል ፖል ፓግባ ጉዳይ ከቀያይ ሰይጣኖቹ የበላይ አመራሮች ጋር ለመምከር መሆኑ ነው የተሰማው።
አሮጊቷ የቀድሞ ኮከቧን ወደ ቱሪን ለመመለስ ደፋ ቀና ማለቷን አበርትታ ብትቀጥልም የፓፓ ፔሬዙ ሪያል ማድሪድ ቀመተ መለሎውን የጨዋታ ቀማሪ ወደ ማድሪድ ለማምጣት ባለው ከፍተኛ ፍላጎት የዚህ ዝውውር ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል።
(Sky Sports Italy, via Sky Sports)



ሉካኩ ወደ ኢንተር ሚላን ለመጓዝ ከጫፍ ደርሷል

→ቤልጄሚያዊው ግዙፍ አጥቂ ሮሜሮ ሉካኩ በግል ወደ ጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ለመጓዝ መስማማቱን በርካታ የጣሊያን ጋዜጦች ዘግበዋል።አንዳንድ ሚዲያዎችም የዚህ ዝውውር ጉዳይ የተገባደደ መሆኑን እና ተጨዋቹ እሰከ 2024  በክለቡ ለመቆየት መፈረሙን በቀናት ውስጥም ዝውውሩ ይፋ እንደሚሆን ነው ያተቱት።
(Gazzetta dello Sport, via Metro)




ሲቲ ከሃሪ ማጉዌር ዝውውር እጁን አውጥቷል

→ማንቸሰተር ሲቲ በአመቱ ድንቅ ብቃቱን በቀበሮዎቹ ቤት ያሳየውን እንግሊዛዊውን ተከላካይ ሀሪ ማጉዌር ለማዘዋወር የነበረውን ፍላጎት ለጊዜው ገትቶታል።ውሃ ሰዋያዊዎቹ ይህንን የዘየዱት ሌስተር ሲቲ ለ26 አመቱ ተከላካይ £90M በመተመኑ ነው ።
(Mail)



ዩናይትድ አማካይ ፍለጋ እየማሰነ ነው

→ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለማዘዋወር ገፍቶ መሄዱ ተነግሯል።የ24 አመቱ ኮከብ በሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሊቨርፑል እና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ማንቸስተር ሲቲም በጥብቅ ይፈለጋል።
(Radio Rossonera, via Sun)




ኮሼልኒ ወደ ጀርመን?

→ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከአርሰናል ቤት መውጣቱ አይቀሬ መሆኑ እየተነገረ ያለውን ፈረንሳዊውን የ33 አመት አንጋፋ ተከላካይ ላውረንት ኮሼልኒ ወደ ሲግናል ኢዱና ፓርክ በማምጣት የአጭር ጊዜ ተተኪ ሊያደርገው ይሻል።
(Mail)



ስፐርስ ሁለት ተጨዋቾችም አቅዳለች

→ቶተንሃም በክረምቱ የዝውውር መስኮት የሪያል ቤቲሱን የ23  አመት አርጀንቲናዊ የጨዋታ ቀማሪ ጂዮቫኒ ሎ ሴልሶ እና የሊዮኑን የ22 አመት አማካይ ታንጉይ ኒዱንቤ ለማስፈረም አቅዷል።ስፐርስ ይህንን ስታደርግ የክለቧን የዝውውር ሪከርድ እንደምትሰብርም ተገልጿል።
(Mirror)



የባርሳ እና ራኪቲች እህል ውሃ ሊያበቃ ነው

→የባርሴሎናው አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ በቂ የሆነ ገንዘብ ከቀረበ የ31 አመቱ ክሮሺያዊ አማካይ ኢቫን ራኪቲች ከክለቡ ቢለቅም ግድ እንደሌላቸው ተነግሯል።በርካታ የካታላኑ ክለብ ደጋፊዎች ግን አሰልጣኙ ከክለቡ እንዲለቁ በመወትወት ላይ ናቸው።
(Cadena SER - in Spanish)



ቶማስ ሙኒር በፔዤ መቆየት ይፈልጋል

→ከአርሰናል ጋር ስሙ በስፋት በመያያዝ ላይ ያለው ቤልጄሚያዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ ቶማስ ሙኒር በፓሪሰን ዤርመን መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።አርሰናል ይህንን ተጨዋች አጥብቆ እንደሚፈልገው በተደጋጋሚ ሲዘገብ ቆይቷል።
(Express)



ሀዛርድ ኩርቶዋ ወደ ማድሪድ እንድመጣ ምክንያት ሆኖኛል አለ


→ትናንት ከሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ጋር ትውውቅ ያደረገው ቤልጄሚያዊው ኮከብ ኤደን ሀዛርድ ወደ ሎስብላንኮዎቹ እንዲመጣ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ቲቦውት ኮርቶዋ እንዳግባባው ተናግሯል።ሀዛርድ ስለ ማሊያ ቁጥር ተጠይቆም ሞድሪችን 10 ቁጥር ማሊያ እንዲለቅለት ጠይቆት እምቢ እንዳለው ተናግሯል።
(Football.London)



አርሰናል የአጥቂዎቹን ኮንትራት ሊያራዝም ነው

→አርሰናል በግላቸው አስደናቂ አመትን ካሳለፉት ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ እና አሌክሳንደር ላካዜት ጋር ንግግር ጀምሯል።የአርሰናል የበላይ አመራሮች የሁለቱን አጥቂዎች ኮንትራት ለማራዘም ዳጎስ ያለ ክፍያ እንዳቀረቡም ተነግሯል።
(football.london)



No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...