አቅራቢ - ሳምሶን ስለሺ
═════════════════════════
ስፖርቲንግ ሊዝበን የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ የሆነውን ለጁቬንቱስ ከ 9
አመት በታች እየተጫወተ የሚገኘውን ክርስቲያኖ ጃርን ለማስፈረም ከአያቱ
ዶላሪስ አቬሮን ጋር ተገናኝተዋል። [SportMediaset]
═════════════════════════
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቀጣዩ አመት የቻምፕዮን
ሊግ ዋንጫን የሚያሸንፍ ከሆነ አንድ አመት እረፋት ለመውሰድ እያጤነበት
ይገኛል።(Star)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ የ 31 አመቱን ክሮሺያዊ ኢቫን ራኪቲችን ለማስፈረም
ከስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና ጋር ተገናኝቱዋል።(Sport - in Spanish)
═════════════════════════
ዩናይትድ የዝውውር ሪከርዱን በመስበር ከክርስታል ፓላስ የ 21 አመቱን
የመስመር ተከላካይ አሮን ዋን ቢሳካን እና የሌስተር ሲቲውን የ 26 አመት
የመሀል ተከላካይ ሀሪ ማጉዌርን በድምሩ ሁለቱንም በ £130m ለማስፈረም
ፍላጎት አላቸው።(Standard)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትዶች የኖርዊቹን እንግሊዛዊ ተከላካይ አሮን ዋን ቢሳካን
ማስፈረም የማይችሉ ከሆነ የ 19 አመቱን የኖርዊች ሲቲ ተከላካይ ማክስ
አሮንስን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።(Sky Sports)
═════════════════════════
የአያክሱ የመሀል ተከላካይ ማቲያስ ዴሊት አሁን ልቤ ምን እንደሚለኝ
አላውቅም ነገር ግን ስለወደፊት ቆይታዬ ከእረፍት ቡኃላ ወስናለው ሲል
ተናግሯል።(Mundo Deportivo - in Spanish)
═════════════════════════
የማቲያስ ዴሊት አማካይ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ቢዘዋወር የመጀመሪያ
ተሰላፊ የመሆን እድል የተሻለ እንደሚሆን ነገሮታል ወደ ባርሴሎና ከመዘዋወር
ይልቅ ለወደፊት የእግርኩዋስ ህይወቱ።(Sport)
═════════════════════════
ቸልሲ የአሁኑን አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪን ለመተካት አሰልጣኞችን
እያፈላለገ ነው በቀጣዩ ሳምንትም ጣልያናዊው አሰልጣኝ ከስታምፎርድ ብሪጅ
እንደሚለቁ ይፋ ይደረገል።(Mirror)
═════════════════════════
የቸልሲ ባለስልጣናት ማውሪዚዮ ሳሪ በድጋሚ እንዲያጤኑበት ነግረዋቸዋል
ጣልያናዊው ሰው በስታምፎርድብሪጅ ለተጨማሪ አመት እንዲቆይ ስለሚፈልጉ።
(Sun)
═════════════════════════
ቸልሲ ከደርቢ ካውንቲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ጋር ተገናኝተዋል
የቀድሞ አማካያቸውን በድጋሚ ወደ ስታምፎርድብሪጅም ለመመለስም እንደሆነ
ተዘግቡዋል።(Mail)
═════════════════════════
የቸልሲው የክንፍ መስመር ተጫዋች ካሉም ሆድሰን ኦዶያ አዲስ ኮንትራት
ከመፈረሙ በፊት በዋናው ቡድን በቂ የመጫወታ ግዜ እንዲሰጡት ዋስትና
ይፈልጋል። የ 18 አመቱ እንግሊዛዊ በሰማያዊዎቹ ቤት የቀረው የ 1 አመት
ኮንትራት ብቻ ነው።(Sun)
═════════════════════════
ሬያል ማድሪድ ሁሉንም ነገር ማድረግ ይፈልጋል የማንችስተር ዩናይትዱን
ፈረንሳያዊ አማካይ ፖል ፖግባን ለማስፈረም የአሰልጣኝ ዜኔዲን ዚዳንም
የመጀመሪያ ተቀዳሚ ምርጫ ነው።(Marca)
═════════════════════════
አርሰናል የሮማውን አማካይ ሎዛኖ ፔሌግሪኒን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው
ተጫዋቹም የውል ማፍረሻው £27m ብቻ ነው ነገር ግን
ከቶተንሀም፣ከኤስሚላን እና ከኢንተር ሚላን ከፍተኛ ፉኩኩር ይጠብቃቸዋል የ
22 አመቱን ጣልያናዊ ለማስፈረም።(Mirror)
═════════════════════════
ዌስትሀም የቪያርያሉን ስፔናዊ አማካይ ፓብሎ ፎርናሌስን ኢላማቸው
አድርገውታል በቬልታቪጎው ስሎቫኪያዊ አማካይ ስቴንስላቭ ሎቦትካ ላይ
ያለውን ፍላጎት ካቀዘቀዙት ቡኃላ። (Guardian)
═════════════════════════
ከፓሪሴንዤርመን ጋር የተለያየው የቀድሞ የጣልያን ግብ ጠባቂ ጂያንሉጆ
ቡፎን ወደ ፖርቶ ሊቀላቀል ነው በልብ ህመም ምክንያት ጫማ የሰቀለውን የ
38 አመቱን ስፔናዊ በረኛ ኢከር ካሲያስን ለመተካት።(Tuttosport - in
Italian)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣዩ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ስፔናዊውን
ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያን አዲስ ኮንትራት አቅርበውለት የግዜ ገደብ ሰተውታል
ኮንትራቱ የማያራዝም ከሆነ በቀጣዩ አመት በነፃ ዝውውር ከመልቀቅ ይልቅ
ከወዲሁ ለመሸጥ።(Telegraph)
═════════════════════════
ዩናይትድ የአያክሱን የ 23 አመት ግብ ጠባቂ አንደር ኦናናን ለማስፈረም
እየተመለከቱ ነው ዴቪድ ዴህያ በዚህ ክረምት የሚለቅ ከሆነ።(Independent)
═════════════════════════
ባርሴሎናዎች ተስፍ አድርገዋል እስከ €60m በሚደርስ ገንዘብ እስክ
ፈረንጆቹ ሰኔ 30 ድረስ ተጫዋቾችን መሸጥ ይፈልጋሉ የ 2018-19 የፋይናንስ
አወጣጥ ባላንሳቸውን ለማመጣጠን።(ESPN)
═════════════════════════
እንዲሁ በተመሳሳይ የካታሎኑ ክለብ የ 15 አመቱን የዌስትሀም አጥቂ ላዊ
ባሪን ማስፈረም ይፈልጋሉ።(Birmingham Mail)
═════════════════════════
እንግሊዛዊው አማካይ አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌን በሊቨርፑል እስከ
2023 የሚያቆየው ኮንትራት ቢኖረውም ለተጨማሪ 12 ወራት የሚያቆየውን
አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ተዘጋጅቱዋል።(Mail)
═════════════════════════
አትሌቲኮ ማድሪድ ፖርቹጋላዊውን የቤኔፊካ የፊት መስመር ተጫዋች ጆኦ
ፍሌክስ የአንቱዋን ግሬዝማን ቁጥር 1 ተተኪ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው።
(AS - in Spanish)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ ጣልያናዊውን የመስመር ተከላካይ ማቲዮ ዳርሚያን
ለመሸጥ ከቫሌንሺያ እና ሁለት ስማቸው ካልተጠቀሱ የጣልያን ክለቦች ጋር
እየተነጋገሩ ነው።(ESPN)
═════════════════════════
የቦካ ጁኔሩ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኒኮላስ ቡርዲሶ ተስፍ አድርገዋል የ 35
አመቱን ጣልያናዊ የሮማ አማካይ ዳንኤል ዴሮሲን ወደ አርጀቲና
እንደሚያመጡት።ነገር ግን ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ተጫዋቹ ወደ አሜሪካኑ
ሎሳንጀለስ ያቀናል እያሉ ይገኛሉ።(Closs Continental via Yahoo)
═════════════════════════
ኮስታርካዊው ግብ ጠባቂ ኬለር ናቫስ ሬያል ማድሪድ የቀሪውን የሁለት
አመት ኮንትራት ገንዘብ እንዲከፍሉት ይፈልጋል በዚህ ክረምት ከክለቡ በነፃ
የዝውውር ለመልቀቅ ነገር ግን ሎስብላንኮዎቹ ከተጫዋቹ €20m ዝውውር
ይፈልጋሉ።(AS - in Spanish)
═════════════════════════
የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና ሀላፊ ኤድውድ ዋርድ በዚህ ክረምት
የስፖርቲንግ ዳይሬክተር እንደሚቀጥሩ ተስፋ አድርገዋል። (Mail)
═════════════════════════
የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ የሆነው አሮን ዋንቢሳካ ለክለቡ ክሪስታል
ፓላስ ህልሙ ወደሆነው ኦልትራፎርድ እንዲዘዋወር እንዲፈቅዱለት ጠይቁዋል።
═════════════════════════
ትላንትና ማታ ቤልጄም ስኮትላንድን 3-0 ስታሸንፍ 2 ግቦችን ያስቆጠረው
ሮሚዮ ሉካኮ፦ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ተገናኝቻለው ለክለቤ እና ለወኪሌ
ፌድሪኮ ፓስቶሬሌ ጥሩ ውሳኔ የሚለውን ውሳኔውን እንደሚናገር
ተናግሩዋል።በዚህ ሰዓት የ Gazzetta dello Sport ጋዜጠኛ የሆነው
ፍራንሲስኮ ፎንታና ወደ ኢንተር ትዘዋወራለክ እንዴ ሲለው ሉካኮ መልስ
ከመስጠት በመቆጠብ ፈገግታውን አሳይቶታል።
═════════════════════════
ቶተንሀም የመሀል ክፍሉን ለማጠናከር ፖርቹጋላዊውን አማካይ ብሩኖ
ፈርናንዴስን ለማስፈረም ስፖርቲንግ ሊዝበን የለጠፈበትን £63m ለመክፈል
ፍቃደኛ እንደሆኑ እየተነገረ ነው።(O Jogo)
═════════════════════════
አርሰናል የቻይናው ክለብ ዴሊያንግ ይፋንግ ለቤልጄማዊው የክንፍ መስመር
ተጫዋች ያኒክ ካራስኮ የሚፈልገውን £25m ለመክፈል ፍቃደኛ ናቸው።
(evening standard)
═════════════════════════
ማርሴሎ በዚህ ክረምት ከሬያል ማድሪድ የመልቀቅ እቅድ የለውም
ፈረንሳያዊው ተከላካይ ፌርላንድ ሜንዲይ ወደ ሳንቲያጎ በርናበው ቢዘዋወርም
═════════════════════════
ሊቨርፑል ስሙ £60million ከተገመተው የሊሉ አይቬሪኮስታዊ ኮከብ
ኒኮላስ ፔፔ ጋር ስሙ ተያይዞ ቢነሳም Evening Standard ግን የቀያዮቹ
የፍላጎት ኢላማ ውስጥ የለም ሲል ዘግቡዋል።
═════════════════════════
ቸልሲ የሁለት አመት የዝውውር እገዳ ቢጣልበትም የቫሌንሺያውን
ፖርቹጋላዊ ኮከብ ጎንካሎ ጉዴስን ለማስፈረም £62m ማቅረባቸው እየተነገረ
ይገኛል።(express)
═════════════════════════
የፓሪሴዤርመኑ ኮከብ ኔይማር በፈረንሳዩ ክለብ ደስተኛ አደለም በዚህ ወደ
ባርሴሎና መመለስ ይፈልጋል።(Sport)
═════════════════════════
No comments:
Post a Comment