Tuesday, June 11, 2019

የዕለተ ማክሰኞ ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ እና አቅራቢ - ሳምሶን ስለሺ



═════════════════════════
ሬያል ማድሪድ በዚህ ክረምት ቡድኑን እንደ አዲስ ለመገንባት የአማካይ
ክፍላቸውን ለማጠናከር ከፖል ፖግባ እና ከክርስቲያን ኤሪክሰን አንዱን
ማምጣት ይፈልጋሉ ነገር ግን ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን እስከ
£70m በሆነ ርካሽ ዋጋ ሊያገኙት ይችላሉ ተብሉዋል።(Source: Daily Mail)
═════════════════════════
ዌስትሀም የሴልታቪጎዎቹን ጥንዶች ማክሲ ጎሜዝን እና ስቴንስላቭ
ሎቦትካን ለማስፈረም £53.5m በማቅረብ ድርድር የማድረግ አላማ አላቸው።
(Source: Daily Star)
═════════════════════════
እንደ ፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፓሪሴንዤርመን እምነት የአያክሱን የ 19 አመት
የመሀል ተከላካይ ማቲያስ ዴሊትን ከ £350,000 በላይ ሳምንታዊ ደሞዝ
በማቅረብ እንደሚያስፈርሙት እምነት አድርገዋል።(Source: Independent)
═════════════════════════
ዌስትሀም ዩናይትድ የ 24 አመቱን አማካይ ሞርጋን ሳንሶን ለማስፈረም
ከፈረንሳዩ ክለብ ማርሴ ጋር እየተነጋገሩ ይገኛሉ።ተጫዋቹም €35m ዝውውር
ተመን ወቶለታል።(Source: SkySports)
═════════════════════════
DEAL DONE:ጆንጆ ኬኒ በአንድ አመት የውሰት ውል ከኤቨርተን ወደ
ሻልካ 04 መዘዋወሩ ተረጋግጧል።(Source: FC Schalke 04 )
═════════════════════════
አንቶኒዮ ግሬዝማን አሁን በአትሌቲኮ ማድሪድ በአመት የሚያገኘውን
€23m አመታዊ ደሞዝ በ €6m በመቀነስ ወደ ካታሎኑ ክለብ ባርሴሎና
በሀምሌ አንድ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።በዚህም በአመት €17m አመታዊ
ደሞዝ ያገኛል እንደማለት ነው።(Source: SoccerLink)
═════════════════════════
አርሰናል የሴንቲቴኑን ተከላካይ ዊልያም ሳሊባን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው
ነገር ግን የሊግ 1 ክለብ የ 18 አመቱን ፈረንሳያዊ ተከላካይ በውሰት በመስጠት
በቀጣዩ ሲዝን መልሰው መውሰድ ይፈልጋሉ።(Source: Football.London)
═════════════════════════
ባርሴሎና በድጋሚ ከወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር ንግግር ሊያደርግ ነው
ለመጨረሻ ግዜ ሆላንዳዊውን ተከላካይ ማቲያ ዴሊትን አሳምነው ለማስፈረም።
(Source: ESPN)
═════════════════════════
በፈረንሳያዊው አማካይ ፖል ፖግባ እምነት ያጡት ማንችስተር ዩናይትዶች
እሱን ለመተካት የቶተንሀሙን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን እና የሞናኮውን
አማካይ ዩሪ ቴልማስን ለማስፈረም እያጤኑበት ይገኛሉ የ 26 አመቱ አማካይ
ወደ ሬያል ማድሪድ ወይም ወደ ጁቬንቱስ የሚያቀና ከሆነ።(Source:
Standard)
═════════════════════════
ማንችስተር ሲቲ ለቤኔፊካው ፖርቹጋላዊ የፊት መስመር ተጫዋች ጆኦ
ፍሌክስ £26m አመታዊ ደሞዝ እንዳቀረቡለት ተዘግቡዋል።(Source:
Record)
═════════════════════════
ኢንተር ሚላን ከማንችስተር ዩናይትድ ሮሚዮ ሉካኮ ለማስፈረም ኢቫን
ፔሪሲችን አንድ የዝውውሩ አካል አድርገው ቢያቀርቡም በቀያይ ሴጣኖቹ ውድቅ
ተደርጎባቸዋል።(Source: Daily Star)
═════════════════════════
DEAL DONE:አስቶንቪላ በ £8m ገደማ ከሊል በውሰት የወሰዱትን
አንዋር ኤልጋዚን በአራት አመት ኮንትራት በቁዋሚነት ማስፈረማቸውን
አረጋግጠዋል።(Source: Aston Villa FC )
═════════════════════════
DEAL DONE:የቀድሞ የባየርሙኒክ ተከላካይ ራፊኒያ ወደ ብራዚሉ ክለብ
ፍላሚንጎ በ 2 አመት ኮንትራት መዘዋወሩ ተረጋግጧል።(Source: Clube de
Regatas)
═════════════════════════
ሪያል ማድሪዶች የአማካዩ ማቲዮ ኮቫች መሸጫ ዋጋ £45m ነው ብለዋል።
ሆኖም ቼልሲዎች ያን ያህል ብር መክፈል አይፈልጉም ሆኖም ኢንተር ሚላኖች
ክሮሺያዊውን አማካይ ለማዛወር ፍላጎት አሳይተዋል። (Source: AS)
═════════════════════════

ማን.ዩናይትዶች ስፔናዊው የ28 አመት ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደ ሂያ በዚህ
የዝውውር መስኮት ላይ ፒ.ኤስ.ጂን የሚቀላቀል ከሆነ የ £20m ክፍያ
ይፈፅሙለታል። (Sun)
═════════════════════════
ዩናይትዶች ለ21 አመቱ እንግሊዛዊ ተከላካይ አሮን ቫን ቢሳካ ዝውውር
ያቀረቡት የ £40m ሂሳብ ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ክሪስታል ፓላሶች ተከላካዩን
ለመልቀቅ እስከ £60m ድረስ ይፈልጋሉ። (Sky Sports)
═════════════════════════
የአርሰናሉ አለቃ ኡናይ ኤምሬ ከ27 አመቱ ቤልጂየማዊ የፒ.ኤስ.ጂ ቀኝ
ተመላላሽ ተከላካይ ቶማስ ሙኒር ስለሚያዛውሩበት ሁኔታ ከፓሪሱ ክለብ ጋር
ተወያይተዋል። (Express)
═════════════════════════
ጉዳት ካስተናገደ ቡኃላ በአሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በቂ የመሰለፍ እድል
እያገኘ የማይገኘው እንግሊዛዊው የመስመር ተከላካይ ዳኒ ሮዝ ከቶተንሀም
ሆስፐር ሊለቅ እንደሚችል ፍንጭ ሰቱዋል።
═════════════════════════
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዴር ዴሻምፕ የሊዮኑ የመስመር
ተከላካይ ፌርላንድ ሜንዲ ወደ ሬያል ማድሪድ እንደሚዘዋወር
አረጋግጠዋል።አንዶራን ከመግጠማቸው በፊት በሰጡት ቅድመ ጫወታ ፕሬስ
ኮንፍራንስ፦ከሁለት አመት በፊት በሁለተኛው የፈረንሳይ የሊግ እርከን ይጫወት
ነበር አዎን ግን በቅርብ ለሬያል ማድሪድ ይጫወታል ሲሉ ተናግረዋል።
═════════════════════════
የማንችስተር ዩናይትዱ ኮከብ ፖል ፖግባ ወደ ጁቬንቱስ ለመመለስ
ከስምምነት መድረሱ እየተዘገበ ይገኛል።ለዚህም የጣልያኑ ክለብ የፋይናንስ
ጨዋነት ደንብን ለማክበር ሲባል 5 ተጫዋቾችን ለገበያ ማቅረባቸውን
Corriere dello Sport ዘግቡዋል።እነሱም ማርዮ ማንዙኪች፣ዳግላስ
ኮስታ፣ጆኦ ካንሴሎ፣ሁዋን ኩዋድራዶ እና ማቲያ ፔሪኒ ናቸው።
═════════════════════════
ከ talkSPORT ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ የቶተንሀም ሆስፐር አሰልጣኝ
ሀሪ ሬድናፕ ማንችስተር ዩናይትድ ጋሬዝ ቤልን ከሬያል ማድሪድ
እንዲያዘዋውሩት አስጠንቅቀዋል : ይህ ዝውውር የሚሳካ ከሆነ ትልቅ ዝውውር
ነው እና ይመስለኛል ወደ ቀድሞ አቁዋሙ ይመለሳል። እሱ አስደናቂ ተጫዋች
ነው ማንኛውንም ቡድን መቀየር የሚችል ተጫዋች ነው።
═════════════════════════
ሬያል ማድሪድ የናፖሊ ኢላማ በሆነው በኮሎምቢያዊው አማካያቸው ሀሜስ
ሮድሪጌዝ ላይ £37.35m የዝውውር ዋጋ ለጥፈውበታል።በባየርሙኒክ የሁለት
አመት የውሰት ውሉን ያጠናቀቀው እና ከካርሎ አንቾሎቲ ጋር በበርናበው
የሰራው ሀሜስ በጣልያኑ ክለብ በጠንካራ ሁኔታ እየተፈለገ ይገኛል ሲል
Corriere dello Sport ዘግቡዋል።
═════════════════════════
ጀርመናዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች ዩልያን ድላክስለር በዚህ ክረምት
ከፓሪሴንዤርመን የመልቀቅ ምንም አይነት ፍላጎት የለውም የቶተንሀም እና
የባየርሊቨርኩሰን ኢላማ ቢሆንም።(Source: BILD)
═════════════════════════
ፓሪሴንዤርመን ከሌስተር ሲቲውን የመስመር ተከላካይ ሪካርዶ ፓሬራን
ተገናኝተዋል ቤልጄማዊው የመስመር ተከላካይ ቶማስ ሚኑር ለመልቀቅ
ስለተዘጋጀ እሱን ለመተካት በማሰብ።(Source: YS)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የግራ መስመር ተከላካይ አሮን
ዋንቢሳካን ከክርስታል ፓላስ ለማስፈረም £40m ቢያቀረቡም ውድቅ
ከተደረገባቸው ቡኃላ አሁን ሌላ የተሻሻለ £50m የዝውውር ገንዘብ ሊያቀርቡ
ነው።(Source: SkySports)
═════════════════════════
በአያክስ የተሳካ አመትን ያሳለፈው ዶኒ ቫንደርቤክ ልቡ ወደ ፕሪምየርሊጉ
ሸፍቱዋል ከቶተንሀም እና ከማንችስተር ዩናይትድም አንዱን የመቀላቀል ፍላጎት
አለው።(Source: talkSPORT)
═════════════════════════
አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ በ 24 ሰዓት ውስጥ የቸልሲ አሰልጣኝነታቸውን
በመልቀቅ ወደ ጁቬንቱስ እንደሚያቀኑ ይጠበቃሉ።(Source: Sky Italy)
═════════════════════════
የቶተንሀሙ ፈረንሳያዊ ግብ ጠባቂ ሁጎ ሎሪስ የማንችስተር ዩናይትድ ቁ 1
ኢላማ ሆኑዋል ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ዴቪድ ዴህያ በዚህ ክረምት
ከኦልትራፎርድ የሚለቅ ከሆነ።(Source: Sun Sport)
═════════════════════════
የ 26 አመቱ ስሎቬኒያዊ የአትሌቲኮ ማድሪዱ ግብ ጠባቂ ጃንኦብላክ በዚህ
ክረምት መልቀቅ ይፈልጋል በዚህም ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ማቅናት
ይፈልጋል ከፓሪሴንዤርመን ይልቅ።(ESPN)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ ለሬያል ማድሪድ የ 26 አመቱ ፈረንሳያዊ አማካይ ፖል
ፖግባ እንደማይሸጥ ነግረዋቸዋል።(AS)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ የአሮን ዋንቢሳካን ዝውውር የማያሳካ ከሆነ
ከቶተንሀም በዚህ ክረምት ሊለቅ የሚችለውን የ 28 አመቱ የመስመር ተከላካይ
ዳኒ ሮዝ ላይ ያላቸው ፍላጎት በድጋሚ ሊያገረሽ እንደሚችል ተነግሯል።
(Manchester Evening News)
═════════════════════════
ቶተንሀም ሆስፐር በጠንካራው ሁኔታ የማርሴውን ጃፓናዊ የቀኝ መስመር
ተከላካይ ሂሮኪ ሳኪን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው። (Sky Sports)
═════════════════════════
ሊቨርፑል ከ 31 አመቱ የወርደርብሬመን የፊት መስመር ተጫዋች ማክስ
ክሩስ ዝውውር እራሳቸውን አግልለዋል።(Liverpool Echo)
═════════════════════════
ቫሌንሺያ ስፔናዊውን የኒውካስል አጥቂ አዮዞ ፔሬዝን የማስፈረም ፍላጎት
አላቸው።(Cope - in Spanish)
═════════════════════════
ፖርቹጋላዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ በዚህ ክረምት
ከባርሴሎና መልቀቅ ይፈልጋል።አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ የተጫዋቹ ፈላጊ
ክለብ ነው ነገር ግን የካታሎኑ ክለብ ለተጫዋቹ ዝውውር €40-€50m
ይፈልጋል።(Marca)
═════════════════════════
ማንችስተር ሲቲ የቀድሞ የስቶክ ሲቲ አማካይ የነበረውን የሮሪ ዴላፕን የ
16 አመት ልጅ ከደርቢ ካውንቲ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።(Derby
Telegraph)
═════════════════════════

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...