Monday, June 10, 2019

የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

ዕለተ ሰኞ ምሽት የወጡ አዳዲስ የሀገር ውስጥ እንዲሁም የባህር ማዶ ስፖርታዊ መረጃዎችን እንደሚከተለው አሰናድተናል

 

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)    
አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)







የሀገር ውስጥ ዜናዎች

➖በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትናንት ተቋርጦ ዛሬ የቀጠለው የዲላ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታ በዲላ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሁለት ጨዋታ በቀረው ውድድርም ወልቂጤ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን ሙሉ ለሙሉ ለማለት በቀረበ መልኩ አረጋግጧል፡፡
መድን ለማደግ ሁለቱንም ጨዋታዎች አሸንፎ ወልቂጤ ሁለቱንም ተሸንፎ የስድስት ጎል ልዩነቱን መቀልበስ ይኖርበታል ሲል ሀገርኛው ድህረ ገፅ ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።
ምንጭ ➖Soccer Ethiopia


የባህር ማዶ ዜናዎች

ፖግባ ወደ ጁቬንትስ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሷል


➖የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ፖል ፖግባ ወደ ቀድሞ ክለቡ ጁቬንትስ ክረምት ላይ ለመመለስ ከስምምነት ላይ መድረሱን የጣሊያኑ ሚዲያ Corriere dello Sport በዛሬው አምዱ አስነብቧል።ጋዜጣው በሀተታው እንደገለፀው ከሆነ ቢያንኮኔሬዎቹ ፈረንሳዊውን የጨዋታ ቀማሪ ወደ ቱሪን ከማምጣታቸው በፊት ግን አንዳንድ ተጨዋቾችን ለመልቀቅ ነው ያሰቡት።
ፖግባ ከሞሪንሆ ስንብት በኋላ በሶልሻየር ስር በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት አስደናቂ አቋምን ያሳየ ቢሆነም የኋላ ኋላ ከደረጃ በታች ተጫውቷል በማለት በርካታ የቀያይ ሰይጣኖቹ ደጋፊዎች ወቀሳ ሲሰነዝሩበት መሰንበታቸው ይታወሳል።
(Corriere dello Sport)


አሮጊቷ በርካታ ተጨዋቾችን ልትለቅ ነው

➖ጁቬንትሶች በተከፈተው የዝውውር መስኮት ከተጨዋቾች ሽያጭ £97.81m  ወደ ካዝናቸው ለማስገባት ተሰናድተዋል።አሮጊቷ ይህንን ገንዘብ ለማግኘት ክሮሺያዊውን አጥቂ ማሪዮ ማንዙኪች ፥ ፉል ባኩን ጁዋዎ ካንሴሎ ፥ ዊንገሩን ሁዋን ኳድራዶ እና ግብ ጠባቂውን ማቲያ ፔሪን ገበያ ላይ የምታወጣ ይሆናል፡፡
(Tuttomercato)


ሲቲ አዲሱ የፌሊክስ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል

➖ማንቸስተር ሲቲ በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ ያለውን የቤኔፊካውን የ19 አመት ተጨዋች ጁዋዎ ፌሊክስ ለማዘዋወር ፍክክር ውስጥ መግባቱ ተገልፇል።ወሃ ሰማያዊዎቹ ለዝውውሩ ያሰናዱት ሂሳብም £26M መሆኑ ተነግሯል።
ፌሊክስ በዋናነት በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወቃል።ብዙ ጫና እየደረሰባቸው ያሉት የቀያይ ሰይጣኖቹ ዳይሬክተር ኢድ ውድ ዋርድም ይህንን ዝውውር አጥብቀው ይሹታል።
(Record)


ሪያል ማድሪድ ምባፔን ወደ በርናቢዮ ለማምጣት እየሰራ ነው


➖አንቷን ግሪዝማን ከባርሴሎና ይልቅ ወደ ፓሪሱ ክለብ ፓሪሰን ዤርመን ይሄዳል የሚለው ዜና ሚዛን እየደፋ መምጣቱን ተከትሎ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሪያል ማድሪድ ኪልያን ምባፔን ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል።ከኔይማር ጋር ያለው ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ የሚነገርለት ታዳጊው ኮከብ ምባፔ ሌላ ሱፐር ስታር ክለቡ የሚያስፈርም ከሆነ ወደ በርናቢዮ የሚያደርገው ጉዞ ሊሰምር እንደሚችል ነው እየተነገረ ያለው።ሎስብላንኮዎቹ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ስንብት በኋላ ድርቅ የመታውን የአጥቂ ክፍላቸው ምባፔን ከሃዛርድ በማጣመር መመልስ ይፈልጋሉ።
(AS)


አርሰናል አማካይ ፍለጋ ገበያ ወጥቷል

➖አርሰናል የፊዮረንቲናውን የቀድሞ አስቶን ቪላ አማካይ ጆርዳን ቬርቶት ለማዘዋወር  ጥረት መጀመሩን L'Equipe አስነብቧል።ታማኙ የፈረንሳይ ሚዲያ አክሎም ምንም እንኳን መድፈኞቹ የ26 አመቱን ተጨዋች ለማዘዋወር ፍላጎታቸው ከፍተኛ ቢሆንም የጣሊያኑ ናፖሊም የዚህን ተጨዋች ዝውውር በአፅንዖት እንደሚመለከተው ገልፇል።
(L'Equipe)


"ወደ ጁቬንትስ እንደመጣ ክርስቲያኖ ጠይቆኛል" ማቲያስ ደ ላይት



➖በበርካታ ክለቦች አይን ውስጥ የወደቀው የአያክሱ ታዳጊ ተከላካይ ደ ላይት ትናንት በኔሽንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታው ከተገባደደ በኋላ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ጁቬንትስ እንዲመጣ እንደጠየቀው ተናገረ።
ሆላንዳዊው የ19 አመት ተከላካይ በዘንድሮ አመት ከአያክስ ጋር በተለይ በሻምፒዮንስ ሊግ አስደናቂ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ በበርካታ ጉምቱ ሀያላን የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ የወደቀ ሲሆን ባርሴሎና ወይም ፒ.ኤስ.ጂ ማረፊያው እንደሚሆን ሲጠበቅ ነው የትናንት ምሽቱ ክስተት የተከሰተው።
(NOS)


የቼልሲ ቀጣዩ አሰልጣኝ???

➖ቼልሲዎች ማውሪዚዮ ሳሪን ካሰናበቱ ማንን መተካት እንዳለባቸው አለመወሰናቸው ተነግሯል።ነገር ግን በዘንድሮ አመት ደርቢ ካውንቲን ይዞ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ከጫፍ ደራሶ ያልተሳካለት የቀድሞ ሌጀንድ ፍራንክ ላምፓርድ ከእጩዎቹ ውስጥ መሆኑ ታውቋል።
(Daily Star)


ዩናይትድ ፔሪሲችን አልሟል

➖ማንቸስተር ዩናይትዶች ሮሜሮ ሉካኩን ለኢንተር ሚላን በመስጠት በምትኩ ኢቫን ፔሪሲችን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ማምጣት ይፈልጋሉ።ቀያይ ሰይጣኖቹ ክሮሺያዊውን ዊንገር በተለይ በሞሪንሆ ጊዜ በእጅጉ ሲፈልጉት እንደነበር ይታወሳል።
(Daily Star)


አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሃና ልጅ)

ስላነበቡልን እናመሰግናለን!

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...