ከትላንት ማምሻ ጀምሮ ቸልሲ እና ጎንዛሎ ሂግዌን ተስማምተዋል ሚሉ መረጃዎች ሲዎጡ ነበር ዛሬ ረፋዱንም ተጠናክረው ወተዋል ምናልባትም ዝውውሩ በሰአታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል ቸልሲዎች ለሂግዌን በሳምንት እስከ 140ሺ.ፓ ለመክፈል ተስማምተዋል በክረምቱ ደግሞ በ36ሚ.ፓ የመግዛት ግዴታ ውስጥ መግባታቸው እና መስማማታቸው እየተነገረ ነው
ጆዜ ሞሪንሆ ቤኔፊካን እንዲያሰለጥኑ ፍላጎት እንዳላቸው የክለቡ ፕሬዛዳንት ሉይስ ፊሊፔ ቬራ ተናግረዋል በቅርቡ ሩይ ቪክቶሪያን ከሀላፊነት እንደተነሱ ይታወቃል ቬራ ሲናገሩም በቀጣዩ ሳምንት አዲስ ነገር ጠብቁ ጆዜን እስካሁን አላናገርኩትም ግን ቡድኑን መያዝ ሚፈልግ ከሆነ ነገ ቡድኑን መያዝ እንደሚችል እናገራለው ሞሪንሆ አሰልጣኙ እንዲሆን የማይፈልግ የለም ብለዋል
ዴኒስ ሱዋሬዝ አርሰናልን ሚቀላቀል ከሆነ ሄነሪክ ሚኪታሪያን አርሰናልን ሊለቅበት የሚችልበት እድል አለ ኡናይ ኤምሪ ዝውውሩ አሁን ቋሚ እንዲሆን ይፈልጋሉ ባርሴሎና ግን አሁን በውሰት ሰተው በክረምቱ በ20ሚ.ፓ ከፍሎ የማስፈረም አማራጭ ስምምነት ውስጥ ሚያስገባ ከሆነ ስፔናዊውን አማካይ ማግኘት ይችላሉ የሚል እምነት አላቸው ዝውውሩም ወደ መጠናቀቁ ደርሷል
ሪያል ማድሪድ ፒቴክን በውሰት ውል ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል በጣሊያን ሴሪአ 12ጎሎችን ያሥቆጠረውን ፒቴክን አምጥተው የጎል ማግባት ችግራቸውን ለመፍታት ይሄንን ፖላንዳዊውን ግብ አዳኝ ፈልገውታል
ባርሴሎናዎች የ19 አመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ ዦን ክላይቭቶዲቦን ከቱሉዝ በነፃ ለማስፈረም ተስማምተዋል በክረምቱ ወደ ካታሎንያ የሚያመራ ይሆናል
ማንችስተር ዩናይትድ የፊዮሬንቲናውን ሰርቢያዊ ተከላካይ ኒኮላ ሜሪንኮቪች ለማዘዋወር እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተሰምቷል አማካዩን አንድሬስ ፔሬራን የዝውውሩ አካል አድርገው ስለማቅረባቸው ተነግሯል ከዚህ ውጪ በቼልሲ እና አርሰናል የሚፈለገውን የካግላሪውን አማካይ ኒኮሎ ባሬላን ለማስፈረም ዩናይትዶች 30ሚ.ፓ አቅርበዋል
ባይርን ሙኒክ በአለም ዋንጫ ድንቅ ብቃቱን ያሳየውን የስቱትጋርቱን ቤንጃሚን ፓቫንን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ባየርኖች ለልጁ ውል ማፍረሻ 35ሚ.ዩ ከፍለዋል ልጁም በአመቱ መጨረሻ ባየርንን ይቀላቀላል
አንድሬስ ኢኔስታ ስለ ኔይማር ወደ ባርሴሎና መመለስ ተጠይቆ ሲመልስ በእግር ኳስ ማይመስሉ ግን የሆኑ 100ሺ ነገሮችን አውቃለው ነገር ግን ኔማር ወደ ባርሴሎና ይመለሳል ብዬ አላስብም ብሏል ከአለማችን ምርጥ ተጨዋች አንደኛው ነውም የሚል አስተያየት ሰቷል
gobezoch bertw manchester united wedfit
ReplyDelete