ቼሌሲ ዛሬ ለቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ዊንገር ክርስቲያን ፑሉሲች ይፋዊ የሆነ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል ።ሰማያዊዎቹ ለአሜሪካዊው ተጨዋች ያለቸው ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም ክለቡ ዶርትሙንድ ግን ለተጨዋቹ £70M ይፈልጋል ።ፑሉሲች ከቼልሲ በተጨማሪ በሊቨርፑል በጥብቅ ይፈለጋል ። (Evening
Standard)
ለበርካታ ቀናት በዝውውር ዜናዎች ሲነገር የነበረው የስፔናዊው አማካይ ኢብራሂም ዲያዝ ጉዳይ በስተመጨረሻ እልባት ማግኘቱ እየተወዘገበ ነው።የ19 አመቱ አማካይ ምንም እንኳን ፔፕ ጋርዲዮላ በክለቡ እንዲቆይ ቢፈልጉም ወደ ሪያል ማድሪድ መጓዙ ግን አይቀሬ ነው ተብሏል ። (Sun)
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡኒይ ኤምሬ የ27 አመቱ ዌልሳዊ አማካይ አሮን ራምሴ ብቃቱን እያሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰው ክሆሎቱን በማሳደግ ላይ እንዲታትር ተናግረዋል ።ስፔናዊው አሰልጣኝ አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር በኮንትራት ጉዳይ ይነጋገራልም ብለዋል ። (Telegraph)
አርሰናል እና ቶተንሀም በአመቱ መጨረሻ ውሉ የሚጠናቀቀውን እና ከክለቡ ፒ ኤስ ጂ ጋር ንግግር ላይ የሚገኘውን አድናን ራቢዮት ለማዘዋወር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል ።የ23 አመቱ ፈረንሳዊ አማካይ በክለቡ በቂ የመሰለፍ ዕድል ባለማግኘቱ ከፓርክ ደ ፕሪንስ መልቀቅ ይፈልጋል ። (RMC, via Sport)
ብራዚላዊው የጁቬንትስ ተከላካይ አሌክስ ሳንድሮ ስሙ ካልተገለፀ የእንግሊዝ ክለብ አመታዊ €10M በደሞዝ መልክ እንደቀረበለት ተነገረ።የ27 አመቱ ተጨዋች ባሳለፍነው አመት ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል ። (Calciomercato - in Italian)
ቼልሲ፣አርሰናል እና ቶተንሀም የ26 አመቱን ስፔናዊ የሪያል ማድሪድ አማካይ ኢስኮ ለማዘዋወር ፍላጎቱ አላቸው ።ሶስቱ የእንግሊዝ ክለቦች በተደጋጋሚ ሎስብላንኮዎቹ ደጅ እየጠኑ ነው። (Sun)
ጆዜ ሞሪንሆ ፖግባን ተቹ
የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፈረንሳዊውን
አማካይ ፖል ፖግባ ከሳውዝሀምተን ጋር 2ለ2 ከተለያዩ በኃላ
መተቸታቸው አይዘነጋም ።አወዛጋቢው አሰልጣኝ ስሙ በስፋት
ከዝውውር
ዜናዎች ጋር በመያያዝ ያለውን ተጨዋች በድጋሚ 'ቫይረስ'
ሲሉም
ገልፀውታል ።
ፖግባ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር ችግር ውስጥ ከገባ የሰነባበተ ሲሆን
ስሙም በስፋት ከሌሎች ክለቦች ጋር በመያያዝ ላይ እንደሆነ
ይታወቃል ።
(Daily Record)
አዝብሉኬታ በቼልሲ ለተጨማሪ አራት አመታት የሚያቆየውን
ኮንትራት ፈርሟል።ስፔናዊው ተከላካይ በስታንፎርድ ብሪጅ እስከ
2022 ለመቆየት የተስማማው ትናንት ሲሆን በአዲሱ ውሉ
መሰረት በሳምንት £150,000 የሚከፈለውም ይሆናል
።አዝብኬታ በቼልሲ ደጋፊዎች ዘንድ በእጅጉ የሚወደድ ተጨዋች
መሆኑ ይታወቃል ። (Goal)
ሉካ ሞድሪች በሪያል ማድሪድ ቤት የእግር ኳስ ህይወቱን
መጨረስ እና ጫማ መስቀል እንደሚፈልግ ተናገረ።ስሙ በስፋት
ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር በመያያዝ ላይ የሚገኘው
ክሮሺያዊው አማካይ ትናንት በፍራንስ ፉትቦል የሚዘጋጀውን
ባሎንዶር ካሸነፈ በኃላ ነው ይህንን አስተያየት የሰጠው። (Goal)
ጋርዲዮላ ለሮይ ሳኔ በማንቸስተር ሲቲ ቤት ለበርካታ አመታት
ይቆያል ብሎ እንደሚያስብ ተናገረ።ስፓኒያርዱ የመልካም እግር
ኳስ አቀንቃኝ ጀርመናዊው ተጨዋች የኬቨን ደብሮይነን እና
ራሂም ስተርሊንግን ፈለግ በመከተል አዲስ ውል እንደሚፈርምም
ተናግሯል ።
(Goal)
አርሰናል ፣ቶተንሀም፣ኤቨርተን እና ሳውዝሀምተን የራቢ ሌብዙኩን
ተጨዋች ሀንስ ዎልፍ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል
።ኦስትሬያዊው አማካይ በርካታ ከቶተንሀሙ ኤሪክሰን ጋር
አጨዋወቱን የሚያመሳስሉት በUEFA YOUTH LEAGUE
2017 ላይ ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ችሎም ነበር ።
ለክለቡ ደግሞ ባሳለፍነው አመት በአጠቃላይ 45 ጊዜ ተሰልፎ
መጫወት የቻለ ሲሆን 12 ግቦችን ከመረብ ሲያዋህድ ስምንት
ኳሶችን አሲስት አድርጓል ። (Goal)
No comments:
Post a Comment