ማንቸስተር ሲቲ በ125 አመት ታይቶ የማያውቅ ታሪክ አስመዘገበ
የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 38 ንፁ የግብ ልዩነት በማስመዝገብ በ125 አመት ታሪክ ታይቶ የማያውቅ ታሪክ አስመዝግቧል ።
ትናንት ዋትፎርድን 2ለ1 ያሸነፉት ውሃ ሰማያዊዎቹ በአሁኑ ሰዓት ሊጉን በአምስት ነጥብ ልዩነት እየመሩም ነው።
በዚህም ምክንያት በዘንድሮው አመት የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን 45 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን ሰባት ግቦች ብቻ ነው የተቆጠሩበት።
ይህም ማለት 38 ንፁህ ግብ አላቸው ፤ይህ ደግሞ በ125 አመት ታሪክ ታይቶ አያውቅም ።
ከዚህ የተሻለ ሪከርድ አስመዝግቦ የነበረው በ1892-93 ሰንደርላንድ የነበረ ሲሆን በ15 ጨዋታዎች ንፁህ 39 ግቦች ነበሩት ።
No comments:
Post a Comment