ጁቬንትሶች በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ደስተኛ ያልሆነውን እና በጆዜ ሞሪንሆ በተደጋጋሚ በመተቸት ላይ ያለውን ፖል ፖግባን ለማዘዋወር ጥያቄ አቅርበዋል ።የ25 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል ባሳለፍነው አመት በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ 'ቫይረስ' ተብሎ መዘለፉ ይታወሳል ። (Sun)
የ19 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል ወደ ፓሪሰን ዤርመን ከመጓዙ በፊት ከአርሰናል የዝውውር ጥያቄ ቀርቦለት ውድቅ ማድረጉን ተናገረ።ባሳለፍነው የሩሲያ የአለም ዋንጫ አስደናቂ አቋሙን ያሳየው እና የውድድሩ ምርጥ ታዳጊ ተጨዋች ተብሎ የተሸለሙ ምባፔ ሞናኮ ሳለ አርሰናል በተደጋጋሚ ለዝውውር እንደጠየቀው ነው ይፋ ያደረገው ። (France Football via Metro)
ከቀናት በፊት ማርኩዊዝን ያሰናበተው ሳውዝሀምተን አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ጥረት እያደረገ ነው።ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ዛሬ ሳውዝሀምተን ከ ቶተንሀም ከመጫወቱ የቀድሞውን የራቢ ሌብዚክ አሰልጣኝ ራልፍ ሀሰንሁቲ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል ። (Guardian)
ኤቨርተኖች ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት በውሰት ከባርሴሎና አምጥተውት የነበረውን አንድሬ ጎሜዝ በቋሚነት የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ።ምንም እንኳን ባርሴሎና ተጫዋቹን መሸጥ የሚፈልገው በከፍተኛ ዋጋ ቢሆንም የመርሲሳይዱ ክለብ ግን የፖርቹጋላዊውን የ25 አማካይ በክለቡ ደስተኛ መሆን ተከትሎ ዝቅ ባለ ዋጋ ማቆየት ይፈልጋል ።
(Times)
የሊቨርፑሉ ብራዚላዊ አማካይ ፋቢንሆ ምንም እንኳን ስሙ በስፋት ከፓሪሰን ዤርመን ጋር ቢያያዝም ሊቨርፑልን የሚለቅበት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ ተናግሯል ። የ25 አመቱ ተጨዋች በሊቨርፑል ደስተኛ እንደሆነም ተናግሯል ። (UOL, via FourFourTwo)
በሜጀር ሊግ ሶከር LA GALAXY በመጫወት ላይ የሚገኘው የ37 አመቱ አወዛጋቢ ተጨዋች ኢብራሂሞቪች ወደ ቀድሞው ክለቡ ኤሲ ሚላን ለመመለስ በንግግር ላይ ነው።
(Goal)
ቼልሲ በኤሲ ሚላን በጥብቅ የሚፈለገውን ስፔናዊ የባርሴሎና አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ለማዘዋወር ከጣሊያኑ ክለብ ጋር ፉክክር ውስጥ ገብቷል ።የ24 አመቱ ተጨዋች በባርሴሎና በቂ የመሰለፍ ዕድል እየተሰጠው አይደለም ። (Express)
አርሰናል ባየርን ሙኒክን እና ባርሴሎናን በመፎካከር የሊሉን የ23 አመት ዊንገር ኒኮላስ ፔፔ ለማዘዋወር ትንቅንቁን ተቀላቅሏል ።አይቮሪኮስታዊው ተጨዋች በኡናይ ኤምሬ በጥብቅ ይፈለጋል ። (Mercato
365, via Talksport)
ቼሌሲ ዛሬ ለቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ዊንገር ክርስቲያን ፑሉሲች
ይፋዊ የሆነ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል ።ሰማያዊዎቹ
ለአሜሪካዊው ተጨዋች ያለቸው ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም ክለቡ
ዶርትሙንድ ግን ለተጨዋቹ £70M ይፈልጋል ።ፑሉሲች ከቼልሲ
በተጨማሪ በሊቨርፑል በጥብቅ ይፈለጋል ። (Evening
Standard)
ለበርካታ ቀናት በዝውውር ዜናዎች ሲነገር የነበረው የስፔናዊው
አማካይ ኢብራሂም ዲያዝ ጉዳይ በስተመጨረሻ እልባት ማግኘቱ
እየተወዘገበ ነው።የ19 አመቱ አማካይ ምንም እንኳን ፔፕ
ጋርዲዮላ በክለቡ እንዲቆይ ቢፈልጉም ወደ ሪያል ማድሪድ
መጓዙ ግን አይቀሬ ነው ተብሏል ። (Sun)
ማንቸስተር ሲቲ በ125 አመት ታይቶ የማያውቅ ታሪክ
አስመዘገበ
የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 38 ንፁ የግብ
ልዩነት በማስመዝገብ በ125 አመት ታሪክ ታይቶ የማያውቅ
ታሪክ አስመዝግቧል ።
ትናንት ዋትፎርድን 2ለ1 ያሸነፉት ውሃ ሰማያዊዎቹ በአሁኑ ሰዓት
ሊጉን በአምስት ነጥብ ልዩነት እየመሩም ነው።
በዚህም ምክንያት በዘንድሮው አመት የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን
45 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን ሰባት ግቦች ብቻ ነው
የተቆጠሩበት።
ይህም ማለት 38 ንፁህ ግብ አላቸው ፤ይህ ደግሞ በ125
አመት ታሪክ ታይቶ አያውቅም ።
ከዚህ የተሻለ ሪከርድ አስመዝግቦ የነበረው በ1892-93
ሰንደርላንድ የነበረ ሲሆን በ15 ጨዋታዎች ንፁህ 39 ግቦች
ነበሩት ።
No comments:
Post a Comment