ሀዛርድ ወደ ሪያል ማድሪድ ለመጓዝ በግሉ ተስማምቷል
ትናንት እና ዛሬ የወጡ በርካታ የአውሮፓ ሚዲያዎች በተለይ ደግሞ የስፔን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ሀዛርድ ወደ ሪያል ማድሪድ ለመጓዝ በግሉ ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ቤልጄሚያዊው አጥቂ ምንም እንኳን በአዲሱ አሰልጣኝ ማውሩዚዮ ሳሪ ደስተኛ ቢሆንም የተሻለ ስኬትን በተለይ ደግሞ ሻምፒዮንስ ሊግን እና መሰል ታላላቅ ዋንጫዎችን ለማሳካት ወደ ሎስብላንኮዎቹ መሄድን ይፈልጋል ።
ክርስቲያኖ ሮናልዶን ወደ ጁቬንትስ ከሸኘ ወዲህ ከፍተኛ የግብ ችግር የገጠመው ሪያል ማድሪድም የ27 አመቱ የሰማያዊዎቹ ኮከብ ፈላጊ ነው።
(Goal)
No comments:
Post a Comment