Thursday, December 6, 2018

የአርብ ማለዳ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

FOOTBALL GOSSIP : ሀዛርድ ..ኔይማር...ፌኪር...ካቫኒ...ዲ ዮንግ....ናካጂማ...ሄይተን


➡️ሪያል ማድሪድ ከቼልሲው ቤልጄሚያዊ የጨዋታ አቀጣጣይ ኤድን ሀዛርድ ጋር በግል ተነጋግሮ ለማዘዋወር ከስምምነት ላይ ደርሷል ።ሎስብላንኮዎቹ ይህንን ዝውውር በጥር ወር ወይም በክረምቱ ወር የዝውውር መስኮት ለመጨረስ እየሰሩ ነው። (Onda Madrid , via AS)



➡️ብራዚላዊው የአለማችን ውዱ የፓሪሰን ዤርመን ተጨዋች ኔይማር ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጓዝ እንደሚፈልግ ተናገረ ።የ26 አመቱ ተጨዋች ማንቸስተር ዩናይትድን ጨምሮ በሌሎች የእንግሊዝ ክለቦች በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወቃል ። (Goal)



➡️የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የክለብ ብሩዡን አጥቂ ዌስሊ ሞራኤስ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በ£15M የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ።ፊዮረንቲና እና ቫሌንሲያም የ22 አመቱ ብራዚላዊ ፈላጊዎች ናቸው።  (Sun)




➡️የፓሪሰን ዤርመኑ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ቡፎን ከፎር ፎር ቱ ጋር በነበረው ቆይታ ስለ ኤዲንሰን ካቫኒ ተጠይቆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በፍፁም ወደ ናፖሊ ይጓዛል ብሎ እንደማያስብ ተናገረ።የ31 አመቱ ኡራጓዊ ከኔርማር ጋር ባለው እሰጣ እገባ ምክንያት ከክለቡ መልቀቅን እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ይነገራል ። (Tiki Taka, via FourFourTwo)




➡️ፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን ምባፔ ኔዘርላንዳዊው የ21 አመት የአያክስ አማካይ ዲ ዮንግ ወደ ፒ.ኤስ.ጂ መምጣት ከፈለገ ክለቡ በእጅጉ እንደሚደሰት ተናገረ። (France Football )




➡️ቼልሲ ከናፖሊ ጋር በ24 አመቱ አልባኒያዊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ኤል ሰዒድ ሀይሳጅ ጉዳይ ንግግር ጀምሯል ።ማውሩዚዮ ሳሪ በኔፕልሱ ክለብ ሳሉ ከሚወዷቸው ተጨዋቾች አንዱ ሀይሳጅ እንደነበር ይነገራል ። (calcionercati - in Italian )




➡️ኢንተር ሚላን ጣሊያናዊውን የማንቸስተር ዩናይትድ የመስመር ተከላካይ ማትዮ ዳርሚያን በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ይጥራል ።ኢንተር የ29 አመቱን ተጨዋች ባለፈው አመት በውሰት ለመውሰድ መሞከሩ ይታወሳል ። (Gazzetta dello sport - in Italian )




➡️ቀውስ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ £20M የተገመተውን የጋላታሳራይ የመሀል ተከላካይ ኦዛን ካባክ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል ።አርሰናል ፣ሮማ እና ኢንተር ሚላንም የ18 አማቱ ተስፈኛ ተጨዋች ፈላጊዎች ናቸው ።




➡️በአሁኑ ሰዓት በውሰት በቼልሲ ቤት የሚገኘው እና በዋናነት ባለቤቱ ሪያል ማድሪድ የሆነው ክሮሺያዊው አማካይ ማቲዮ ኮቫቺች ወደ ሎስብላንኮዎቹ መመለስ እንደማይፈልግ ተነገረ።ሰማያዊዎቹ የ24 አመቱን ተጨዋች በቋሚነት የማስፈረም ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ቶተንሀምም ከፍተኛ ፍላጎት አለው ። (As)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...