የዕለት እሁድ ምሳ ሰዓት የዝውውር ዜናዎች
◾ሲሞኒ ፋልካኦን በአትሌቲኮ ማስፈረም ይፈልጋል
➡ዲያጎ ኮስታን በጉዳት ያጣው አትሌቲኮ ማድሪድ ከፍተኛ የግብ ማጥቃት ችግር እያጋጠመው በመሆኑ አዲስ አጥቂ ለማስፈረም ገበያ ላይ ማጥናቱን ተያይዞታል ።
Don ballon በዘገባው ዛሬ እንዳተተው ከሆነ ደግሞ ዲያጎ ሲሞኒ በዋናነት የሚፈልገው የቀድሞውን የክለቡ ተጨዋች ራዳሚር ፋልካኦን ነው።ፋልካኦ በፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ በአዲሱ አሰልጣኝ ቴሪ ኦንሪ ስር እምብዛም ደስተኛ እንዳልሆነ ይነገራል ።ኮሎምቢያዊው ኮከብ ወደ ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ የመዘዋወር ዕድሉ ሰፊ ነው ያለው ጋዜጣው የስፔኑ ክለብ ሌላኛውን ኮሎምቢያዊ ሀሜስ ሮድሪጌዝም ለማዘዋወር ይጥራል ብሏል ።
◾አርሰናል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ኦዚልን መሸጥ ይፈልጋል
➡ዛሬ The Sun ባስነበበው ሀተታ አርሰናል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ሜሲት ኦዚልን በ£25M ለመሸጥ አቅዷል ።
መድፈኞቹ ለጀርመናዊው የጨዋታ ቀማሪ የሚከፍሉትን ሳምንታዊ 350,000 ፓውንድ ለመቀነስ ሲሉ ነው ይህንን የሚያደርጉት ብሏል ጋዜጣው ።
የተጨዋቹ ዋነኛው ፈላጊ የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ሲሆን ሌላኛው የጣሊያን ክለብ ጁቬንቱስም ፍላጎት አለው ።
◾ባርሴሎና £200M ለሀሪ ኬን መድቧል
➡ቶተንሀም ቁልፍ ተጨዋቹን እንዲሸጥ ግፊት እየተደረገበት ነው።ባርሴሎና በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ሀሪ ኬንን ለማዘዋወር £200M እንደበጀተ The daily star አስነብቧል ።
የካታላኑ ክለብ አንድ በትልቅ ደረጃ ላይ የሚገኝ አጥቂን የማዘዋወር ፍላጎት ያለው ሲሆን ለዚህ መነሻ የሆነው ደግሞ በክለቡ የሚገኘው አጥቂ ሊውዝ ሱዋሬዝ ዕድሜ 32 መጠጋቱ እና ተተኪውን ማግኘት በመፈለጉ ነው።
አዲሱ ስታዲየሙን በመገንባት ላይ የሚገኘው እና ወጪውን ለማካካስ የሚፈልገው ስፐርስ ተጫዋቹን መሸጥ የሚፈልገው ከ£150M በላይ ነው።
◾ማንቸስተር ሲቲ በዲያዝ የዝውውር ጉዳይ ለመጨረሻ ጊዜ መነጋገር ይፈልጋል
➡ማንቸስተር ሲቲ የ19 አመቱን ስፔናዊ አማካይ በክለቡ ለማቆየት ለመጨረሻ ጊዜ ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋር ሊነጋገር ነው።የ19 አመቱ ስፔናዊ ክለቡ ማንቸስተር ሲቲ በተደጋጋሚ የኮንትራት ማራዘሚያ ቢያቀርብለትም እርሱ ግን ሊቀበል አልቻለም ፤በዋናነት ደግሞ ምክንያቱ ሪያል ማድሪድ የዝውውር ጥያቄ ስላቀረበለት ነው ተብሏል ።ዘገባው የthe sun ነው።
◾ ፒ.ኤስ.ጂ ሀዛርድን ለማዘዋወር የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅሏል
➡የፈረንሳዩ ክለብ ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅሎታል።
ፓሪሰን ዤርመን በሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈለገውን ቤልጄሚያዊ ኮከብ ኤድን ሀዛርድ ለማዘዋወር ነው ፉክክሩን የተቀላቀለው።ሀዛርድ ለወራት ስሙ በስፋት ከሪያል ማድሪድ ጋር በመያያዝ ላይ የቆየ ሲሆን ክለቡ ቼልሲ ተጨማሪ ኮንትራት ቢያቀርብለትም ለመፈረም ግን ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም ።
ሀዛርድ ያለው ኮንትራትም በ2020 የሚያበቃ ይሆናል ዘገባ የmirror ነው።
◾ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲ ዲ ዮንግን ሊያጣ በመሆኑ ተበሳጭቷል
➡ፒ.ኤስ.ጂ የአያክሱን አማካይ ዲ ዮንግ ለማዘዋወር ከጫፍ መድረሱን ተከትሎ ፔፕ ጋርዲዮላ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱን mirror አስነብቧል ።ማንቸስተር ሲቲ ሆላንዳዊውን ታዳጊ ኮከብ ለማዘዋወር እስከ መጨረሻው ጥረት ያደረገ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን ይህ ጥረቱ የከሸፈ ይመስላል ።
አብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ፒ ኤስ ጂ ዝውውሩን እንደጨረሰው እየዘገቡ ነው።
◾ ሊዮኔል ሜሲ በላሊጋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ሁለት
ቅጣት ምት አስቆጠረ
➡️ሊዮኔል ሜሲ ትናንት በስፔን ላሊጋ ካታላን ደርቢ ሁለት ቅጣት
ምቾችን በማስቆጠር በግሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በላሊጋ አንድ
ጨዋታ ሁለት ግብ (ቅጣት ምት) በማስቆጠር አዲስ ሪከርድ
አስመዝግቧል ።
ሜሲ ትናንት ክለቡ ባርሴሎና ኤስፓኞልን 4ለ0 ባሸነፈበት
አስደናቂ እንቅስቃሴን በማድረግ ክለብ የሊጉ መሪ እንዲሆንም
አድርጓል ።
በዚህም መሰረት ሊዮኔል ሜሲ ለተከታታይ 13 ሲዝኖች
በየአመቱ ቢያንስ 10 የቅጣት ምት ግብ በማስቆጠር በላሊጋው
ታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።
ሜሲ በአጠቃላይ በአመቱ እስካሁን ዘጠኝ የቅጣት ምቶችን
በላሊጋው ብቻ ያስቆጠረ ሲሆን ይህም በአውሮፓ ካሉ ምርጥ
አምስት ሊጎች እሱን አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል ።
◾ ማንቸስተር ሲቲ ለአንደር £50M አዘጋጅቷል
➡ማንቸስተር ሲቲ የሮማውን ኮከብ ሴንጊዝ አንደር ለማዘዋወር £50M አቅርቧል። አንደር ከዚህ በኃላ በክለቡ ለተጨማሪ አራት አመታት የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም ዝቅተኛ ተከፋይ ከሚባሉት ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ነው።ከማንቸስተር ሲቲ በተጨማሪ አርሰናል ፣ቶተንሀም እና ቼልሲም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው ።
◾ቶተንሀም፣አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሺፑ ተጨዋች ላይ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል
➡የብሪስቶሉ የግራ መስመር ተከላካይ ሊዮርዲ ኬሊ የእንግሊዝ ክለቦች አይን ውስጥ ገብቷል ።የ21 አመቱ እንግሊዛዊ ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ሳውዝጌትም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጠርቶት ነበር ።
◾ማንቸስተር ዩናይትድ ኩሊባሊን ለማዘዋወር £90M ያስፈልገዋል
➡ማንቸስተር ዩናይትድ የናፖሊውን ድንቅ ተከላካይ ለማዘዋወር £90M መጠየቁን the times አስነብቧል ።ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ቀያይ ሰይጣኖቹ የ27 አመቱን ተከላካይ ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ለድርድር ሰዎችን ወደ ጣሊያንም ልከዋል ።
No comments:
Post a Comment