ሊዮኔል ሜሲ በላሊጋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ሁለት ቅጣት ምት አስቆጠረ
ሊዮኔል ሜሲ ትናንት በስፔን ላሊጋ ካታላን ደርቢ ሁለት ቅጣት ምቾችን በማስቆጠር በግሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በላሊጋ አንድ ጨዋታ ሁለት ግብ (ቅጣት ምት) በማስቆጠር አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል ።
ሜሲ ትናንት ክለቡ ባርሴሎና ኤስፓኞልን 4ለ0 ባሸነፈበት አስደናቂ እንቅስቃሴን በማድረግ ክለብ የሊጉ መሪ እንዲሆንም አድርጓል ።
በዚህም መሰረት ሊዮኔል ሜሲ ለተከታታይ 13 ሲዝኖች በየአመቱ ቢያንስ 10 የቅጣት ምት ግብ በማስቆጠር በላሊጋው ታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።
ሜሲ በአጠቃላይ በአመቱ እስካሁን ዘጠኝ የቅጣት ምቶችን በላሊጋው ብቻ ያስቆጠረ ሲሆን ይህም በአውሮፓ ካሉ ምርጥ አምስት ሊጎች እሱን አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል ።
No comments:
Post a Comment