"ቁጥሮች አይዋሹም -፤ባሎንዶር ለኔ ነበር የሚገባኝ" ሮናልዶ
➡የጁቬንትሱ አጥቂ በዘንድሮው አመት ስድስተኛ ባሎንዶሩን ለማግኘት ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም የቀድሞው የክለብ አጋሩ ሉካ ሞድሪች ማሸነፉ አይዘነጋም ።
ዛሬ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነበረው ቃለ ምልልስም በዚህ ዓመት የነበረው ባሎንዶር ከሞድሪች ይልቅ ለሱ እንደሚገባ ተናግሯል ።
"እኔ ሁልጊዜም በየአመቱ ባሎንዶርን ማሸነፍ ይገባኛል ፤የምሰራው ለዚህ ነህ ምናልባት ካልተሳካ ግን የአለም ፍፃሜ ነው ማለት አይደለም ።ቁጥሮች አይዋሹም ፤ ይህ ማለት ግን ባላሸነፍ እንኳን በጣም ይከፋኛል ማለት አይደለም ።ምርጥ እና ደስተኛ ጓደኞች እንዲሁም ቤተሰቦች አሉኝ ፤አለም ላይ ባሉ ምርጥ ክለቦች ተጫውቻለሁ ፤ይህንን ባለማሸነፌ ቤቴ ሄጄ የማለቅስ ይመስልሃል ?
"እርግጥ ነው ተከፍቻለው፥ነገር ግን ህይወት ይቀጥላል እኔም ጠንክሬ እየሰራው ነው" በማለት ተናግሯል ሮናልዶ።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ በ2018 በ48 ጨዋታዎች 45 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
No comments:
Post a Comment