Monday, December 10, 2018

የዕለተ ማክሰኞ ማለዳ እግር ኳሳዊ መረጃዎች

➡ባርሴሎና በዘንድሮው አመት አስደናቂ እንቅስቃሴ በፕሪሚየር ሊጉ እያደረገ የሚገኘውን የኤቨርተኑን አጥቂ ሪቻርድሰን ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል ።የ21 አመቱ ብራዚላዊ በመርሲሳይዱ ክለብ ሸጋ የሚባል አመትን በማሳለፍ ላይ ይገኛል ። (star)



➡ ቤልጄሚያዊው ኮከብ ኤድን ሀዛርድ በድጋሚ ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር በስፋት መያያዝ ጀምሯል ።ሀዛርድ ስለ ቀጣይ ቆይታው ተጠይቆ ከዚህ በፊት "ሪያል ማድሪድ መሄድ አልፈልግም ብዬ ራሴን ማታለል አልፈልግም "ማለቱ አይዘነጋም ።ቤልጄሚያዊው የ27 አመት የጨዋታ ቀማሪ ትናንት ደግሞ ከቼልሲ ጋር በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ መነጋገር ማቆሙን ተናግሯል ።
(RMC Sport via
Express)



➡የኤሲ ሚላኑ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሊዮናርዶ ክለባቸው የ31 አመቱን ስፔናዊ አማካይ ሴስክ ፋብሪጋዝ ለማዘዋወር ከቼልሲ ጋር ንግግር መጀመሩን ይፋዊ በሆነ መልኩ ገልፀዋል ። (London Evening
Standard)



➡ቶተንሀም በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገውን ሮማንያዊ የFCSB ተጨዋች ዴኒስ ማን ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብቷል ።የቀድሞው የስቴዋ ቡካሬስቱ የ20 አመት አጥቂ ከሁለቱም ክለቦች ጋር በመነጋገር ላይ ነው። (Sun)



➡የፉልሀሙ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራንዮሪ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ሌስተር ሲቲ በሪከርድ ዋጋ ያዘዋወረውን የ30 አመት አልጄሪያዊ አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ወደ ክለባቸው ለማምጣት እየሰሩ ነው።ተጫዋቹን ያስፈረሙት እራሳቸው በሌስተር ሳሉ መሆኑ አይዘነጋም ። (Telegraph)



➡በዘንድሮው አመት አስደናቂ አቋም እያሳየ ባለው ወልቭስ ውስጥ ምርጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው የ21 አመቱን ፖርቹጋላዊ አማካይ ሩበን ዴቪስ ወኪሉ ወደ ጁቬንትስ እንዲጓዝ  እየገፋፋው ነው። (Calciomercato - in Italian)



➡የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ እና እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ እና በአሁኑ ሰዓት BT SPORT ላይ በተንታኝነት እየሰራ የሚገኘው ሪዮ ፈርዲናንድ የ28 አመቱን የማንቸስተር ሲቲ ተከላካይ ዎከር በአሁኑ ሰዓት ምርጥ የሚባል አቋም ላይ የሚገኝ ተጨዋች ነው ሲሉ አሞግሶታል። (independent )



➡የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዠርደን ክሎፕ ስማቸው በስፋት ከናፖሊ ጋር በመያያዙ ስለ ጉዳዩ ሲጠየቁ ወደ ጣሊያን የመሄድ ሀሳብ እንደሌላቸው ተናግረዋል ። (Liverpool Echo)



➡የ34 አመቱ ኔዘርላንዳዊ የባየርን ሙኒክ ዊንገር አሪያን ሮበን ምንም አይነት የዝውውር ጥያቄ ቢቀርብለትም በአመቱ መጨረሻ ራሱን ከእግር ኳስ እንደሚያገል ተናገረ። (goal)




"ቁጥሮች አይዋሹም -፤ባሎንዶር ለኔ ነበር የሚገባኝ" ሮናልዶ
➡የጁቬንትሱ አጥቂ በዘንድሮው አመት ስድስተኛ ባሎንዶሩን
ለማግኘት ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም የቀድሞው የክለብ
አጋሩ ሉካ ሞድሪች ማሸነፉ አይዘነጋም ።
ዛሬ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነበረው ቃለ ምልልስም በዚህ ዓመት
የነበረው ባሎንዶር ከሞድሪች ይልቅ ለሱ እንደሚገባ ተናግሯል

"እኔ ሁልጊዜም በየአመቱ ባሎንዶርን ማሸነፍ ይገባኛል
፤የምሰራው ለዚህ ነህ ምናልባት ካልተሳካ ግን የአለም ፍፃሜ
ነው ማለት አይደለም ።ቁጥሮች አይዋሹም ፤ ይህ ማለት ግን
ባላሸነፍ እንኳን በጣም ይከፋኛል ማለት አይደለም ።ምርጥ እና
ደስተኛ ጓደኞች እንዲሁም ቤተሰቦች አሉኝ ፤አለም ላይ ባሉ
ምርጥ ክለቦች ተጫውቻለሁ ፤ይህንን ባለማሸነፌ ቤቴ ሄጄ
የማለቅስ ይመስልሃል ?
"እርግጥ ነው ተከፍቻለው፥ነገር ግን ህይወት ይቀጥላል እኔም
ጠንክሬ እየሰራው ነው" በማለት ተናግሯል ሮናልዶ።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ በ2018 በ48 ጨዋታዎች 45 ግቦችን
ማስቆጠር ችሏል።



◾ዛሬ በተወዳጁ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃግብር ፡

➡ጋላታሳራይ ከ ፖርቶ - 2:55
➡ሻልከ 04 ከ ሎኮሞቲቭ ሞስኮ - 2:55
➡ክለብ ብሩዥ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ - 5:00
➡ሞናኮ ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ - 5:00
➡ባርሴሎና ከ ቶተንሀም - 5:00
➡ኢንተርሚላን ከ ፒ.ኤስ.ቪ - 5:00
➡ሊቨርፑል ከ ናፖሉ - 5:00
➡ክርቬና ዛቫዳ ከ ፒ.ኤስ.ጂ - 5:00

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...