Wednesday, December 12, 2018

የሀሙስ ማለዳ አዳዲስ ስፖርታዊ ዜናዎች

➡ሪያል ማድሪድ ትናንት በሻምፒዮንስ ሊግ በሜዳው በሲ ኤስ ኬ ሞስኮ 3ለ0 ተሸንፏል ።ሎስብላንኮዎቹ ምንም እንኳን ከምድቡ ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም ውጤቱ ግን ያልተጠበቀ ነበር ።


➡በሌላ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ጁቬንትስም ተሸንፈዋል ።ወደ ስፔን በማቅናት በሜስታያ ቫሌንሲያን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 2ለ1 ሲሸነፍ ጁቬንትስም በያንግ ቦይስ በተመሳሳይ ውጤት 2ለ1 ተሸንፏል ።


➡ስፔናዊው የቼልሲ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ስሙ ከባርሴሎና ጋር መያያዝ ጀምሯል።የ26 አመቱ አጥቂ ህይወት በሀገረ እንግሊዝ እምብዛም አልጋ በአልጋ አልሆነለችለትም። (RAC1 - in
Spanish)


➡ቶተንሀም ለሪያል ማድሪድ እና ማንቸስተር ዪናይትድ  ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆን በጥር ወር የዝውውር መስኮት አሳልፎ እንደማይሰጥ አሳውቋል ።ስፐርስ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ ምናልባትም በአመቱ መጨረሻ ልትለቅ ትችላለች ። (Guardian)



➡ጁቬንትስ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ፈረንሳዊውን የ25 አማካይ ፖል ፖግባ ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማዘዋወር £80M ያቀረበ ሲሆን ይህ ዝውውር የማይሳካ ከሆነ አይኑን ወደ ሪያል ማድሪዱ ስፔናዊ ኮከብ ኢስኮ የሚያዞር ይሆናል ። (Tuttosport - in Italian)


➡አርሰናል ተከላካዮችን በማፈላለግ ላይ ይገኛል ።መድፈኞቹ በዋናነት ሶስት ተጨዋቾችን ዕቅዳቸው ውስጥ አስገብተዋል ።አይቮሪ ኮስታዊው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ኤሪክ ቤሊ፣የቼልሲው እንግሊዛዊ ተከላካይ ጋሪ ካሂል እና የሪያል ቫላዶሊዱ ስፔናዊ ተከላካይ ፈርናንዶ ካሌሮ ናቸው ተጨዋቾቹ።



➡ስፔናዊው የ33 አመት የቶተንሀም ተከላካይ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ ወደ ቀድሞው ክለቡ አትሌቲኮ ቢልባኦ መመለስ እንደሚፈልግ ተናግሯል ። (Evening Standard)



➡አይቮሪኮስታዊው የ35 አመት ተጨዋች ያያ ቱሬ አሁንም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጫወት እንደሚችል ተናግሯል ።ቱሬ በግሪኩ ክለብ ኦሎምፒያኮስ ለሶስት ወራት ከተጫወተ በኃላ በስምምነት የተሰናበተ ሲሆን በዚህ ሰዓት በቻይና እና ሜጀር ሊግ ሶከር ክለቦች ይፈለጋል ። (Sky Sports)


➡ ሪያል ማድሪድ የ20 አመቱን የሪቨር ፕሌት አማካይ ኤግዙዌል ፓላሲሎስ ለማዘዋወር ከስምምነት ላይ ደርሷል ።የ20 አመቱ አርጀንቲናዊ ከክለቦች ለአለም ዋንጫ በኃላ ሎስብላንኮዎቹን የሚቀላቀል ይሆናል ። (Marca - in Spanish)


➡ስፔናዊው የ31 አመት የባርሴሎና ተከላካይ ዤራርድ ፒኬ ከክለቡ ጋር በድርድር ላይ መሆኑ ተገለፀ።ተጨዋቹ ከክለቡ ሊለቅ የሚችልበት ዕድል አለ ተብሏል ። (Diari d'Andorra - in
Spanish)



➡ ኢንተር ሚላን ከአውሮፓ ሻምጊዮንስ ሊግ ማሰናበቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ የ25 አመቱን አርጀንቲናዊ አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል ። (As)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...