"ሪያል ማድሪድ ክርስቲያኖን ናፍቆታል" ማርሴሎ
የሪያል ማድሪዱ የግራ መስመር ተከላካይ ማርሴሎ ክለቡ ክርስቲያኖን እንደናፈቀው ተናግሮ የሚጠበቅ መሆኑንም አክሏል ።
ከዘጠኝ ስኬታማ አመታት በኃላ ሮናልዶ ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት ወደ ጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ መጓዙ ያልተጠበቀ ነበር ።
ማድሪድም ተጫዋቹን ካጣ ወዲህ በሊጉ በእጅጉ እየተቸገረ ሲሆን ያልተጠበቁ ሽንፈቶችን እያስተናገደ አሁን በአሰልጣኝ ሳንቲያጎ ሶላሬ እየተመራ ከባርሴሎና ጋር የአምስት ነጥብ ልዩነትም አለበት።
ማርሴሎም ሪያል ማድሪድ "የአለማችንን ምርጡን ተጨዋች" ቢያጣም በአውሮፓ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ይቀጥላል ብሏል ።
"እሱ ምርጥ ተጨዋች የቡድን አጋሬ ምርጥ ጓደኛዬም ነበር ፤ከራሞስ እና ሞድሪችም ጋር እንዲሁ ።የአለማችን ምርጡ ተጨዋች ከክለብህ ሲወጣ መናፈቅህ የሚጠበቅ ነው።ይህ ማለት ግኝ እኛ በየቦታው ምርጥ ተጨዊቾች የሉንም ማለት አይደለም ።ሁሉም ክለብ ክርስቲያኖ ቢኖረው ደስተኛ ይሆናል ፤በዚሁሉ ነገር ውስጥም ቢሆን ተጨዋቾች ቢሄዱም ቢመጡም ማድሪድ ግን ማድሪድ ሆኖ ይቀጥላል ። " ብሏል ማርሴሎ ።
ሮናልዶ ጁቬንትስን ከተቀላቀለ ወዲህ በ20 ጨዋታዎች 11 ግቦችን አስቆጥሯል ።
No comments:
Post a Comment