Saturday, December 15, 2018

የቅዳሜ ምሳ ሰዓት አዳዲስ እግር ኳሳዊ ዜናዎች

➡አርሰናል ሱዋሬስን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።መድፈኞቹ የባርሴሎናውን አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ለማዘዋወር እየሰራ መሆኑን The independent አስነብቧል ።ሱዋሬዝ በባርሴሎና በመጀመሪያ ተመራጭ ተሰላፊነት ለመጫወት ጥረት እያደረገ ቢሆንም ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ግን ዕድሉን ሊሰጡት አልቻሉም ።በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ተጫዋቹን ለማዘዋወር እየሰሩ ሲሆን ባርሴሎና ለተጨዋቾቹ የሚፈልገው ዋጋ €14M ነው።



➡ሌስተር ሲቲ የቀድሞውን የሞናኮ አሰልጣኝ ሊዮናርዶ ዣርዲም በዋና አሰልጣኝነት ለመቅጠር እየሰራ መሆኑን Le10Sport ዘግቧል ።ዣርዲም በአመቱ መጀመሪያ አካባቢ ከሞናኮ የተሰናበተ ቢሆንም በክለቡ ስኬታማ ጊዜን ማሳለፉ አይዘነጋም ።ቀበሮዎቹ ምንም እንኳን በሊጉ ሰንጠረዥ ዘጠኛ ደረጃ ላይ ቢገኙም አዲስ አሰልጣኝ ስለመቅጠር እያሰቡ ነው።



➡ፉልሀም ጋሪ ካሂልን ከቼልሲ በጥር ወር የዝውውር  መስኮት ለማዘዋወር እየሰራ ነው ሲል West
London Sport አስነበበ።እንግሊዛዊው ተከላካይ በማውሩዚዮ ሳሪ ስር የቋሚ ተሰላፊነት ዕድል የተነፈገው ሲሆን በዚህ አመት አንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ብቻ ነው ለሰማያዊዎቹ ማድረግ የቻለው።ቼልሲ የ32 አመቱን ተጨዋች ማሰናበትም ይፈልጋል ።



➡ጁቬንትስ ፒያካን በ ቼሳ ከፊዮረንቲና ጋር መቀያየር ቢፈልግም ፊዮረንቲና ደስተኛ እንዳልሆነ Calciomercato አስነብቧል ።



➡ፍላሚንጎ ጋቢሬል ባርቦሳ ለማዘዋወር ከወኪሎቹ ጋር ድርድር ላይ መሆኑን ESPN Brazil ገልጿል ።ባርቦሳ ከኢንተር ሚላን በውሰት ወደ ሳንቶስ ከተጓዘ ወዲህ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል ።

የ22 አመቱ ብራዚላዊ አጥቂ ባርቦሳ በሌሎች የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦችም ይፈለጋል ።



➡ፖቼቲንሆ ከወር በኃላ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ክለቡ አዳዲስ ተጨዋቾችን እንደማያስፈርም ተናገረ ።ስፐርስ ባለፈው የዝውውር መስኮትም አንድም ተጨዋች ያላዘዋወረች ቢሆንም በዚህ ሰዓት በሊጉ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ።



➡ኔይማር በፒ.ኤስ.ጂ የመቆየት ዕድሉ ሰፊ ነው።ብራዚላዊው ተጨዋች ኔይማር ምንም እንኳን ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ቢያያዝም በፓሪሱ ክለብ የመቆየት ዕድሉ ሰፊ መሆኑን le10sport አስነብቧል ።ኔይማር በክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ መሆኑ ይታወቃል ።



➡በርንማውዝ እና ዌስት ሀም የቼልሲውን አማካይ ሩበን ሎፍተስቺክ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በውሰት ለመውሰድ ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን sun ዘግቧል ።ሁለቱም ክለቦች ጥያቄያቸውን ለለንደኑ ክለብ ማቅረባቸውም ተገልጿል ።



➡ቶተንሀም እና አርሰናል የሆፈንየሙን አማካይ ፍሎሪያን ጊርሊቲች ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳላቸው bild አስነብቧል ።ኦስትሪያዊው ተጨዋች በጀርመኑክለብ እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም ክለቦች ግን የውል ማፍረሻውን ለመክፈል ዝግጁ ናቸው ።ወኪሉም ከሳምንት በፊት ወደ እንግሊዝ መጓዙ ታውቋል።



➡ቼልሲ የበርንማውዙን ዊልሰን ለማዘዋወር እየሰራ ነው ሲል Express አስነብቧል ።ሰማያዊዎቹ £30M ያቀረቡ ሲሆን ማውሩዚዮ ሳሪ ተጫዋቹን በማዘዋወር በሞራታ እና ዢሩ የሚመራውን የአጥቂ ክፍል ማጠናከር ይፈልጋሉ ።ዊልሰን በዚህ ሰዓት በጉዳት ላይ የሚገኝ ሲሆን በርንማውዝ ተጫዋቹን እንደማይሸጥ አስታውቋል ።



➡ኢንተር ሞድሪችን እና ኮንቴን ወደ ክለቡ ለማስኮብለል እየሰራ ነው።
ኢንተር ሚላን በአመቱ ሽልማቶችን በሙሉ ጠራርጎ የወሰደውን ሉካ ሞድሪች እና አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን ወደ ሳን ሴሮ ለማምጣት እየሰራ መሆኑን mirror አስነብቧል ።
የክለቡ አዲሱ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ቤፔ ማሮታ በጁቬንትስ ሳለ ከኮንቴ ጋር በጋራ መስራቱ ይታወሳል ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...