Wednesday, December 12, 2018

የዕለተ ረቡዕ ምሽት አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

➡ ማንቸስተር ሲቲ ለሳውል ኒጉዌዝ ያቀርባል የተባለው ሪከርድ ዋጋ እውነት አይደለም ሲል ፔፕ ጋርዲዮላ አስተባበለ ።
ከስፔን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ማንቸስተር ሲቲ የተጫዋቹን የውል ማፍረሻ €150M ለመክፈል ጥያቄ አቅርቧል ።ውሃ ሰማያዊዎቹ ሳውልን በማምጣት የፈርናንዲንሆ የረዥም ጊዜ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋል ። [Goal]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ ሊቨርፑል የቦሩሲያ ሞንቼግላድባሁን አማካይ ቶርገን ሀዛርድ ለማዘዋወር ፍላጎት አለው ።የኤድን ሀዛርድ ታናሽ ወንድም የሆነው ቶርገን ሀዛርድ በዘንድሮው አመት በጀርመኑ ክለብ አስደናቂ አመትን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን በአስራ አምስት ጨዋታዎች 10 ግቦችን ሲያስቆጥር 5 ኳስ አሲስት አድርጓል ። [Liga Financial ]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ዲሚትሪ ቤርባቶቭ ዩናይትድ የሌስተር ሲቲውን ተከላካይ ሀሪ ማጉዌር ማዘዋወር እንዳለበት ተናገረ።ቤርባቶቭ ከ BT SPORTS ጋር በነበረው ቆይታ ማጉዌር በአለም ዋንጫው በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ አስደናቂ ጊዜን እንዳሳለፈ እና በቡድን ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ መፍጠር እንደሚችል ተናግሯል ። [BT SPORTS ]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ባርሴሎና ራኪቲችን እንደማይሸጥ አሳወቀ።የካታላኑ ክለብ ይህንን ያለው ክሮሺያዊው ተጨዋች ስሙ ከዝውውር ጋር በተለይ ደግሞ ከፈረንሳዩ ከበርቴ ክለብ ፓሪሰን ዤርመን ጋር በስፋት መያያዙን መሰረት በማድረግ ነው። [Mundo Deportivo]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ዌስትሀም የክለቡ ታማኝ ተጨዋች የሆነውን እና ሌጀንዳቸውን ማርክ ኖብል እስከ 2021 የሚያቆየውን ኮንትራት አስፈርመውታል። [West Ham United]
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

➡የቶተንሀሙ አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ ወደ ቀድሞው ክለቡ አትሌቲኮ ቢልባኦ መመለስ ይፈልጋል ።ተጨዋቹ የሀሪ ኬን ምርጥ ብቃት ላይ መገኘት ተከትሎ የቋሚ ተሰላፊነትን ዕድል ሊያገኝ አልቻለም ።ከ cadera SER ጋር በነበረው ቆይታም ወደ አትሌቲ መመለስ እፈልጋለሁ ሲል ተናግሯል ። [cadera SER]
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ አርሰናል ቤሊ እና ካሂልን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።መድፈኞቹ ሮብ ሆልዲንግ መጎዳቱን ተከትሎ የሱን ምትክ በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ ።
ESPN እንደዘገበው ከሆነ መድፈኞቹ የማንቸስተር ዩናይትዱን ኤሪክ ቤሊ እና የቼልሲውን ጋሪ ካሂል ማዘዋወር የሚፈልጉት በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው። [ESPN]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ዩናይትድ የቦርዶውን ፓብሎ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ቀውስ ላይ የሚገኙት ቀያይ ሰይጣኖቹ ብራዚላዊውን የ27 አመት ተከላካይ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ በማምጣት የሚቆጠርባቸውን የግብ መጠን የመቀነስ አላማ አላቸው ። [fox sports]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ኒውካስትል የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ለማዘዋወር ካሰባቸው ተጨዋቾች አንዱ የቤኔፊካው አማካይ አንድሬስ ሳማሪስ አንዱ ነው።
ኒውካስትል ፖርቹጋላዊውን ተጨዋች ባሳለፍነው ክረምትም ለማዘዋወር ሞክሮ በሂሳብ ምክንያት ባለመስማማት አልተሳካለትም ነበር ። [The mirror ]
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡ አትሌቲኮ ማድሪድ ዲያኮ ኮስታን የሚሸጥ ከሆነ ኤዲንሰን ካቫኒን ማስፈረም ይፈልጋል ።ኮስታ በቻይና ክለቦች በጥብቅ እየተፈለገ መሆኑን ተከትሎ ሲሞኒ ተጨዋቹ የሚሸጥ ከሆነ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ እንዲመጣለት ይፈልጋል ። [Le10Sport]

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...