Tuesday, December 11, 2018

የዕለተ ረቡዕ ከሰዓት አዳዲስ ስፖርታዊ ዜናዎች

➡ትናንት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እጅግ በጣም ተጠባቂ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን ደረጃ ቀያሪ የሆኑ ውጤቶች ተመዝግበው አንዳንድ ተጠባቂ ክለቦች ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፉ ቀርተዋል ።
በምድብ ሁለት በኑካም ፕ ባርሴሎና ከ ቶተንሀም ያደረጉት ጨዋታ አንዱ ነበር ።ይህ ጨዋታ 1ለ1 ያለቀ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ኢንተር ሚላን ከውድድሩ ተሰናብቷል ።

➡ በሌላኛው ምድብ ሶስት ደግሞ ሊቨርፑል በአንፊልድ ናፖሊን አስተናግዶ በሙሀመድ ሳላህ ብቸኛ ግን ማሸነፍ ችሏል። እዚሁ ምድብ ውስጥ ፒ.ኤስ.ጂ ዝቬዝዳን 4ለ1 በማሸነፍ የምድቡ መሪ በመሆን አጠናቋል።በጨዋታው ኔይማር ፣ካቫኒ፣ምባፔ እና ማርኪኒሆስ  ግቦችን አስቆጥረዋል ። ሊቨርፑል ሁለተኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን አሳዛኝ በሆነ መልኩ ናፖሊ ከውድድሩ ተሰናብቷል ።

የቀያዮቹ አሰልጣኝ ዠርደን ክሎፕ ከጨዋታው በኃላ ግብ ጠባቂያቸው አሊሰንን በእጅጉ አመስግነዋል ።


➡ሉካስ ቶሬራ በአርሰናል ደጋፊዎች የህዳር ወር ምርጡ ተጨዋች ተብሏል ።ኡራጓዊው አማካይ በመድፈኞቹ ቤት እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ደጋፊዎች በእጅጉ ደስተኛ ናቸው ።


➡ ኤሲ ሚላን የቀድሞውን ኮከቡን ዝላታን ኢብራሂሞቪችን ለማዘዋወር ያደረገው ጥረት በመክሸፉ አይኑን ወደ ሌላ ተጨዋች አዙሯል ።ሚላን በአሁኑ ሰዓት በጥብቅ ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች ውስጥ የ21 አመቱ የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ መሆኑም ታውቋል። (Gazzetta dello sport)



➡ቤልጄሚያዊው የ31 አመት ተከላካይ ቬንሰንት ኮምፓኒ ባርሴሎና በጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊያዘዋውራቸው ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች አንዱ ነው። (sun)



➡ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ፖል ፖግባ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ከቋሚ አሰላለፍ ውጪ መሆኑ ያልጠበቀው እና ያስከፋው መሆኑ ተነግሯል ።ዛሬ በሻምፒዮንስ ሊግ በሜስታያ ማንቸስተር ዩናይትድ ቫሌንሲያን ሲገጥም ግን እንደሚሰለፍ ጆዜ ሞሪንሆ ተናግረዋል ። (Guardian)


➡ቶተንሀም የሪያል ማድሪዱን ታዳጊ ኮከብ ማርኮ አሴንሲዮ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል ።ስፐርስ የ22 አመቱን ስፓኒያርድ ለማግኘት በርካታ ጥረት ታደርጋለችም ተብሏል ። (Marca - via Mirror)


➡ቼልሲ በባርሴሎና እምብዛም የመሰለፍ ዕድል እየተሰጠው ያልሆነውን እና በበርካታ ክለቦች የሚፈለገውን የ24 አመት አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ለማዘዋወር ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ሰማያዊዎቹ ሴስክ ፋብሪጋዝን መልቀቃቸው አይቀሬ መሆኑን ተከትሎ ነው እዚህ ዝውውር ላይ ያተኮሩት ። (Mirror)


◾ዛሬ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃግብር ፡
➡ሪያል ማድሪድ ከ ሲኤስኬ ሞስኮ - 2:55
➡ቪክቶሪያ ፕሌዝን ከ ሮማ - 2:55
➡አያክስ ከ ባየርን ሙኒክ - 5:00
➡ቤኔፊካ ከ ኤኢኬ አቴንስ - 5:00
➡ሻካታር ዶኔስክ ከ ሊዮን - 5:00
➡ማንቸስተር ሲቲ ከ ሆፈንየም - 5:00
➡ያንግ ቦይስ ከ ጁቬንትስ - 5:00
➡ቫሌንሲያ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ - 5:00

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...