Friday, December 28, 2018

የአርብ ምሽት አዳዲስ እግር ኳሳዊ ዜናዎች

•የፍላሚንጎውን አማካይ  ሬይነር ካርቫልሆን ለማዘዋወር ማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን The sun አስነብቧል ።የ16 አመቱ ተጨዋች በብራዚሉ ክለብ አካዳሚ ውስጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ጁቬንቱስ እና ሮማም አይናቸውን ጥለውበታል።



•የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሪያል ማድሪዱን ግብ ጠባቂ ኬለር ናቫስ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳላቸው  Ok Diario አስነብቧል ።ኮስታሪካዊው ግብ ጠባቂ ቲቦዉት ኮርቶዋ ከቼልሲ ከተዘዋወረ በኃላ ቋሚ ተሰላፊ መሆን አልቻለም ።


•ውሉ በ2020 የሚያበቃው ሉካ ሞድሪች ሪያል ማድሪድ ያቀረበለትን አዲስ ኮንትራት ውድቅ ማድረጉን As አስነብቧል ።የ2018ቱን የባሎንዶር አሸናፊ በዋነኛነት ኢንተር ሚላን ይፈልገዋል።



•"ማንቸስተር ዩናይትድ ቡድኑን ማዋቀር የሚፈልገው በምርጡ ተጨዋች ፖግባ
ዙሪያ ነው" ሶልሻየር
አዲሱ የቀያይ ሰይጥኖቹ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶልሻየር በፖል ፖግባ ዙሪያ ቡድኑን
ማዋቀር እንደሚፈልግ ተናገረ ።
ፈረንሳዊው አማካይ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን
በመጀመርያዎቹ ሁለት ጨዋታዎችም ሁለት ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ሁለት ኳስ
ደግሞ ለግብ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ፖግባ ምንም እንኳን በቀድሞው አሰልጣኝ ሞሪንሆ ስር ወጥ ብቃት ባያሳይም
ሶልሻየር ግን የ25 አመቱ አማካይ በኦልድ ትራፎርድ ተጽዕኖ
እንደሚፈጥር ተናግሯል ።


"ፖግባ ትልቅ ተጨዋች ነው ብዬ አስባለሁ ።እሱ አለም ላይ ካሉ ጥቂት ምርጥ
ተጨዋቾች አንዱ ነው።በተለይ በማጥቃት ሂደት ላይ ድንቅ ነው።እኛ ቡድናችንን
በሱ ዙሪያ ማዋቀር እንፈልጋለን ነገር ግን በስኳዳችን ውስጥ በርካታ ምርጥ
ተጨዋቾች አሉ።" ብሏል ሶልሻየር።



•ፓሪሰን ዤርመን አሮን ራምሴን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር
ከአርሰናል ጋር ንግግር ጀምሯል።ዌልሳዊው አማካይ በአመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ
የሚያበቃ በመሆኑ በጥር ወር የዝውውር መስኮት አርሰናል ተጨዋቹን መሸጡ
አይቀሬ ነው። የፈረንሳዩ ክለብ ለተጨዋቹ £9M ያቀረበ ሲሆን ባየርን ሙኒክ እና
ጁቬንቱስም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(L'Equipe - in French)



•በጊዜያዊነት ኦሊገነር ሶልሻየርን የሾመው ማንችስተር ዩናይትድ
መጨረሻ የጁቬንትሱን አሰልጣኝ ማክሲሚሊያኖ አሌግሬ በአሰልጣኝነት
የመቅጠር ዕቅድ አለው።
(ESPN)


•ቶተንሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ይልቅ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ
ፖቼቲንሆን በጥብቅ እንደሚፈልግ ያምናል።
(Telegraph)



•የማንቸስተር ዩናይትዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢድ ዉድ ዋርድ በጥር ወር
የዝውውር መስኮትም ይሁን በቀጣዩ ክረምት የዝውውር መስኮት ፖል ፖግባን
የመሸጥ ፍላጎቱ የላቸውም ።የ25 አመቱ ፈረንሳዊ አማካይ በተለይ በጁቬንትስ
እና ባርሴሎና በጥብቅ ይፈለጋል።
(Telegraph)



•ኤድን ሀዛርድ አሁንም ከቼልሲ ጋር በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ለመነጋገር ፈቃደኛ
አይደለም ።የ27 አመቱ ቤልጄሚያዊ ውሉ ክረምት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን
በሪያል ማድሪድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(Sun)



•ዌስት ሀም ፍሪ ኤጀንት ለሆነው የቀድሞው የአርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ
ተጨዋች ሳሚር ናስሪ የዝውውር ጥያቄ ያቀረበለት ሲሆን ሳምንታዊ £80,000
ደሞዝም አሰናድቶለታል።
(Mirror)



•በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘው የ31 አመቱ አርጀንቲናዊ ጎንዛሎ ሂጎይን ወደ
ቼልሲ ለመዘዋወር ይፈልጋል።የተጨዋቹ ባለቤት  ለመሸጥ ፈቃደኛ
ነው።
(Sportmediaset - in Italian)



፨ሪያል ማድሪድ የሪያል ቤቲሱን ፉል ባክ ጁኒየር ፊርፖ የማዘዋወር ፍላጎት
አለው።ሎስብላንኮዎቹ የ22 አመቱን ተጨዋች የረዥም ጊዜ የማርሴሎ ተተኪ
ማድረግ ይፈልጋሉ።
(AS)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...