°ቼልሲ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን የአጥቂ አማካይ ክርስቲያን ፑሉሲች በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ለማዛዋወር £45M አሰናድቷል።የጀርመኑ ክለብ ግን የሌሎችን ክለቦች ፍላጎት በመመልከት አሜሪካዊውን ተጨዋች በተሻለ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል።
(ESPN)
°የኒውካስትሉ አሰልጣኝ ራፋ ቤኒቴዝ የሊድስ ዩናይትዱን አጥቂ ኬማር ሩፌ ለማዛወር አቅደዋል።ቤኒቴዝ ተጨዋቹን ማዘዋወር የሚፋልጉት በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው።
(Sunday Mirror)
°አዲሱ የማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶልሻየር ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሄያ እና ፈረንሳዊውን አንቶኒዮ ማርሻል አዲስ ኮንትራት እንዲፈርሙለት ይፈልጋል።ለማንችስተር ዩናይትድ የበላይ አመራሮችም አሳውቋቸዋል።
(Mail on Sunday)
°ጣሊያናዊው የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ማቲዮ ዳርሚያን በሴሪያዎቹ ክለቦች ኢንተር ሚላን እና ላዚዮ ይፋለጋል።
(Calciomercato)
°አርሰናል በቶተንሀም በጥብቅ የሚፈለገውን የኖርዊች ሲቲውን የ18 አመት ታዳጊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ማክስ አሮንስ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል።
(Sunday Mirror)
°ሊቨርፑል ቱርካዊውን የ19 አመት የአጥቂ አማካይ አብዱልቃድር ኡመር የማስፈረም ፍላጎት አለው።ሮማ እና ማንችስተር ሲቲም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸዉ ።
(Fotomac, via Star on Sunday)
°የ33 አመቱ የቶተንሀም አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ለመዘዋወር በግሉ ከስምምነት ላይ ደርሷል።
(Turkish outlet Star, via Sun on
Sunday)
ቁጥራዊ እውነታዎች
⬅️ሮበርቶ ፈርሚንሆ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች መሀከል ያለው ልዩነት 90 ሰከንድ ብቻ ነው።
➡️ሮበርቶ ፈርሚንሆ በፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ላይ 8 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፤ ሮቢ ፎለር በ9 ግቦች በታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች ነው።
➡️ሳዲዮ ማኔ የሊቨርፑልን ማሊያ ለብሶ አርሰናል ላይ 4 ግቦችን አስቆጥሯል ፤ በግሉ ከየትኛውም ክለብ በላይ መድፈኞቹ ላይ በርካታ ግብ አስቆጥሯል ።
➡️አርሰናል በፕሪሚሪየር ሊግ በአጠቃላይ በመጀመርያው አጋማሽ 4 ግብ ሲቆጠርበት ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ነው፤ ሁለት ጊዜ በሊቨርፑል (2001 በማንችስተር ዩናይትድ ፣2014 በቼልሲ)
➡️የሮበርቶ ፈርሚንሆ ሀት ሪክ በሁለቱ ክለቦች ታሪክ ስድስተኛ ሀትሪክ ነው።
➡️ሙሀመድ ሳላህ በአንድ ጨዋታ ግብ ሲያስቆጥር እና አሲስት ሲያደርግ ከባለፈው አመት ጀምሮ ለ10ኛ ጊዜ ነው።በአውሮፓ አምስቱ ታላቅ ሊጎች የሚበልጠው ኔይማር በ11 ጨዋታዎች ነው።
➡️ሮበርቶ ፈርሚንሆ በፕሪሚየር ሊግ ከሮቢንሆ እና አፎንሶ አልቬዝ በኃላ ሀትሪክ የሰራ በሶስተኛው ብራዚላዊ ሆኗል።
No comments:
Post a Comment