Friday, December 28, 2018

ሶልሻየር በፖግባ ዙሪያ ቡድኑን መገንባት ይፈልጋል

"ማንቸስተር ዩናይትድ ቡድኑን ማዋቀር የሚፈልገው በምርጡ ተጨዋች ፖግባ ዙሪያ ነው" ሶልሻየር

አዲሱ የቀያይ ሰይጥኖቹ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶልሻየር በፖል ፖግባ ዙሪያ ቡድኑን ማዋቀር እንደሚፈልግ ተናገረ ።
ፈረንሳዊው አማካይ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን በመጀመርያዎቹ ሁለት ጨዋታዎችም ሁለት ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ሁለት ኳስ ደግሞ ለግብ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ፖግባ ምንም እንኳን በቀድሞው አሰልጣኝ ሞሪንሆ ስር ወጥ ብቃት ባያሳይም ሶልሻየር ግን የ25 አመቱ አማካይ በኦልድ ትራፎርድ ተጽዕኖ
 እንደሚፈጥር ተናግሯል ።
ፖግባ ትልቅ ተጨዋች ነው ብዬ አስባለሁ ።እሱ አለም ላይ ካሉ ጥቂት ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው።በተለይ በማጥቃት ሂደት ላይ ድንቅ ነው።እኛ ቡድናችንን በሱ ዙሪያ ማዋቀር እንፈልጋለን ነገር ግን በስኳዳችን ውስጥ በርካታ ምርጥ ተጨዋቾች አሉ።



No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...