•ፓሪሰን ዤርመን አሮን ራምሴን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ከአርሰናል ጋር ንግግር ጀምሯል።ዌልሳዊው አማካይ በአመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ የሚያበቃ በመሆኑ በጥር ወር የዝውውር መስኮት አርሰናል ተጨዋቹን መሸጡ አይቀሬ ነው። የፈረንሳዩ ክለብ ለተጨዋቹ £9M ያቀረበ ሲሆን ባየርን ሙኒክ እና ጁቬንቱስም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(L'Equipe - in French)
•በጊዜያዊነት ኦሊገነር ሶልሻየርን የሾመው ማንችስተር ዩናይትድ በአመቱ መጨረሻ የጁቬንትሱን አሰልጣኝ ማክሲሚሊያኖ አሌግሬ በአሰልጣኝነት የመቅጠር ዕቅድ አለው።
(ESPN)
•ቶተንሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ይልቅ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲንሆን በጥብቅ እንደሚፈልግ ያምናል።
(Telegraph)
•የማንቸስተር ዩናይትዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢድ ዉድ ዋርድ በጥር ወር የዝውውር መስኮትም ይሁን በቀጣዩ ክረምት የዝውውር መስኮት ፖል ፖግባን የመሸጥ ፍላጎቱ የላቸውም ።የ25 አመቱ ፈረንሳዊ አማካይ በተለይ በጁቬንትስ እና ባርሴሎና በጥብቅ ይፈለጋል።
(Telegraph)
•ኤድን ሀዛርድ አሁንም ከቼልሲ ጋር በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደለም ።የ27 አመቱ ቤልጄሚያዊ ውሉ ክረምት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በሪያል ማድሪድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(Sun)
•ዌስት ሀም ፍሪ ኤጀንት ለሆነው የቀድሞው የአርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ሳሚር ናስሪ የዝውውር ጥያቄ ያቀረበለት ሲሆን ሳምንታዊ £80,000 ደሞዝም አሰናድቶለታል።
(Mirror)
•በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘው የ31 አመቱ አርጀንቲናዊ ጎንዛሎ ሂጎይን ወደ ቼልሲ ለመዘዋወር ይፈልጋል።የተጨዋቹ ባለቤት ጁቬንትስም ለመሸጥ ፈቃደኛ ነው።
(Sportmediaset - in Italian)
፨ሪያል ማድሪድ የሪያል ቤቲሱን ፉል ባክ ጁኒየር ፊርፖ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።ሎስብላንኮዎቹ የ22 አመቱን ተጨዋች የረዥም ጊዜ የማርሴሎ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋሉ።
(AS)
No comments:
Post a Comment