Thursday, December 27, 2018

የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


•ሪያል ማድሪድ ለረዥም ጊዜ ሲፈልገው የቆየውን ቤልጄሚያዊውን የ27 አመት አጥቂ ኤድን ሀዛርድ ለማዘዋወር አዲስ ጥያቄ አቅርቧል ።ሎስብላንኮዎቹ የ26 አመቱን ኢስኮ እና በውሰት ስታንፎርድ ብሪጅ የሚገኘውን ማቲዮ ኮቫቺች ለቼልሲ በመስጠት ነው ሀዛርድን ለማምጣት ጥያቄ ያቀረቡት።
(Onda Cero, via
Metro)



•ጁቬንቱስ በማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ በጥብቅ እየተፈለገ ያለውን የ28 አመቱን ብራዚላዊ ዳግላስ ኮስታ እንደማይሸጥ ተናገረ ።ሁለቱ የማንችስተር ክለቦች ተጨዋቹን ማዘዋወር የሚፈልጉት በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው።
(Calciomercato)



•ዌስት ሀም የ31 አመቱን ቺሊያዊውን የተከላካይ አማካይ ጋሪ ሜደል ለማዘዋወር £6.5M ያቀረበ ቢሆንም የተጨዋቹ ባለቤት ቤስኪታሽ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል ።
(Talksport)



•ኮንትራቱ በመጪው ክረምት የሚጠናቀቀው የ31 አመቱ የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ በቴሪ ሄንሪው ሞናኮ በጥብቅ ይፈለጋል።
 (Le Sport 10 - in French)



•ባርሴሎና የፒ.ኤስ.ጂውን አማካይ አድናን ራቢዮ ለማዘዋወር ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠሉን Mundo Deportivo አስነብቧል ።ራቢዮ ከካታላኑ ክለብ ጋር በግል ከስምምነት ላይ መድረሱም እየተነገረም ይገኛል።ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ከባርሴሎና በተጨማሪ በጁቬንትስ፣በሊቨርፑል፣በማንችስተር ሲቲ እና በባየርን ሙኒክ
 ይፈለጋል።



•የቶተንሀሙ ተከላካይ ዳቪንሰን ሳንቼዝ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ከስፐርስ እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን ዋነኛ ፈላጊው ደግሞ የስፔኑ ሪያል ማድሪድ ነው ሲል Don Balon አስነብቧል ።ኮሎምቢያዊው ተጨዋች በፒኤስጂ፣ኤሲ ሚላን እና ባርሴሎናም በጥብቅ ይፈለጋል።



•ሊዮኔል ሜሲ ኔይማር በድጋሚ ወደ ባርሴሎና ቢመጣ ደስተኛ እንደሚሆን ተናገረ።
ኔይማር 2017 ላይ ወደ ፒኤስ ጂ ከተዘወረ በኃላ የአለማችን ውዱ ተጨዋች የሆነ ሲሆን ከዚያ ጊዜ አንስቶ ስሙ ከባርሴሎና እንዲሁም ከሪያል ማድሪድ ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።
ሜሲም ዛሬ እንደተናገረው ምንም እንኳን ተጨዋቹን ዳግመኛ ወደ ባርሴሎና መመለስ አዳጋች ቢሆንም ቢሳካ ግን ደስተኛ እንደሚሆን ተናግሯል ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...