ማንቸስተር ዩናይትድ ፖግባን ለመሸጥ አቅዷል
ማንቸስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን አማካይ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለመሸጥ ማቀዱን Mirror አስነብቧል ።ጋዜጣው በዘገባው እንዳተተው ከሆነ ቀያይ ሰይጣኖቹ ተጫዋቹን በሪከርድ ዋጋ ለቀድሞው ክለቡ ጁቬንትስ ለመሸጥ ያሰቡ ሲሆን ከአሮጊቷ ተጨዋች ለማዛዋወርም ነው ያቀዱት።
ፖግባ ከፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ጋር በዚህ አመት ግጭት ውስጥ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጣው እንዳለው ግን ቀያይ ሰይጣኖቹ ሞሪንሆ በክለቡ ቢቆዩም ባይቆዩም ፈረንሳዊውን አማካይ ለአሮጊቷ መሸጥን ይሻሉ።
ዩናይትድ ፖግባን ለጁቬንትስ ሲሸጥ ከሚራለን ፒያኒች ወይም ከአሌክስ ሳንድሮ አንዱን ተጨዋች ማዘዋወርንም በውሉ ለማካተት ነው ያቀደው ።
No comments:
Post a Comment