ሮናልዶ በጁቬንትስ ታሪክ ሴሪያ ላይ 5,000ኛውን ግብ አስቆጠረ
በጁቬንትስ ቤት የተለያዩ ሪከርዶችን በመሰባበር ላይ የሚገኘው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንት ጁቬንትስ በሴሪያው ታሪክ 5000ኛውን ግብ ሲያስቆጥር የግቧ ባለቤት ሆኗል ።
ሮናልዶ ትናንት በደርቢ ዴላ ሞሌ ጁቬንትስ ከ ቶሪኖ ጋር በነበረው ጨዋታ በ70ኛው ደቂቃ ነው ግቡን ያስቆጠረው ።
በጁቬንትስ ታሪክ ከዚህ በፊት 4,000ኛውን ግብ ያስቆጠረው ጣሊያናዊው አጥቂ ዲ ቫዮ በ2003፣እንዲሁም 3,000ኛውን ደግሞ ማሲሞ ቢርሳቺ ነበር ።
2000ኛው ጂያኒ ሮሲ በ1962 1,000ኛውን ደግሞ ካርሎ ፓሎራ በ1948 መሆኑን ታሪክ ይነግረናል ።
No comments:
Post a Comment