Friday, December 7, 2018

የቅዳሜ ረፋድ አዳዲስ እግር ኳሳዊ ዜናዎች

➡️ቤልጄሚያዊው የ25 አመት አጥቂ ሮሜሮ ሉካኩ አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ደስተኛ ባለመሆኑ በማንቸስተር ዩናይትድ የሚኖረውን ቆይታ እያጤነበት ነው።ሉካኩ ከሞሪንሆ ጋር ያለው ግንኙነት ከተበላሸ ሰነባብቷል ። (sun)



➡️ጆዜ ሞሪንሆ በቅርብ አመታት ማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል በዚህ መልኩ ገንዘብ በማውጣት ከቀጠሉ ማንቸስተር ዩናይትድ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይከብደዋል ሲሉ ተናግረዋል ። (mirror )


➡️ፓሪሰን ዤርመን Financial fair play ለመከላከል ከብራዚላዊው አጥቂ ኔይማር ወይም ከፈረንሳዊው አጥቂ ኪሊያን ምባፔ አንዱን ለመሸጥ እንደተዘጋጀ ታማኙ የፈረንሳይ ጋዜጣ L'Equipe አስነብቧል ።
በዘገባው ላይ አስተያየቱን የሰጠው ፓሪሰኝ ዤርመን ግን ዘገባው ሀሰት ነው ብሏል ። (PSG-iN French)



➡️የአያክሱ የ21 አመት አማካይ ፍራንክ ዲ ዮንግ ከማንቸስተር ሲቲ ይልቅ ፓሪሰን ዤርመንን መቀላቀል ይፈልጋል ።የፈረንሳዩ ክለብም ለኔዘርላንዳዊው ተጨዋች €75M አሰናድቷል። (De Telegraaf- ij Dutch )



➡️ሊቨርፑል በውሰት ደርቢን የሚገኘውን የ21 አመት ዊንገር ሀሪ ዊልሰን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ አንፊልድ ለመመለስ አቅዷል ። (Liverpool Echo)



➡️ኡናይ ኤምሬ በሳምንቱ መነጋገሪያ የሆነው የአርሰናል ተጨዋቾች ፓርቲ በእጅጉ አስቆጥቷቸው ።ዲሲፕሊን ላይ ቆራጥ የሆኑት ስፔናዊ አሰልጣኝ አራት ተጨዋቾችንም ይቀጣሉ ተብሏል ። (sun)




➡️ አትሌቲኮ ማድሪድ ማክሲ ጎሜዝን ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል ።የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የግብ ማስቆጠር ችግር በቡድኑ ውስጥ አለ።
የሴልታ ቪጎው አጥቂ በፍራሽ አዳሾቹ ቤት በዚህ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈለግ ሲሆን በዘንድሮው አመት በክለቡ በ13 ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍም ችሏል።



➡️ሄሬራ በማንቸስተር ዩናይትድ አዲስ ውል ሊፈራረም ነው።የ29 አመቱ አማካይ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ውል ሊፈራረም መሆኑን ከወደ እንግሊዝ የሚወጡ ሚዲያዎች እየጠቆሙ ነው።
ሄሬራ 2014 ላይ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ከመጣ አንስቶ በጆዜ ሞሪንሆ ስር  ኤፍ ኤ ካፕ፣ኢኤፍ ኤል ካፕ እና ዩሮፓ ሊግን አሳክቷል ።



➡️ሀይሳጅ ስሙ ከቼልሲ ጋር እየተያያዘ ነው።
አልባኒያዊው የናፖሊ ተጨዋች ኤልሳንድ ሀይሳጅ ከቀድሞው አሰልጣኙ ማውሩዚዮ ሳሪ ጋር በድጋሚ በስታንፎርድ ብሪጅ ለመገናኘት ዕድሉ የተከፈተለት ይመስላል ።
ቼልሲ ዴቪድ ዛፓኮስታን በአሁኑ ሰዓት በመጠቀም ላይ ባለመሆኑ የሀይሳጅን ዝውውር ለመጨረስ የሚፈልገው በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው።
በስተመጨረሻ ዛሬ ምሽት 2:30 በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ከ ማንቸስተር ሲቲ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀጥታ እናስተላልፋለን 

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...