➡️ አትሌቲኮ ማድሪድ ማክሲ ጎሜዝን ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል ።የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የግብ ማስቆጠር ችግር በቡድኑ ውስጥ አለ።
የሴልታ ቪጎው አጥቂ በፍራሽ አዳሾቹ ቤት በዚህ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈለግ ሲሆን በዘንድሮው አመት በክለቡ በ13 ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍም ችሏል።
➡️ሄሬራ በማንቸስተር ዩናይትድ አዲስ ውል ሊፈራረም ነው።የ29 አመቱ አማካይ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ውል ሊፈራረም መሆኑን ከወደ እንግሊዝ የሚወጡ ሚዲያዎች እየጠቆሙ ነው።
ሄሬራ 2014 ላይ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ከመጣ አንስቶ በጆዜ ሞሪንሆ ስር ኤፍ ኤ ካፕ፣ኢኤፍ ኤል ካፕ እና ዩሮፓ ሊግን አሳክቷል ።
➡️ሀይሳጅ ስሙ ከቼልሲ ጋር እየተያያዘ ነው።
አልባኒያዊው የናፖሊ ተጨዋች ኤልሳንድ ሀይሳጅ ከቀድሞው አሰልጣኙ ማውሩዚዮ ሳሪ ጋር በድጋሚ በስታንፎርድ ብሪጅ ለመገናኘት ዕድሉ የተከፈተለት ይመስላል ።
ቼልሲ ዴቪድ ዛፓኮስታን በአሁኑ ሰዓት በመጠቀም ላይ ባለመሆኑ የሀይሳጅን ዝውውር ለመጨረስ የሚፈልገው በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው።
➡️ሮማ ቬል ሂናን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
ሮማ የፌይኖርዱን አማካይ ቶኒ ቪልሌይና በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር መንቀሳቀስ ጀምሯል ።
የ23 አመቱ ተጨዋች በተደጋጋሚ ከሮተርዳም እንደሚለቅ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን ወደ ሳምፕዶሪያ ለመዘዋወር ተቃርቦም እንደነበር ይታወሳል ።
➡️የአንድሬ ጎሜዝ ቆይታ በኤቨርተን እጅ እንዳልሆነ ማርኮ ሲልቫ ተናገሩ።
ማርኮ ሲልቫ አሁንም ኤቨርተን አንድሬ ጎሜዝን በቋሚነት ማስፈረም ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደለም ።
አማካዩ በሲዝኑ መጀመሪያ ከባርሴሎና በውሰት ከመጣ አንስቶ አመርቂ የሚባል እንቅስቃሴን በቡድን ውስጥ በማድረግ ላይ ይገኛል ።
በዚህም ምክንያት ኤቨርተን ፖርቹጋላዊውን የ24 አመት ተጨዋች በቋሚነት ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ቢሆንም አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ግን ጉዳዩ በነሱ እጅ አለመሆኑን ገልፀዋል ።
➡️ማልኮም በቻይና ክለብ ይፈለጋል ።
የቻይናው ክለብ ጉዋንግዙ ኤቨርግራንዴ የባርሴሎናውን አጥቂ ማልኮም ባልተጠበቀ ሁኔታ ለማዘዋወር ጥረት ላይ መሆኑን Direct tv sports አስነብቧል ።
ጉዳት ላይ የሚገኘው አጥቂ ህይወት በካምፕ ኑ የከበደችው ሲሆን ስሙም በስፋት ከዝውውር ጋር በመያያዝ ላይ ነው።
ፓውሊንሆን ከዚህ በፊት ያዘዋወረው ጉዋንግዙ አሁን ደግሞ ሌላ ብራዚላዊ ከባርሴሎና ለመውሰድ እየሰራ ነው።
➡️ማንቸስተር ዩናይትድ £40M በመክፈል ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆን የሞሪንሆ ተተኪ ለማድረግ እየሰራ ነው።
ማንቸስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ የሞሪንሆ ተተኪ ለማድረግም £40M ለመክፈል ዝግጅቱን አጠናቋል።
የቶተንሀሙ አሰልጣኝ ፖርቹጋላዊውን በውጥረት ላይ ያሉትን አሰልጣኝ ለመተካትም ሁነኛ ሰው መሆኑን የግሌዘር ቤተሰቦች ያምናሉ ።
እንግሊዝ ፕርሜርሊግ
⚽️ቅዳሜ
➡️ በርንስማውዝ ከ ሊቨርፑል - 8:30
➡️ አርሰናል ከ ሀደልስፊልድ ታወን - 12:00
➡️ በርንሌይ ከ ብራይተን - 12:00
➡️ ካርዲፍ ሲቲ ከ ሳውዝሀምፕተን - 12:00
➡️ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ፉልሀም - 12:00
➡️ ዌስትሀም ከ ክሪስታል ፓላስ- 12:00
➡️ ቼልሲ ከ ማንቸስተር ሲቲ - 2:30
➡️ ሌስተር ሲቲ ከ ቶተንሀም - 4:45
⚽️እሁድ
➡️ ኒውካስል ዩናይትድ ከ ዎልቭስ - 1:00
⚽️ሰኞ
➡️ ኤቨርተን ከ ዋትፎርድ - 5:00
🛑 ቡንደስሊጋ
⚽️አርብ
➡️ ወርደር ብሬመን ከ ፎርቹን
⚽️ቅዳሜ
➡️ ባየርሙኒክ ከ ኑረምበርግ - 11:30
➡️ ሻልካ 04 ከ ቦርሲያ ዶርትመንድ - 11:30
➡️ ባየር ሊቨርኩሰን ከ ኦግስበርግ - 11:30
➡️ ፍራይቡርግ ከ አርቢ ላይፕዚክ - 11:30
➡️ ወልፍስበርግ ከ ሆፈንየም - 11:30
➡️ ሀርታበርሊን ከ ኢንትራንክ ፈርት - 2:30
⚽️እሁድ
➡️ ሜንዝ ከ ሀኖቨር - 11:30
➡️ ቦርሲያ ሞንቼግላድባህ ከ ስቱትጋርት - 2:00
🛑 ስፔን ላሊጋ
➡️ ሌጋኔስ ከ ጌታፌ - 5:00
➡️ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ - 8:00
➡️ ቫሌንሺያ ከ ሲቪያ - 12:15
➡️ ቪያርያል ከ ሲልታቪጎ - 2:30
➡️ ኢስፓኞል ከ ባርሴሎና - 4:45
⚽️እሁድ
➡️ ኢባር ከ ሌቫንቴ - 8:00
➡️ ሁሴኬ ከ ሪያል ማድሪድ - 12:15
➡️ ሬያል ሶሲዳድ ከ ሬያል ቫላዶሊድ - 2:30
➡️ ሬያል ቤቲስ ከ ራዮ ቫይካኖ - 4:45
⚽️ሰኞ
➡️ አትሌቲኮ ቢልባኦ ከ ጂሮና - 5:00
🛑የጣልያን ሴሪያ
⚽️አርብ
➡️ ጁቬንቱስ ከ ኢንተር ሚላን - 4:30
⚽️ቅዳሜ
➡️ ናፖሊ ከ ፍሮሲኖኔ - 8:00
➡️ ካግላሪ ከ ሮማ - 2:00
➡️ ላዚዮ ከ ሳምፒዶሪያ - 4:30
⚽️እሁድ
➡️ ሳሱሎ ከ ፊዮረንቲና - 8:30
➡️ ኢምፖሊ ከ ቦሎኛ - 12:00
➡️ ፓርማ ከ ቼቮ ቬሮና - 12:00
➡️ ዩዲኒዜ ከ አቲላንታ - 12:00
➡️ ጄኖዋ ከ ስፓል - 2:00
➡️ ኤስሚላን ከ ቶሪኖ - 4:30
No comments:
Post a Comment