Tuesday, December 4, 2018

የማክሰኞ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዜናዎች

የሀገር ውስጥ ዜናዎች 
በዘንድሮው አመት ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር ዛሬ የመልስ ጨዋታውን በአዲስ አበባ ስቴዲየም ያደርጋል ።የባለፈው አመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኖቹ ባሳለፍነው ሳምንት በመጀመሪያው ጨዋታ ጅቡቲ ድረስ ተጉዘው የጅቡቲን ክለብ ጅቡቲ ቴሌኮም 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል ።


እናም ዛሬ የዚህን ጨዋታ መልስ በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚያደርጉ ሲሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ከቻሉ የግብፁን ጠንካራ ክለብ አል አህሊ የሚገጥሙ ይሆናል ።


የባህር ማዶ ዜናዎች 

አዝብሉኬታ በቼልሲ ለተጨማሪ አራት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።ስፔናዊው ተከላካይ በስታንፎርድ ብሪጅ እስከ 2022 ለመቆየት የተስማማው ትናንት ሲሆን በአዲሱ ውሉ መሰረት በሳምንት £150,000 የሚከፈለውም ይሆናል ።አዝብኬታ በቼልሲ ደጋፊዎች ዘንድ በእጅጉ የሚወደድ ተጨዋች መሆኑ ይታወቃል ።



ሉካ ሞድሪች በሪያል ማድሪድ ቤት የእግር ኳስ ህይወቱን መጨረስ እና ጫማ መስቀል እንደሚፈልግ ተናገረ።ስሙ በስፋት ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር በመያያዝ ላይ የሚገኘው ክሮሺያዊው አማካይ ትናንት በፍራንስ ፉትቦል የሚዘጋጀውን ባሎንዶር ካሸነፈ በኃላ ነው ይህንን አስተያየት የሰጠው።



ጋርዲዮላ ለሮይ ሳኔ በማንቸስተር ሲቲ ቤት ለበርካታ አመታት ይቆያል ብሎ እንደሚያስብ ተናገረ።ስፓኒያርዱ የመልካም እግር ኳስ አቀንቃኝ ጀርመናዊው ተጨዋች የኬቨን ደብሮይነን እና ራሂም ስተርሊንግን ፈለግ በመከተል አዲስ ውል እንደሚፈርምም ተናግሯል ።



አርሰናል ፣ቶተንሀም፣ኤቨርተን እና ሳውዝሀምተን የራቢ ሌብዙኩን ተጨዋች ሀንስ ዎልፍ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ።ኦስትሬያዊው አማካይ በርካታ ከቶተንሀሙ ኤሪክሰን ጋር አጨዋወቱን የሚያመሳስሉት በUEFA YOUTH LEAGUE 2017 ላይ ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ችሎም ነበር ።
ለክለቡ ደግሞ ባሳለፍነው አመት በአጠቃላይ 45 ጊዜ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን 12 ግቦችን ከመረብ ሲያዋህድ ስምንት ኳሶችን አሲስት አድርጓል ።




ኡናይ ኤምሬ የአሮን ራምሴ የኮንትራት ጉዳይ በትኩረት እየተከታተሉት ነው።አሁን ያለው ውል በአመቱ መጨረሻ የሚያልቀው ራምሴ በአመቱ መጨረሻ ፍሪ ኤጀንት የሚሆን ሲሆን በአሁኑ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ባየርን ሙኒክን ጨምሮ በርካታ ክለቦች ይፈልጉታል ።በሳምንቱ መጨረሻ በሰሜን ለንደን ደርቢ ድንቅ የነበረው ዌልሳዊው አማካይ በአርሰናል መቆየት የሚፈልግ ቢሆንም ክለቡ ግን ኮንትራት ሊያቀርብለት አልቻለም ።ሆኖም አሁን ኡናይ ኤምሬ የ27 አመቱን ተጨዋች አዲስ ኮንትራት ለማስፈረም አቅደዋል ።




ማንቸስተር ዩናይትድ ቶፕ 4 ውስጥ ለመግባት 'ተዐምር'
ይፈልጋል ሲሉ ሞሪንሆ ተናገሩ።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ክለባቸው በቀጣዩ አመት
ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድል ማግኘት ጠባብ መሆኑን
ተናግረዋል ።ቀያይ ሰይጣኖቹ ባሳለፍነው ቅዳሜ
ከሳውዝሀምተን ጋር 2ለ2 ከተለያዩ በኃላ በፕሪሚየር ሊጉ
ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሁለት
ነጥብ ብቻም ነው ማሳካት የቻለው ።
በአሁኑ ሰዓት ከመሪው ክለብ በ16 ነጥብ የሚያንሰው
ማንቸስተር ዩናይትድ አራተኛ ደረጃ ላይ ካለው አርሰናል ደግሞ
በስምንት ነጥብ ያንሳሉ። ባለፈው አመት ከነበረን የተጨዋቾች ጥራት አንፃር እና ቶፕ 4
ውስጥ ከነበሩት ክለቦች ብቃት አንፃር ሁለተኛ ደረጃን ይዘን
ማጠናቀቅ እንደምንችል ተናግሬ ነበር ።ዘንድሮ ግን በርካታ
ችግሮችን እየተጋፈጥን ነው።ገና አመቱ ከመጀመሩ በፊት
የውድድር ዘመኑ ከባድ እንደሚሆን ተናግሬ ነበር ።አሁን
የፊታችን ያሉትን ጨዋታዎች በቻለው መጠን ማሸነፍ አለብን
ቶፕ 4 ውስጥ ለመግባት ግን ተዐምር ያስፈልጋል።



ሞድሪች ባሎንዶርን አሸነፈ።
ባሳለፍነው አመት ከክለቡ ጋር ሻምፒዮንስ ሊግን ከሀገሩ ጋር
ለአለም ዋንጫ ፍፃሜ የደረሰው ሞድሪች ትናንት ለሊት
የባሎንዶር ሽልማትን በማግኘት የመጀመሪያው ክሮሺያዊ
ተጨዋች ሆኗል ።ሞድሪች ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤አንቶዋን
ግሬዝማን እና ሊዮኔል ሜሲን በማስከተል ነው ማሸነፍ የቻለው

በዚህም ምክንያት ሞድሪች ከአስር አመት በኃላ ከሜሲ እና
ሮናልዶ ውጪ ባሎንዶርን ያሸነፈ ተጨዋችም ሆኗል
።ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለቱ ኮከቦች ውጪ ባሎንዶርን ያሸነፈው
2007 ካካ መሆኑ አይዘነጋም ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...