ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ክለባቸው በቀጣዩ አመት ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድል ማግኘት ጠባብ መሆኑን ተናግረዋል ።ቀያይ ሰይጣኖቹ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከሳውዝሀምተን ጋር 2ለ2 ከተለያዩ በኃላ በፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻም ነው ማሳካት የቻለው ።
በአሁኑ ሰዓት ከመሪው ክለብ በ16 ነጥብ የሚያንሰው ማንቸስተር ዩናይትድ አራተኛ ደረጃ ላይ ካለው አርሰናል ደግሞ በአራት ነጥብ ያንሳሉ።
ባለፈው አመት ከነበረን የተጨዋቾች ጥራት አንፃር እና ቶፕ 4 ውስጥ ከነበሩት ክለቦች ብቃት አንፃር ሁለተኛ ደረጃን ይዘን ማጠናቀቅ እንደምንችል ተናግሬ ነበር ።ዘንድሮ ግን በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጥን ነው።ገና አመቱ ከመጀመሩ በፊት የውድድር ዘመኑ ከባድ እንደሚሆን ተናግሬ ነበር ።አሁን የፊታችን ያሉትን ጨዋታዎች በቻለው መጠን ማሸነፍ አለብን ቶፕ 4 ውስጥ ለመግባት ግን ተዐምር ያስፈልጋል
No comments:
Post a Comment