ሉካ ሞድሪች የ2018 ባሎንዶርን አሸነፈ
ባሳለፍነው አመት ከክለቡ ጋር ሻምፒዮንስ ሊግን ከሀገሩ ጋር ለአለም ዋንጫ ፍፃሜ የደረሰው ሞድሪች ትናንት ለሊት የባሎንዶር ሽልማትን በማግኘት የመጀመሪያው ክሮሺያዊ ተጨዋች ሆኗል ።ሞድሪች ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤አንቶዋን ግሬዝማን እና ሊዮኔል ሜሲን በማስከተል ነው ማሸነፍ የቻለው ።
በዚህም ምክንያት ሞድሪች ከአስር አመት በኃላ ከሜሲ እና ሮናልዶ ውጪ ባሎንዶርን ያሸነፈ ተጨዋችም ሆኗል ።ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለቱ ኮከቦች ውጪ ባሎንዶርን ያሸነፈው 2007 ካካ መሆኑ አይዘነጋም ።
No comments:
Post a Comment