የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በሰሜን ለንደን ደርቢ ቶተንሀምን ባሸነፉበት ጨዋታ ኦዚል ቡድኑ ውስጥ ይኑር አይኑር እንዳላወቁ ተናግረዋል ።ጀርመናዊው የ30 አመት አማካይ ከበርንማውዝ ጋር ከሳምንት በፊት ያልተሰለፈ ሲሆን በተጠባቂው ሰሜን ለንደን ደርቢም አልነበረም ።ክለቡ ምክንያቱን ሲያስረዳው ተጨወቹ የጀርባ ጉዳት አጋጥሞታል ብሏል ።ኦዚል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ ከኢንተር ሚላን ጋር በመያያዝ ላይ ነው። (Mail)
ፖላንዳዊው የናፖሊ አማካይ ፒዮትር ዜኔንስኪ ምንም እንኳን በሊቨርፑል በጥብቅ ቢፈለግም በኔፕልሱ ክለብ አዲስ ኮንትራት ሊፈርም መሆኑን ከወደ ጣሊያን የሚወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።የ24 አመቱ ተጨዋች ዠርደን ክሎፕ በጥብቅ ከሚፈልጓቸው ተጨዋቾች አንዱ ነው። (Calciomercato)
አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን አጥቂ ቶኑ አብረሃም ከቼልሲ በውሰት ለመውሰድ ድርድር ላይ ይገኛል ።አስቶን ቪላ የ21 አመቱን ተጨዋች ከአንድ አመት በላይ የሆነ ውልም ሊያቀርብለት ይሻል። (Birmingham
Mail)
የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ ከሳውዝሀምተን ጋር 2ለ2 ከተለያዩ በኃላ አብጠልጥለዋል።አወዛጋቢው አሰልጣኝ ስሙ በስፋት ከዝውውር ዜናዎች ጋር በመያያዝ ያለውን ተጨዋች 'ቫይረስ' ሲሉም ገልፀውታል ። (Daily Record)
የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ በመርሲሳይድ ደርቢ በ95ተኛው ደቂቃ በተቆጠረባቸው ግብ በሊቨርፑል ሲሸነፉ የቀያዮቹ አሰልጣኝ ዠርደን ክሎፕ ሜዳ ውስጥ በመግባት ያሳዩት የደስታ አገላለፅ ይቅር የማይባል ነው ሲሉ ተናግረዋል ። (Liverpool Echo)
የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቅዳሜ ዕለት በርንማውዝን ባሸነፉበት ጨዋታ የ31 አመቱ አጥቂ ሴርጂዮ አጉዌሮ ያልተሰለፈበት ምክንያት ድካም ስለነበረበት እና ቢሰለፍ ለአንድ ወር ሊጎዳ ይችል እንደነበር ተናግረዋል ። (Times - subscription required)
የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ፍሬድ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ደስተኛ አለመሆኑ ተነገረ።ብራዚላዊው ተጨዋች እስካሁን በፕሪሚየር ሊጉ ስድስት ጨዋታዎችን ብቻ የጀመረ ሲሆን ይህም ምቾት አልሰጠውም ። (Manchester Evening News)
የቶተንሀሙ አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ በለንደን ደርቢ ምንም እንኳን ሽንፈትን ቢያስተናግዱም አርጀንቲናዊው የ20 አመት ተከላካይ ሁዋን ፎይዝ ምርጥ አቋሙን እንዳሳየ እና በቡድኑ ውስጥ ካሉ ቁልፍ ተጨዋቾች አንዱ መሆኑን ተናግሯል ።
(Football.London)
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ዛሬ በሻምፒዮንስ ሊግ ከዚህ በኃላ Video assistant referee (VAR) እንዲተገበር ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል ።
(Times -
No comments:
Post a Comment